በመጀመሪያ ግማሽ ዓመት በዞኑ የታቀዱ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች አፈጻጸም አበረታች መሆኑን የጉራጌ ዞን የምክር ቤት አባላት ገለጹ።

የጉራጌ ዞን ምክር ቤት 4ኛ ዙር 11ኛ ዓመት 25ኛ መደበኛ ጉባኤውን በወልቂጤ ከተማ አካሂዷል።

በጉባኤው የተገኙ የምክር ቤት አባላት የአስፈጻሚ መስሪያ ቤቶች የአንደኛ ግማሽ አመት አፈጻጸም ላይ እንዳሉት በሀገሪቱ የተከሰተውን የትምህርት ስብራት ለመጠገን አበረታች ስራዎች እየተሰራ ይገኛል።

በዚህም ባለሀብቶችና ህብረተሰቡ በማስተባበር የአንደኛ ደረጃ የተማሪዎች መጽሐፍ በማሳተም ተደራሽ ለማድረግ የሚደረገው ጥረት እና በቅድመ መደበኛና በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ልጆች በአፍ መፍቻ ጉራጊኛ ቋንቋ እንዲማሩ መደረጉ የሚበረታታ መሆኑን ተገልጿል።

የጉራጌ ህዝብ ቱባ ባህሎችና እሴቶች ለማስተዋወቅ የተከናወኑ ተግባራት የሚረታቱ ሲሆን በቀጣይ ተተኪ የባህል ኪነት ቡድን የማፍራት ስራ ታቅዶ መሰራት አንደሚገባ እንዲሁም በዞኑ የኢንቨስትመንት ቦታ ወስደው ወደ ልማት ባልገቡ ባለሀብቶች ላይ የተጀመረውን እርምጃ መውሰድ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ገልጸዋል።

የግብርና ምርትና ምርታማነት ለማሰደግ የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎች አርሶ አደሩ እንዲጠቀም የማድረግ ስራ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገ እና በአምና መኸር እርሻ የተከሰተውን የግብዓት አቅርቦት ችግር ለመቅረፍ የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት ከወዲሁ መከናወን እንዳለበት የምክር ቤቱ አባላት ተናገሩ።

አክለውም በዞኑ በግንባታ ሂደት ላይ የሚገኙ ካፒታል ፕሮጀክቶች በወልቂጤ ከተማ የተጀመሩ የውስጥ ለውስጥ የአስፋልት መንገዶች ፣ የአዳሪ ትምህርት ቤትና የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶች ግንባታ በወቅቱ ማጠናቀቅ ፣ በቆሴ፣ በወልቂጤና በዳርጌ አካባቢዎች የተፈጠረውን የጸጥታ ችግሮች መቅረፍ፣ ያደሩ የማዳበሪያ እዳዎች ተመላሽ እንዲሆኑ፣ የኑሮ ውድነት ለማረጋጋት የቅዳሜና የእሁድ ገበያዎች በሁሉም አካባቢ ማጠናከር እንደሚገባ በጉባኤው ተጠይቋል።

በተያያዘ በወልቂጤ መናኸሪያ ተሳፋሪዎች በትራንስፖርት ታሪፍ ልክ በትኬት ከከፈሉ በኋላ መንገድ ላይ ተሳፋሪዎችን በማስገደድ ትርፍ እንዲከፍሉ የሚደረግ መሆኑንና የከተማው ህዝብ በባጃጅ ላይ ከታሪፍ በላይ እየከፈለ ለከፍተኛ ብዝበዛ እየተዳረገ በመሆኑ አፋጣኝ የእርምት እርምጃ ሊወሰድ እንደሚገባ የምክር ቤቱ አባላት አሳስበዋል።

የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ በጉባኤ ማጠቃለያ እንደተናገሩት ከምክር ቤቱ አባላት የተነሱ ጥያቄዎች የቀጣይ የእቅድ አካል በማድረግ ክፍተቱ ለመሙላት ርብርብ ይደረጋል።

የስራ እድል ለመፍጠርና የኑሮ ውድነት ለማረጋጋት ከፍተኛ አቅም የሚፈጠረውን የግብርና ልማት የማጠናከር ስራ በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

በግንባታ ላይ የሚገኘው የአዳሪ ትምህርት ቤት በማጠናቀቅ ወደ ስራ ለማስገባት ይሰራል ያሉት ዋና አሰተዳዳሪው ዞኑ የሚያመነጨውን ሀብት አሟጦ የመሰብሰብ ስራ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የምጉራጌ ዞን ምክር ቤት የዞኑ ክፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንትና ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው ለረጅም ዓመታት ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ ሞሲሳ ቆርቻና አቶ ፈህሩ አብራር ከኃላፊነት በማንሳት የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዋና ፕሬዚዳንት #አቶሙዘኪርአወል አድርጎ ሹሟል።

በተመሳሳይ ምክር ቤቱ በዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ለተለያዩ አስፈፃሚ መስሪያ ቤት ኃላፊነት የቀረቡለትን እጭዎች ተቀብሎ አጽድቋል።

በዚሁ መሰረት፡-
1, አቶ ክብሩ ፈቀደ የጉራጌ ዞን ዋና የመንግስት ተጠሪ
2, አቶ አበራ ወንድሙ የዞኑ ም/አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ
3, አቶ አለማየሁ ገ/መስቀል የዞኑ ረዳት የመንግስት ተጠሪ
4, ወ/ሮ አመተሩፍ ሁሴን የዞኑ ረዳት የመንግስት ተጠሪ
5, አቶ መብራቴ ወ/ማርያም የዞኑ ትምህርት መምሪያ ኃላፊ
6, ወ/ሮ ነጅሚያ ማህሙድ የዞኑ ሴቶችና ህጻናት መምሪያ ኃላፊ
7, አቶ የህያ ሱልጣን የዞኑ ሰላምና ጸጥታ መምሪያ ኃላፊ
8, ወ/ሮ ትብለጥ እስጢፋኖስ የዞኑ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት መምሪያ ኃላፊ
9, አቶ አየለ ፈቀደ የዞኑ ጤና መምሪያ ኃላፊ
10, አቶ መስፍን ስርገማ የዞኑ ቴክኒክና ሙያ ት/ት ስልጠና መምሪያ ኃላፊ
11,አቶ አየለ ፈቀደ የዞኑ ውሃ ማዕድንና ኤነርጂ መምሪያ ኃላፊ
12, አቶ ሙራድ ያሲን የዞኑ ስራ ዕድል ፈጠራ ኢንዱስትሪ ልማት መምሪያ ኃላፊ
13, አቶ ፈይሰል ሀሰን የዞኑ ወጣቶችና ስፓርት መምሪያ ኃላፊ
14, አቶ ሀዲሙ ሀሰን የዞኑ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ
15, አቶ ናስር ሀሰን የዞኑ ኢንቨስትመንት መምሪያ ኃላፊ እንዲሁም

የወልቂጤከተማፍርድቤትፕሬዚዳንት

1, አቶ ታጠቅ ሀ/ማርያም አድርጎ የሾመ ሲሆን የተጎደሉ የቋሚ ኮሚቴ አባላት እጭዎች ተቀብሎ አጽድቋል።
መረጃውን ያጠናከረው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *