በላይነት በማረጋገጥ የተጀመሩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ሰራዎች ማስቀጠል እንደሚገባ የጉራጌ ዞን ምክር ቤት አስታወቀ።

የጉራጌ ዞን ምክር ቤት የ10 ወረዳዎችና 5 የከተማ ምክር ቤቶች የ4ኛ ዙር 10ኛ አመት 22ኛ የአፈ-ጉባኤዎች የጋራ ምክክር መድረክ በወልቂጤ ከተማ ተካሄዷል።
የጉራጌ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ልክነሽ ሰርገማ እንዳሉት ምክር ቤቶች በዞኑ የዉስጥ ጉዳይ ከፍተኛ የፖለቲካ ስልጣን ባለቤትና ህግ አዉጪ አካል ሲሆን የህብረተሰቡ ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ እድገት ለማፋጠን ፋይዳ ያላቸዉ ህጎች በማዉጣት ፣ አፈጻጸማቸዉን በመከታተልና በመቆጣጠር ትልቅ ኃላፊነት ያላቸው አካል ነዉ።

አስፈጻሚና የዳኝነት አካላት በነቃ የህዝብ ተሳትፎ በማዋቀርና በማደራጀት የዜጎች መብቶችና ነጻነቶች ማስከበር እንዲሁም መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ተቋሙ የተለያዩ አደረጃጀቶች ፈጥሮ እየሰራ እንደሆነም አመላክተዋል።

በየደረጃዉ የሚገኙ ምክር ቤቶችን ድጋፍና ክትትል በማድረግ የአሰራር ክፍተቶችን በመለየት ሙያዊ ድጋፍ በማድረግ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች በመስጠት ፣ምርጥ ተሞክሮዎችን በመለየትና በመቀመር ወደ ሌሎች አካባቢዎች እንዲሰፋ በትኩረት እየተሰራ እንደሆነም አመላክተዋል።

የህግ የበላይነት በማረጋገጥ የተጀመሩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ሰራዎች ማስቀጠል ይገባል ያሉት ዋና አፈ ጉባኤዋ የምክር ቤቶች የክትትልና የቁጥጥር ስራዎችን ማጠናከርና የህዝብ መድረኮችን በመፍጠር ከህዝቡ የሚነሱ ችግሮች ለአስፈጻሚዉ በማቅረብ በወቅቱ እንዲፈቱ ከመቼዉም ጊዜ በላይ አጽዕኖት ተሰጥቶ ሊሰራበት እንደሚገባም አብራርተዋል።

ቋሚ ኮሚቴዎች ህዝቡ የጣለባቸዉን ሃላፊነት በተገቢዉ በመወጣት የህዝባቸዉን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ መቻል እንዳለባቸዉም አመላክተዋል።

በመድረኩ የተገኙት የጉራጌ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ክብሩ ፈቀደ በበኩላቸዉ ሶስቱም የመንግስት አካላት የመጨረሻ ግብ በየደረጃዉ ህዝቡ የሚያነሳዉ የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች እንዲቀረፉ ማድረግ ነዉ።

የዲሞክራሲ ስርዓት በህዝባችን ተሳታፊነት ብሎም በዉሳኔ ሰጪነት ሂደት ላይ ሚናቸዉ እንዲወጡ በትኩረት መስራት ይገባል ብለዋል።

በምክር ቤቶች የሚሰሩ ስራዎች ክብደትና ትርጉም ተሰጥቷቸዉ የነበሩ ጉድለቶች ማረም ይገባል ያሉት አቶ ክብሩ የሚሰሩ ስራዎች ህዝቡ እንዲያዉቃቸዉ ማድረግና መተቸት እንዳለበትም አብራርተዋል።

በመድረኩ የተገኙ አንዳንድ የምክር ቤት አባላቶች በሰጡት አሰተያየት የፎረም እቅዱ የሚያሰራና የቀበሌ ምክር ቤቶች የሚያጠናክርም እንደሆነም አመላክተዋል።

በአፈጻጸም ፊት ለወጡ የዞን ትምህርት መምሪያ፣ ገቢዎች መምሪያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፣ በወረዳ ምክር ቤቶች ደረጃ የቸሃ ወረዳ ምክር ቤት ፣ የጉመር ወረዳና የእኖር ወረዳ ምክር ቤቶች እንዲሁም በቸሃ ወረዳ ሰፊየና ቋሸ ቀበሌ ፣በጉመር ወረዳ አዶም ቀበሌና ጌታ ወረዳ አጋታ ቀበሌዎች የእዉቀና፣ የሰርተፍኬት እንዲሁም የዋንጫ ሽልማት የተበረከተላቸዉ ሲሆን በተቋማቸዉ ጡረታ ለወጡ ለአቶ ወሰን አህመድ የጋቢና የሰርተፍኬት እንዲሁም ለጥበቃዉ ሰራተኛ ለአቶ ጥበቡ ሀይለክርስቶስ የገንዘብና የሰርተፍኬት ሽልማት ተብርክቶላቸዋል።

በመጨረሻም የፎረም ዕቅድ፣በተሻሻለዉ የፎረም መተዳደሪያ ደንብ ፣ የዝቅተኛ መመዘኛ መስፈርቶችና የድጋፍና ክትትል ሪፖርት ቀርቦ ዉይይት ተደርጎባቸዋል ሲል የዘገበዉ የጉራጌ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ነዉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *