በሕዝብ ተሳትፎ የሚሰሩ የመንገድ ልማት ስራዎች በመንግስት ለሚሰሩ የመንገድ ልማት ስራዎች ከፍተኛ ድጋፍ እንደሚያደርጉ የቀቤና ወረዳ መንገድ ትራንስፖርት ፅ/ቤት አስታወቀ።

በወረዳው በ2014 ዓ.ም በሕዝብ ተሳትፎ ብቻ 30 ኪ.ሜ የሚሸፍን የቀበሌ ውስጥ ለውስጥ መንገድ መሰራቱንና ለዚህም ከህዝቡ 10 ሚሊየን ብር ያህል ተሰብስቦ ሥራ ላይ ውሏል ያሉት የቀቤና ወረዳ የመንገድ ትራንስፖርት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ሙባረክ ዘይኑ ናቸው ።

ሀላፊው አያይዘውም ከወልቂጤ ኢንጌ ዋና መንገድ 10 ኪ.ሜ በመንግስት ደረጃ ማሻሻያና የተጎዱ ቦታዎችን የመጠገን ስራ እየተሰራ ሲሆን በዛሬው እለትም በቃዋ ቀበሌ በሚሰራው የመንገድ ደህንነትና የአከባቢ ጥበቃ ስራ ላይ የወረዳ አመራሮችና የአከባቢው ህብረተሰብ ተሳትፎ በማድረግ እያገዙ ይገኛሉም ብለዋል።

ሀላፊው አክለውም በህብረተሰብ ተሳትፎ መንገድ ከተሰራባቸው ቀበሌዎች መካከል ፍቃዶ፣ሱንካ፣ጣጤሳ ወሸርቤ፣ ደገንሺ-ሞላና ሩሙጋ በዋናነት የሚጠቀሱ ሲሆን በፍቃዶ ቀበሌ አዳዲስ መንገድ ከፈታዎች ከማከናወንም በተጨማሪ በጀብዱ ቀበሌ በሕዝቡ ተሳትፎ የመሸጋገሪያ ዲልዲይ እየተሰራ መሆኑንም ገልፀዋል ።

በተያያዘም ዛሬ በቃዋ ቀበሌ በህብረተሰብ ተሳተፎ እየተሰራ የሚገኘው የመንገድ ልማት ስራ 200 ሜትር እንደሚሸፍን የገለፁት ደግሞ የቀቤና ወረዳ መንገድ ትራንስፖርት ፅ/ቤት የገጠር መንገድ ዘርፍ ሀላፊ አቶ ማፉዝ ቴኒ ናቸው ።

በህብረተሰብ ተሳትፎ የሚሰሩ የመንገድ ልማት ስራዎች የመንግስትን ጫና ከማቃለል በተጨማሪ ህብረተሰቡ ያለበትን የመንገድ ልማት ችግር በራሱ በመፍታት የመንግስትን ጫና በመቀነሱ ረገድ የወረዳው ህዝብ እየተወጣ ያለውን ድርሻ ያሳያል ሲል የዘገበው የቀቤና ወረዳ የመንገድ ትራንስፖርት ፅ/ቤት ነው ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *