በመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ዘርፍ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማረጋገጥ ሁሉም በዘርፉ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ የጉራጌ ዞን ግብርና መምሪያ ገለጸ።

በጉራጌ ዞን ግብርና መምሪያ የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ጽህፈት ቤት የ2016 በጀት አመት የ7 ወራት እቅድ አፈጻጸም ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በወልቂጤ ከተማ አካሂዷል።

የጉራጌ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አበራ ወንድሙ በመድረኩ ተገኝተው እንዳሉት በመሬት ዘርፍ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ዘርፍ በትኩረት መስራት ይገባል።

በዞኑ ሊለሙ የሚችሉ የወልና የአርሶ አደር መሬቶችን በባህርዛፍ መሸፈኑን ጠቅሰው በዞኑ በአንዳንድ መዋቅሮች ባህርዛፍ በመንቀል ወደ ሰብልና ፍራፍሬ ለመቀየር የተጀማመሩ ስራዎችን ይበልጥ አስፍቶ በመስራት አርሶ አደሩ ተጠቃሚ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።

ህገወጥ የወል መሬት ወረራ በማስመለስ ወደ መሬት ባንክ ማስገባት ይገባል ያሉት አቶ አበራ ከዚህም ባለፈ አርሶ አደሩ የብድር ተጠቃሚ እንዲሆን መስራት እንደሚገባም አመላክተዋል።

ዞኑ በዘርፉ ተጠቃሚ እንዲሆን የመሬት ዘርፉ ለማዘመን የተጀማመሩ ስራዎች በትኩረት መሰራት እንዳለበትም አስረድተዋል።

በጉራጌ ዞን ግብርና መምሪያ የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዘመቻ ሳህሌ በበኩላቸው በባህርዛፍ የተያዙ መታረስ ያለባቸው መሬቶችን ለአርሶ አደሩ ግንዛቤ በመፍጠር እንዲታረሱ ማድረግ ይገባል ብለዋል።

ብድር ከማስጠቀም አንጻር ያሉ ውስንነቶችን በቀጣይ ሁሉም ወስዶ ሊሰራበት እንደሚገባ አመላክተዋል።

የመሬት ዘርፉን በማዘመን አርሶ አደሩ ተጠቃሚ ማድረግ ላይ በትኩረት መስራት ይኖርበታል ያሉት ኃላፊው በዚህም ውጤታማ ስራ ለመስራት ቅንጅታዊ አሰራር በማጠናከር መስራት እንዳለበትም አንስተዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች እንዳሉት በ7 ወራት በተሻለ የተከናወኑ ተግባራት በማጠናከርና ያልተከናወኑ ተግባራት በቀጣይ ወስደው እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

ህገወጥ የወል መሬት ወረራ እና የባህር ዛፍ ተከላ ለመከላከል የተጀማመሩ ስራዎችን መኖራቸውን ገልጸው በዚህም ዘርፉ ውጤታማ እንዲሆኑ ባለድርሻ አካላት እገዛ ሊያደርጉ እንደሚገባ ገልጸዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36CxQ
Tiwter https://4pvf.short.gy/bTJNNn

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *