በመሰረታዊ ውትድርና ያሠለጠናቸው ከ8መቶ በላይ የህዝባዊ የሰራዊት አባላት በዛሬው እለት ማስመረቁን የእዣ ወረዳ አስተዳደር ገለፀ።

ተመራቂዎች የአካባቢያቸውን ሰላም ከመጠበቅ ባሻገር ሀገራችን የጀመረችውን የህልውና ዘመቻ በድል እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን መስዋአትነት ለመክፈል መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።

የእዣ ወረዳ ዋና አሰተዳዳሪ በምረቃ ስነ ስርዓቱ ወቅት እንደገለጹት ተመራቂ ህዝባዊ ሰራዊት አባላት በንድፈ ሀሳብና በተግባር የወሰዷቸውን ስልጠናዎች ተግባራዊ በማድረግ የአሸባሪው የህወሃት ቡድንና ተላላኪ የሆኑ ሰርጎ ገቦች በመከታተል የአካባቢያቸው ሰላም በንቃት በመጠበቅ እንዲሁም በወረዳው የሚገኙ የዘማች ቤተሰብ አስመራን በማሰባሰብና ቤተሰቦቻቸው በመንከባከብ ግንባር ቀደም ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል።

የወረዳው ማህበረሰብ ሀገራችን ተገዳ የገባችበት የህልውና ዘመቻ በድል እንዲጠናቀቅ አካባቢውን በመጠብቅ፣ወደ ግንባር በመዝመትና ሀብት በማሰባሰብ ጀግናው የመከላከያ ሰራዊት ደጀን መሆኑን በተግባር እያረጋጠ ነው ያሉት ዋና አስተዳዳሪው እስካሁን በጥሬ ገንዘብና በአይነት በአጠቃላይ ከ3 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ መደረጉን ገለፀዋል ።

የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ወደ ግንባር መዝመት በወረዳው ማህበረሰብ ዘንድ ከፍተኛ መነሳሳት የፈጠረ ሲሆን ከዚህ ቀደም በመደበኛ የመከላከያ ምልመላ ግንባር ከተሸኙ 47 ወጣቶች በተጨማሪ አሁን ላይ ሶስት የወረዳ አመራር ፥ አራት የጤና በለሞያዎችና ከ70 በላይ ተመላሽ የቀድሞ ሰራዊ አባለት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በወቅታዊ ጉዳይ በየደረጃው ከሁሉም የማህበረሰብ ክፍል ጋር የተደረጉ ውይይቶች ውጤታማ እንደነበሩ ገልፀው በአስተሳሰብ ጀምሮ ሁሉም የወረዳው ማህበረሰብ በሀገር ጉዳይ ሰራዊት መሆኑን በተግባር እያረጋገጠ ነው ብለዋል።

የወረዳው ሰላምና ጸጥታ ጽህፈት ኃላፊ አቶ ሰለሞን ሃብቴ በበኩላቸው በወረዳው መሰረታዊ የውትድርና ስልጠናቸውን ያጠናቀቁ 841 ህዝባዊ የሰራዊት አባላት የተመረቁ ሲሆን ሰራዊቱ በቆይታቸው በአንድ ሻለቃ፣በ7 ሻምበል ፣በ29 የመቶና በ87 የጓድ አደረጃጀት ተደራጅተው ስልጠናውን ተከታትለዋል ብለዋል።

የነበራቸው ተነሳሽነት አበረታች የነበረና በዚህም መሰረታዊ እውቀት እንዲኖራቸው አስችሏቸዋል ብለዋል።

የእናት ጡት ነካሽ አሸባሪው የህወሓት ቡድን ኢትዮጲያን ለማፈራረስ ሲኦልም ቢሆን እወርዳለሁ ያለውን ጭራቅ ወደ ተመኘው ሲኦል ለመሸኘት በመጨረሻው ምዕራፍ ላይ በመሆኑ ምርቃቱ ታሪካዊ ነው ብለዋል።

ተመራቂ ህዝባዊ ሰራዊት የወሰዱትን የንድፈ ሀሳብና የተግባር ሰልጠና ተግባራዊ በማድረግ እንዲሁም መላው ህብረተሰቡን በማሳተፍና ከወረዳው የፀጥታ አካላት ጋር ተቀናጅተው በተደራጀ መልኩ በመስራት የአካባቢያቸውን ሰላም ለማስጠበቅ በትኩረት መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል ።

በምርቃቱ ላይ የተገኙት የጉራጌ ዞን ትራንስፖርትና የመንገድ ልማት መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ትብለጥ እስጢፋኖስ እንደገለፁት ሠልጣኞች ለተከታይ ቀናት በወሰዱት ስልጠና አካባቢያቸውን በመጠበቅ ፣የእዣ ወረዳ ህዝብ ሠላም በመጠበቅ በአጠቃላይ ለኢትዮጵያ ተገን በመሆን ከጁንታው ጥፋት ለመታደግ ከሚመለከታቸው አካላት ተቀናጅተው መስራት እንደሚጠበቅባቸው ገልፀዋል ።

ጦርነት ግንባር ላይ ብቻ አይደለም ያሉት ኃላፊዋ ህብረተሰቡ አካባቢውን ነቅቶ በመጠበቅ ፣የዘማች ቤተሠቦችን በመንከባከብ ፣ለሰራዊቱ ሀብት በማሰባሰብ፣የደረሱ ሰብሎችን በመሰብስብና በሌሎች የልማት ስራዎች ግንባር ቀደም ሚናውን በመወጣት ለሰራዊቱ ደጀንነታቸውን ማሳየት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

ከአሰልጣኞች መካከል አምሳለቃ ደንድር በርታ በስልጠናው መሣሪያ መፍታትና መግጠም ፥አተኳኳስ ፥የአካል ብቃትና ሌሎች የንድፈ ሀሳብና የተግባር ስልጠናዎች መሠጠቱን ገለፀዋል።

ጠላትን መመከት የሚያስችል አቅም መፍጠር የሚያስችል ስለጠና መሠጠቱን በማረጋገጥ።

ካነጋገርናቸው ሰልጣኞች መካከል ወ/ሮ እልፍነሽ ስራኒና አስር አለቃ ወጋየሁ አለሜ የአካባቢያቸው ሰላምና ደህንነት ከመጠበቅ በተጨማሪ ለዘማች ቤተሰብ በጉልበት፣ በገንዘብና በተለያዩ ድጋፎች በማድረግ አጋርነታቸው ለማሳየት እንደሚሰሩም ተናግረዋል።

አስፈላጊ ሲሆን ወደ ግንባር በመዝመት አስፈላጊውን መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው ።

  • አካባቢህን ጠብቅ!
  • ወደ ግንባር ዝመት!
  • መከላከያን ደግፍ!
    በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
    Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
    Website:- https://gurage.gov.et
    Telegram:- https://t.me/comminuca
    Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *