በሀገሪቱ እየተስተዋለ ያለውን የዋጋ ንረትና የኑሮ ውድነት ለማረጋጋትና ጥራት ያለው ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ ለማህበረሰቡ ለማቅርብ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑ የጉራጌ ዞን ህብረት ስራ ልማት ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

በዞኑ ሰባተኛው አንድነት የጉራጌ ዞን ሁለገብ የሸማቾች ህብረት ስራ ዩኒየን የምስረታ ጉባኤ በወልቂጤ ከተማ ተካሄደ ።

ዩኒየኑ ስራውን ለመጀመር መነሻ ካፒታል ከአባላቶቹ ከዕጣና ከመመዝገቢያ 6 መቶ 4 ሺህ 5 መቶ ብር እንደሆነና በቀጣይ 13 ሚሊዮን 2 መቶ 62 ሺህ ብር ለማፈላለግ አቅዶ እየሰራ ነዉ።

የጉራጌ ዞን ህብረት ስራ ልማት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጌታሁን ነጋሽ በሰባተኛው ዩኒየን ምስረታው ጉባኤ ላይ ተገኝተዉ እንዳሉት ሁለገብ የሸማቾች ህብረት ስራ ዩኒየን በማቋቋም ለህብረተሰቡ ጥራት ያለው ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያቀርቡ በማድረግ በተለይ መሰረታዊ የፍጆታ እቃዎችን አቅርቦትና ፍላጎት ለማጣጣም የላቀ አስተዋጽኦ እንደሚኖረውም አስታዉቀዋል።

ከወረዳና ከከተማ አስተዳደር የተውጣጡ የሸማቾች መሰረታዊ ህብረት ስራ ማህበራት ተሰባስበው የመሰረቱት ትልቅ አላማ ያለው አንድነት ሁለገብ የሸማቾች ህብረት ስራ ዩኒየን ከመንግስት ጋር በመሆን በየጊዜው የሚስተዋለውን የዋጋ ንረትና የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ እንደሚረዳም ተናግረዋል።

አንድነት ሁለገብ የሸማቾች ዩኒየኑ ከመመስረቱ ባሻገር ወደ ተግባር እንዲገባ በተለይ አባላቱና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ትልቅ ጥርት በማድረግና ተቀናጅተዉ መስራት እንዳለባቸዉም አስረድተዋል።

የዞኑ ህብረት ስራ ልማት ጽህፈት ቤት የህብረት ስራ ማህበራት ማደራጀትና ማስፋፋት ቡድን መሪ አቶ ሀይለኛው ጌታቸው እንደተናገሩት በዞኑ ሰባተኛው አንድነት የሚባል ስያሜ የተሰጠው የጉራጌ ዞን ሁለገብ የሸማቾች ህብርት ስራ ዩኒየን ስራውን ለመጀመር መነሻ ካፒታል ከአባላቶቹ ከዕጣና ከመመዝገቢያ 6 መቶ 4 ሺህ 5 መቶ ብር እንደሆነም ገልጸዋል።

አቶ ሀይለኛው ጌታቸው አክለውም ዩኒየኑ የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት ከተለያዩ የመንግስት ተቋማት 13 ሚሊየን 2 መቶ 62 ሺህ ብር በተዘዋዋሪ ፈንድ ለማፈላለግ እቅድ መያዙንና የፋብሪካና ሸማቹ የሚፈልጋቸውን እቃዎች እንደሚያቀርቡም ጠቅሰዋል።

በምስረታ ጉባኤዉ ላይ የተገኙ አንዳንድ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት ዩኒየኑ ወቅታዊና ሀገራዊ ነባራዊ ሁኔታን ያገናዘበ ስራ ለመስራት እንደሚያግዝ ገልፀው፤ ከመንግስት ጋር በመሆን በቅንጅት በመስራት ዉጤታማ ስራ ለመስራት መዘጋጀታቸዉም አብራርተዋል።

በአንድነት ሁለገብ የሸማቾች ህብረት ስራ ዩኒየን የምስረታ ጉባኤ ላይ የጉራጌ ዞን ህብረት ስራ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌታሁን ነጋሽ ጨምሮ የዞንና ከተማ ከፍተኛ አመራሮች፣የጉራጌ ዞን ህብረት ስራ ልማት ጽ/ቤት የማኔጅመንት አባላት፣ የወረዳና ከተማ አስተዳደር የሸማቾች ህብርት ስራ ዩኒየን አመራሮችና ሌሎችም የሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካላቶች ተሳትፈዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

=ኢትዮጵያን እናልማ፣የፈረሰውን እንገንባ፣ለፈተና እንዘጋጅ!

በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:-
https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *