በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ለሚገኙ ለግንባር ቀደም ፈፃሚዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና በወልቂጤ ከተማ እየተሰጣቸው ይገኛል።

የክልሉ ረዳት የመንግስት ተጠሪና የብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የፓለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ይሁን አሰፋ እንደገለጹት ለክልሉ ልማትና የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ የወጣቶችና የሴቶች ተሳትፎ ወሳኝ ነዉ።

ለክልሉ እንደአንድ ፀጋ የሚቆጠር ይህንን ሀይል ዘመኑን በሚመጥን ዕዉቀትና ክህሎት ማስታጠቅ እንደሚገባም ገልጸዋል።

የክልሉ አመራር አካዳሚ ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ብላቱ ስልጠናውን ባስጀመሩበት ወቅት እንደተናገሩት በመንግሥት ተቋማት የሚያገለግሉ አመራር እና ፈፃሚዎች እውቀት ሊያስጨብጡና ግንዛቤን ሊያሳድጉ የሚችሉ ስራዎች እየተሰራ ይገኛል።

ወጣቶች እና ሴቶች የልማት ግቦች ለማሳካት የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች እውን ለማድረግ ሀላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ለማስቻል እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

የጋራ እቅዶች ለማሳካት የመሪነት ሚና ወሳኝ በመሆኑ ስልጠና ግንዛቤ መፍጠር አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱም አቶ ተስፋዬ ብላቱ ተናግረዋል።
የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት ረዳት ተጠሪ እና ብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካ እና የርእዮተ አለም አቅም ግንባታ ዘርፍ ሀላፊ አቶ ይሁን አሰፋ በበኩላቸው ጊዜውና ወቅቱን ያማከለ ብቁና ተወዳዳሪ የሰው ሀይል መፍጠር የግድ መሆኑን ገልጸዋል።

የስራ እድል ለመፍጠር ምቹ የሆነ ማህበረሰብ መካከል በመሆናችን ያሉን ፀጋዎች በተገቢው ለመጠቀም መስራት ይጠበቃል ብለዋል።
ሁሉም በተመደበበት መስክ ጠንክሮ በመስራት የመሪነት ድርሻውን በመወጣት ብልፅግና ማረጋገጥ እንቅፋቶችን ለማስወገድ ትግል ማድረግ እንደሚገባም አመላክተዋል።

ስልጠናው ለሶስት ቀናት የሚቆይ ሲሆን መሰረታዊ የመሪነት ጥበብ ውሳኔ ሰጭነት አገልጋይነት እዲሁም አለምአቀፋዊ ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበ መሪነትን የተመከተ እንደሚሆን ከአመራር አካዳሚው የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *