ቋማት የሚመደበውን ውስን ሀብት ከሙስናና ብልሹ አሰራር በጸዳ መልኩ ለታለመለት አላማ እንዲውል እየተሰራ መሆኑን የጉራጌ ዞን ጤና መምሪያ አስታወቀ፡፡

የጉራጌ ዞን የጤና መምሪያ የስነ-ምግባር መከታተያ ክፍል የ2016 የግማሽ አመት አፈጻጸም ላይ ትኩረት ያደረገ የውይይት መድረክ በወልቂጤ ከተማ አካሂዷል፡፡

የጉራጌ ዞን ጤና መምሪያ ተወካይ አቶ ሳህሌ ክብሩ በመድረኩ ላይ እንዳሉት የጤናው ሴክተር በስነ-ምግባር የታነጸና ብልሹ አሰራሮችን የሚጸየፍ ባለሙያና አመራር የሚፈልግ ነው፡፡

በጤና ተቋማት የሚስተዋለውን የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች የባለሙያ ስነ-ምግባር ጉድለት፣ የመድሃኒትና የግብዓት እጥረት እንዲሁም ለአገልግሎት ምቹ ያልሆኑ ተቋማት መሆናቸውን ገልጸው የችግሮቹ መንስኤ የተቀመጡ የአሰራር ስርዓቶች በአግባቡ ባለመተግበራቸው ነው፡፡

አክለውም ብልሹ ስነ-ምግባር ለማስተካከልና በየደረጃው የጠቀመጡ የአሰራር ስርዓቶች ሳይሸራረፉ ተግባረዊ ለማድረገ የስነ-ምግባር ኦፊሰሮች የሚያደርጉት አስተዋጽኦ ከፍተኛ እንደሆነ አቶ ሳህሌ ገልጸዋል፡፡

የጉራጌ ዞን ጤና መምሪያ የስነ-ምግባር መከታተያ ክፍል ተወካይ አቶ አበበ አሰፋ በበኩላቸው ለጤና ተቋማት የሚመደበውን ውስን ሀብት ከሙስናና ብልሹ አሰራር በጸዳ መልኩ ለታለመለት አላማ እንዲውል የስነ-ምግባር ኦፊሰሮች ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅተው ሊሰሩ ይገባል ብለዋል፡፡

የጤና ባለሙያዎች የስነ-ምግባር ችግሮች፣ የመድሃኒት ግዥ፣ የወጪና ገቢ አጠቃቀም፣ ጊዜ ያለፈባቸው መድሃኒቶች አወጋገድ፣ የውስጥ ገቢ አሰባሰብና አጠቃቀም፣ በየሱቁ በመሸጠት ላይ የሚገኙ በምግብ እጥረት ለተጎዱ ህጻናት ተብሎ በእርዳታ የመጣ ፕላፕሌት የሚስተዋሉ የአሰራር ዝንፈቶች ለማረም በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

በቀጣይ የዞኑ ጤና መምሪያ በስሩ ለሚገኙ የስነ-ምግባር ኦፊሰሮች ክትትልና ድጋፍ የማድረግ ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አቶ አበበ ጠቁመዋል፡፡

የውይይቱ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት ለጤና ተቋማት የሚመደው በጀት ለታለመለት አላማ እየዋለ ስለመሆኑ ለመከታተልና ብልሹ አሰራር ካለም ለማረም የአሰራር ግልጸኝነት ሊኖር ይገባል ብለዋል፡፡

የስነ-ምግባር ኦፊሰሮች የሚሰሩት ስራ ሚስጥራዊ ስለሆነ ቢሮና የመስሪያ ቁሳቁሶች ለብቻው እንዲኖረው ትኩረት ተሰጥቶት ሊሰራ እንደሚገባ ተናግረዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *