በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አዘጋጅነት በቡታጅራ ከተማ ሲካሄድ የነበረው የባህልና ልዩ ልዩ ስፖርት ውድድር ፌስቲቫል የጉራጌ ዞን በአንደኝነት አጠናቀቀ።
የጉራጌ ዞን በተሳተፈባቸው ልዩ ልዩ የስፖርት ውድድሮች 29ወርቅ፣28 ብር፣24 ነሀስ በአጠቃላይ 81 ሜዳሊዎች በመሰብሰብ ውድድሩን በበላይነት ማጠናቀቅ ችሏል።
የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ፈይሰል ሀሰን እንዳሉት ጉራጌ ዞን ባደረጋቸው ውድድሮች ጠንካራና ተተኪ ስፖርተኞች ያሉባትና ቀጣይ በሀገርና በአለም አቀፍ ደረጃ በመወዳደር የዞኑ ብሎም የሀገር ስም የሚያስጠሩ ስፖርተኞች የታዩበት ነው።
ዞናችን ደግሞ ለስፖርት ዘርፍ ትልቅ አቅም ያለበት መሆኑን ጠቁመዋል
እነዚህ ስፖርተኞች በሀገር አቀፍ ውድድሮች እንዲሳተፉ እና ዘንድሮ ባልተሳተፍንባቸው ዘርፎች በመሳተፍ የዞኑ ማህበረሰብ የሚመጠን ውጤት ለማስመዝገብ በትኩረት እንሰራለን ብለዋል።
በዚህ ውድድር ብርቱ ፉክክርና ጠንካራ ተሳትፎ ያደረገው የጉራጌ ዞን አትሌቲክስ
16ወርቅ 12ብር 16ነሀስ 44ሜዳሊያ
👉ፓራ ሊፒክስ
8ወርቅ 9ብር 7ነሀስ 24ሜዳሊያ
👉በባህል ስፖርት
4ወርቅ 3ብር 1ነሀስ 8ሜዳሊያ
👉በቴክዋንዶ
1ወርቅ 1ብር 2ሜዳሊያ
👉በጠረፔዛ ቴኒስ
2ብር
👉እግር ኳስ
1ብር
👉በድምሩ
29ወርቅ 28ብር 24ነሀስ 81ሜዳሊያ በመሰብሰብ ውድድሩን በበላይነት ነው ያጠናቀቀው።
አቶ ፈይሰል አክለውም ለጉራጌ ዞን አስተዳደር ለአበባው ሰለሞን፣ለወረዳዎችና ድጋፍ ላደረጉ ሁሉ ምስጋናቸው አቅርበዋል።
የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ምክትልና የስፖርት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አደም ሽኩር በበኩላቸው በውድድሩ የተሳተፉ ስፖርተኞች ከሁሉም መዋቅሮች የተወጣጡ ሲሆን ለዚህም ሁሉም መዋቅሮች ድጋፍ አድርገዋል ነው ያሉት።
በዚህ ውድድር ተተኪ ስፖርተኞች ጎልተው የታዩበት ሲሆን ስፖርቱ ህዝባዊ መሰረት የያዘበት እንዲሁም ጨዋታዎቹም በፍጹም ስፖርታዊ ጨዋነት ማጠናቀቅ ተችሏል።
ይህ ደግሞ የህብረተሰቡ የእርስ በርስ ግንኙነት እንዲጎለብት ያደረገ ሲሆን በቀጣይ ደግሞ ፕሮጀክቶች፣ዳኞች፣ስፖርተኞች፣አሰልጣኞች በማጠናከርና በማፍራት ዞኑን በሁሉም የስፖርት አይነት ቀዳሚ እንዲሆን እንሰራለን ብለዋል።