በመስቃንና ማረቆ ወረዳ የነበረው ግጭት በመፍታት እርቀ ሰላም ለመፈጸም የሀገር ሽማግሌዎች ከፍተኛ ሚና መጫወታቸው የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ እርስቱ ይርዳው ገለጹ።

የመስቃን እና ማረቆ ወንድማማች ህዝቦች የሰላም ኮንፈረንስ በኢንሴኖ ከተማ ተካሒዷል:

የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ እርስቱ ይርዳው የበደል ምዕራፍ በይቅርታና በእርቅ እንዲዘጋ ከፍተኛ ሚና ለተጫወቱ ሁሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ባለፉት ሶስት አመታት በመስቃንና ማረቆ ወረዳ የነበረው ግጭት በመፍታት እርቀ ሰላም ለመፈጸም ከጸጥታ ኃይሎችና በየደረጃው ከሚገኙ አመራሮች በተጨማሪ የሀገር ሽማግሌዎች ከፍተኛ ሚና መጫወታቸው ክቡር አቶ እርስቱ ይርዳው ገልጸዋል።

የመስቃንና ማረቆ የህብረተሰብ ክፍሎች በኃይማኖት፣ በጋብቻ እና በሌሎች ማህበራዊ ጉዳዮች የተሳሰሩ ቢሆኑም ለዚህ ግጭት ያበቃቸው በወቅቱ የነበረው ስርዓት ውጤት እንደሆነ አስረድተዋል።

በደቡብ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመልካም አስተዳደር ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አለማየሁ ባውዲ እንደገለጹት በሁለት ወንድማማች ህዝቦች መካከል ሰላም እንዲሰፍን የተደረገው ጥረት ውጤታማ ነው።

የተፈጠረውን የጸጥታ ችግር ለመፍታት ለ29 ጊዜ በሀገር ሽማግሌዎች አማካኝነት እርቅ ለመፍጠር ቢሞከርም ሳይሳካ የቀረው የግል ፍላጎት ያላቸው ሰዎች ጥቅማቸውን ለማስከበር በቀጠናው ሰላም እንዳይሰፍን ጥረት ሲያደርጉ የነበሩ አካላት በመኖራቸው እንደነበር ጠቁመዋል።

የህዝቡ ፍላጎት ሰላምና ልማት መሆኑንና የመስቃን እና የማረቆ ህዝብ በጋብቻ የተሳሰረ ለረጅም ጊዜ ባላቸው የጋራ ባህል እና እሴት አንድ የሆኑ ህዝቦች ናቸው ብለዋል።
በመሆኑም በአካባቢው ወግና ባህል መሰረት የሀገር ሽማግሌዎች ችግሩ በእርቅ እንዲፈታ በማድረጋቸው አቶ አለማየሁ ምስጋና አቅርበዋል።

በሁለቱም ወገን የነበሩ ተፈናቃዮችን ሙሉ ለሙሉ ወደ አካባቢያቸው መመለስ እንደተቻለም ጠቁመዋል።

የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሐመድ ጀማል እንደገለጹት የመስቃን እና የማረቆ ህዝቦች የሰላም እጦት ተቀርፎ በማየታቸው መደሰታቸውን ጠቁመዋል።

በመስቃንና በማረቆ ህዝቦች መካከል በተፈጠረው የሰላም ማጣት ችግር ምክንያት በህዝቡ ላይ ብዙ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ቀውሶች ተፈጥረውበታል፡፡

ከዚህም የተነሳ በርካታ ዜጎች ላለፉት ሶስት አመታት ላልተገባ እንግልት እና ስቃይ ተዳርገው ቆይተዋል ብለዋ።
ዛሬ ግን እነዚህ ወገኖቻችን ወደ ቄያቸው የመመለስ ስራ የተሰራ ቢሆንም አሁንም ያልተሟላላቸው በሕይወታቸውና በእለት ተዕለት ኑሮአቸው ብዙ የጎደሏቸው ነገሮች አሉ ብለዋል፡፡

በመሆኑም በግጭቱ ምክንያት ተፈናቅለው ቤት ንብረታቸው የወደመባቸውን ዜጎች መልሶ ለማቋቋም የሚያስችል ሃብት ሁሉም አቅሙ የቻለውን ገንዘብ ያለው በገንዘቡ፣ ጉልበት ያለው በጉልበቱ፣ ሙያ ያለው በሙያው፣ ለቤት መስሪያ ቁሳቁስ ያለውም እነዚህን ቁሳቁሶች በመለገስ ከዚህ ቀደም ለመከላከያ ሰራዊታችን ድጋፍ እናደርግ የነበረውን ልምድ ተጠቅመን በአጭር ጊዜ ውስጥ አነዚህ ዜጎች በቋሚነት ለማቋቋም የማድረግ ማህበራዊ ኃላፊነታችንን ሁላችንም እንድንወጣ ጥሪዬን አቀርባለሁ ብለዋል፡፡

አያይዘውም አቶ መሀመድ ብዙ ዋጋ የተከፈለበትን ሰላማችን ለማስጠበቅ አብሮነታችንን ሊነጥሉ ከሚፈልጉ ኃይሎች ሴራ መራቅ ይጠበቅብናል ብለዋል።

አሁን የተገኘው ሰላም ፣አንድነት፣መፈቃቀር እና መተሳሰብ ዘላቂ እንዲሆን ወጣቶች፣ሴቶች፣የሀገር ሽማግሌዎች፣የሀይማኖት አባቶች እና በየደረጃው ያሉ የመንግስት ተቋማት ተቀናጅተው ሲሰሩ እንደሆነም አስረድተዋል።

የምስራቅ መስቃን ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አህመዲን ደድገባ እና የማረቆ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ንጉሴ መኪ የሁለት ወንድማማቾች እርቅ መፈጸሙ አስደሳችና ስንናፍቀው የነበረ ነው ብለዋል።

የግል ጥቅመኛ አመራር በፈጠረው ችግሩ ህዝብ እንዲበደል አድርጎታል ያሉት አስተዳዳሪዎቹ አመራሩ የለኮሰው አሳት ወላፈኑ ሌላው አመራር ጭምር ተርፎታል ብለዋል።
በቀጣይ በግጭቱ የተጎዱ የወረዳዎቻቸው ነዋሪዎች ለመካስ እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
በመጨረሻም ለሀገር ከሽማግሌዎችና ሌሎች ለእርቁ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የጸጥታ መዋቅሮች እውቅና ተሰጥቷቸዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡

Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *