ቀልጣፋና ደበኛ ተኮር የአገልግሎት አሰጣጥ ተከትሎ በመስራቱ በተጠናቀቀው በበጀት ዓመት ከ19 ዲስትሪክቶች መካከል 1ኛ በመውጣት የዋንጫ ተሸላሚ መሆኑን ኦሞ ባንክ የወልቂጤ ዲስትሪክ አስታወቀ፡፡

ባንኩ ለህብረተሰቡ የሚሰጠውን አገልግሎት በመጠንና በጥራት ለማሳደግ በትኩረት እንደሚሰራ የኦሞ ባንክ የወልቂጤ ዲስትሪክት ስራ አስኪያጅ አቶ መለሰ ፀጋዬ ገለጹ፡፡

የኦሞ ባንክ የወልቂጤ ዲስትሪክት ስራ አስኪያጅ አቶ መለሰ ፀጋዬ በሰጡት መግለጫ ዲስትሪክቱ ለጉራጌ፣ ለምስራቅ ጉራጌና ለየም ዞኖች እንዲሁም ለማረቆና ለቀቤና ልዩ ወረዳዎች አገልግሎት በመስጠት ላይ እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡

ባንኩ የብሄራዊ ባንክ መስፈርት አሟልቶ ፈቃድ ካገኘበት ሰኔ10/2016 ዓመተ ምህረት ጀምሮ በስሩ በሚገኙ 20 ቅርጫፎች ላይ የሰው ሀይል አደረጃጀት ከማሟላት ጀምሮ የአገልግሎት አሰጣጡ በማዘመን በ13 ቅርጫፎቹ ኦን ላየን አግልግሎት በመስጠት ላይ እንደሚገኝና በተያዘው በጀት ዓመት ቀሪ ሰባት ቅርጫፎች በማካተት በሁሉም ቅርጫፎቹ ኦን ላየን አገልግሎት ለመስጠት በትኩረት እየሰራ መሆኑን ስራ አስኪያጁ አብራርተዋል፡፡

በዚህም ቀልጣፋና ደንበኛ ተኮር የአገልግሎት አሰጣጥ ተከትሎ በመስራቱ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በአራት ክልሎች ከሚገኙ 19 ዲስትሪክቶች ጋር ተወዳድሮ በአጠቃላይ አፈጻጸም 1ኛ በመውጣት የዋንጫ ተሸላሚ መሆን እንደቻለ አቶ መለሰ በመግለጫቸው አመልክተዋል፡፡

በቀጣይ የሀገሪቱ የእድገት ፖሊሲ መሰረት በማድረግ ባንኩ ለህብረተሰቡ የሚሰጠውን አገልግሎት በመጠንና በጥራት ለማሳደግ በትኩረት እንደሚሰራ ስራአስኪያጁ ገልጸዋል፡፡

ኦሞ ባንክ የወልቂጤ ዲስትሪክት የብድርና ቁጠባ ኃላፊና ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ አያልነህ ብርሃኔ በበኩላቸው ባንኩ አንደኛ በመውጣት እውቅና እንዲያኝ ያስቻሉት ምከንያቶች በብሄራዊ ባንክ የተቀመጡ ስታንዳርዶች በተሻለ ደረጃ በመፈጸሙ፣ በርካታ አዲስ ደንበኞች ማፍራት በመቻሉ፣ የተራ ቁጠባ መጠን በማሳደጉ፣ የመክፈል አቅሙ ለባንኩ ከተቀመጠው ሃያ ከመቶ በላይ መሆኑ፣ ከፍተኛ የብድር ስርጭትና የውዝፍ ዕዳ አመላለስ ላይ የተሻለ አፈጻጸም በማሳየቱ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

በአራቱም ክልሎች ከሚገኙ 241 የኦሞ ባንክ ቅርጫፎች በአፈጻጸማቸው ተወዳድረወ የአገና ከተማ 1ኛ፣ አበሽጌ 4ኛ እና የም 5ኛ ደረጃ መውጣት መቻላቸውን የገለጹት አቶ አያልነህ ለዚህ ውጤት መገኘት ከዲስትሪክቱ ጀምሮ ሁሉም የባንኩ ቅርጫፍ ባለሙያዎችና ኃላፊዎች በከፍተኛ ትጋት በቲም መስራት በመቻላቸው ነው፡፡

በቀጣይ የአገልግሎት አሰጣጡ በይበልጥ በማዘመን የህብረተሰቡ ተጠቃሚነት ለማሳደግ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ተቀኛጅቶ እንደሚሰራ ም/ስራአስኪያጁ ተቁመዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *