በሀገር ደረጃ ተተኪ አትሌቶችን ለማፍራት በሚደረገው ጥረት በጉራጌ ዞን እየተደረገ ያለው ተሳትፎ እጅግ የሚበረታታ ነው ሲሉ ኮማንደር አትሌት ጌጤ ዋሚ ተናገሩ።

የኬሮድ ስፖርትና ልማት ማህበር ያዘጋጀው የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ሩጫ በቡታጅራ ከተማ በድምቀት ተካሄዷል።

የኢትዩጽያ አንጋፋ አትሌቶች ማህበር ፕሬዝዳንት ኮማንደር አትሌት ጌጤ ዋሚ ስፖርት ለአንድ ሀገር ኢኮኖሚያዊ ፣ፖለቲካዊና ማህበራዊ እድገት እንዲሁም ሰላምና የእርስ በርስ ትስስር ለማጠናከር እጅግ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል።

በመሆኑም ዘርፉን ለማጠናከር የመንግስትና የግል ተቋሟት፣ባለሀብቶች፣ተራዶ ድርጅቶች፣ባንኮችና ሌሎችም የሚመለከታቸው አካላት የሚያደርጉት ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳስበዋል።

የጉራጌ ዞን ህዝብና መንግስት እንዲሁም የኬሮድ ስፖርትና ልማት ማህበር ተተኪ አትሌቶችን ለማፍራት የሚያደርጉት ጥረት የሚበረታታ ነው ብለዋል ኮማንደር አትሌት ጌጤ ዋሚ።

የኬሮድ የስፖርትና ልማት ማህበር ፕሬዝዳንት አሰልጣኝ ተሰማ አብሽሮ እንደገለጹት በዛሬው እለት የተካሄደው የጎዳና ላይ ሩጫ የጉራጌ ዞን በስፖርት ያለው ታሪክ ለማስቀጠልና ተተኪ አትሌቶች በማፍራት እስከ ፌደራል እንዲደርሱ ያግዛል።

ኬሮድ ስሙም ሰላም የሚሰብክ እንደመሆኑ ዛሬ የተካሄደው የጎዳና ሩጫ ለህብረተሰቡ ሰላምን ለመስበክ ዋና አላማ ያደረገ መሆኑ ተናግረዋል።

የጎዳና ላይ ሩጫው ቀጣይ የነበሩ ክፍተቶችን በማረም ለተሻለ ለውጥና ልማት፣የዞኑ መልካም ገጽታን ለማስተዋወቅ እንዲሁም አለምና ሀገር አቀፍ እንዲሆን ለማድረግ እንደሚሰራም አስታውቀዋል።

ዛሬ በቡታጅራ ከተማ ሲካሄድ የነበረው የ10 ኪሎ ሜትር ውድድር ከ1ኛ እስከ 6ኛ ደረጃ የወጡ ወንድና ሴት አትሌቶች የብር፣የሜዳለያና የነሀስ ተሸላሚ ሆነዋል።በዚህም መሰረት፡-

ከወንዶች

1ኛ ሀልፎም ተስፋዬ
2ኛ ጭምዴሳ ደበሌ
3ኛ ተሰማ መኮንን
4ኛ ምትኩ አያሌ
5ኛ አብራራው ምስጋናው
6ኛ ሀብታሙ ብርሌ ሲሆኑ

ከሴቶች ደግሞ

1ኛ የኔነሽ ሽመክት
2ኛ እናትነሽ አላምረው
3ኛ ዘውዲቱ አደረው
4ኛጥሩዬ መስፍን
5ኛ ሰናይትጌታቸው
6ኛ አለምነሽ ዋለ እንደየ ደረጃቸው ከ30ሺ እስከ 5ሺህ ብር ተሸላሚ ሆነዋል።

በመጨረሻም ሩጫ እንዲሳካ አስተዋጾ ላደረጉ የአትሌቲክስ ክለቦች፣የማህበረሰብ ክፍሎች፣ተራዶ ድርጅቶች፣የግልና የመንግስት ተቋማት እንደየ ደረጃቸው የተለያዩ ሽልማቶችና የእውቅናና የምስጋና ሰርተፊኬት ተበርክቶላቸዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

በመረጃ ምንጭነት ገፃችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!
= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36CxQ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *