በማዕከላዊ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ለ31 ማህበራት የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ አስረከበ።

በማዕከላዊ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ለ31 ማህበራት የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ አስረከበ።

ከተማ አስተዳደሩ በጉብሬ ክፍለ ከተማ ጋሶሬና ኤዋን ተብለው በሚጠሩ አካባቢዎች ወደ አዲሱ ክልል ለመጡ አመራሮችና ሰራተኞች፣ ለመምህራን፣ ለከተማ ነዋሪዎች ና በክብር ለተመለሱ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ከተማ አስተዳደሩ የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ አስረክቧል።

በከተማ አስተዳደሩ 230 ማህበራት በመኖሪያ ቤት ህብረት ስራ ማህበራት የተደራጁ ሲሆን 50 በመቶው በመቆጠብ ህጋዊ ሰውነት ያላቸው ማህበራት 146 እንደሆኑ ተገልጿል።

በዛሬው ዕለት ቦታ የሚረከቡት ማህበራት ህጋዊ ሰውነት ካላቸውና የሚጠበቅባቸውን አስፈላጊውን መስፈርትና ግዴታ ካሟሉት 146 ማህበራት ውስጥ 31 ማህበራት ብቻ ናቸው ።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ዝናቡ ተካበ እንደተናገሩት የሚገነቡት ቤቶች የከተማውን ደረጃ በሚመጥን ዲዛይን መገንባት አለበት ነው ያሉት።

በቀጣይም ህጋዊ ሰውነት ለተሰጣቸውና አስፈላጊውን መስፈርት ላሟሉ ቀሪ ማህበራቶች መሬት የማስተላለፍ ስራው ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ሲሉም ተናግረዋል ።

የጉራጌ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አበራ ወንድሙ በመሬት ርክክብ ፕሮግራሙ ተገኝተው እንደተናገሩት ውስን የሆነውን የከተማ መሬት ለታለመለት ዓላማ በአግባቡ መጠቀም ይኖርብናል ብለዋል ።

በከተሞች የዜጎችን የመኖሪያ ቤት ፍላጎት እንዲሟላ ለማድረግ ዞኑ የተጠናከረ ስራ እንደሚሰራ ጠቅሰው በቀጣይም ህጋዊ ሰውነት ላላቸውና አስፈላጊ መስፈርት ላሟሉ የተደራጁ ማህበራት ፍትሀዊ በሆነ መንገድ መሬት እንዲተላለፍ ይደረጋል ሲሉ ምክትል አስተዳዳሪው ተናግረዋል ።

የጉራጌ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ ታምራት ውድማ በበኩላቸው መሬት የተላለፈላቸው ማህበራት አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማድረግ በፍጥነት ወደ ግንባታመግባት አለባቸው ብለዋል ።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ እንዳለ ስጦታው እንደገለጹት የከተማ ነዋሪውን የመኖሪያ ቤት ፍላጎት ለማሟላት ከተማ አስተዳደሩ የተጠናከረ ስራ ይሰራል ነዉ ያሉት ።
ሌሎች ማህበራት የሚጠበቅባቸውን ግዴታና መስፈርት አሟልተው ሲገኙ በተመሳሳይ መንገድ የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ እንደሚያገኙ ከንቲባው መናገራቸውን ከክልሉ ከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *