የካ
የጉራጌ ዞን የልዩ ልዩ ስፖርት ሻምፒዮና ዉድድርና 21ኛዉ የባህል ስፖርታዊ ዉድድሮች በወልቂጤ ከተማ በዛሬ ዕለት ጀመረ።
በዉድድሩ መክፈቻ ፕሮግራም ላይ የተገኙት የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ እንዳሉት ስፖርታዊ ዉድድሮች ሰላምና አብሮነትን በማስፈንና ባህላዊ እሴቶቻችን በማጠናከር ፋይዳዉ የጎላ እንደሆነም ተናግረዋል።
ለስፖርት እድገት ማነቆ የሆኑ የስፖርት አደረጃጀቶች በማዘመን ፣ ማዝወተሪያ ስፍራዎች ለስልጠና እና ለዉድድሮች ምቹ በማድረግ የአሰራር ዘዴዎችን በመፈተሽ አዳዲስ የአሰራር ዘዴዎችን በመተካት በመንግስትና በአመተር የስፖርቱ አገልጋዮች መካከል ያለዉ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር ይገባል ብለዋል።
በዉድድር መድረኮች ከሚገኙ ሜዳሊያና ዋንጫ ባሻገር የእርስ በእርስ ትዉዉቅ በማስተሳሰር ያሉንን ቱባ ባህሎች ወደ ተሻለ መሰረት ላይ ለማድረስ ስፖርቱ ለማህበረሰቡና ለመንግስት ያለዉ ፋይዳ የጎላ ይሆናል ብለዋል።
በዚህ የልዩ ልዩ ዉድድሮች ታዳጊ ስፖርተኞች የሚታዩበት እንዲሁም አሰልጣኞች የስራ ፌሬዎቻቸዉ የሚታይበትና ልምድ የሚወስዱበት እንደሆነም አስረድተዋል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ምክትልና የስፖርት ዘርፍ ሀላፊ አቶ መዘረዲን ሁሴን በእለቱ በእንግድነት ተገኝተዉ እንዳሉት ስፖርት በአንድ ሀገር ጤናማ አምራችና የተሟላ ስብዕና ያለዉ ዜጋ በመፍጠር ያለዉ ሚና በጣም ከፍተኛ ነዉ።
ስፖርታዊ ዉድድሮች ከሰዉ ልጆች ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ግንኙነት የሚያሳልጥበት እንደሆነም አመላክተዉ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከተመሰረተ ጀምሮ በርካታ የስፖርት ልማት ስራዎች ማከናወን ተችሏል ብለዉ በዚህም የጉራጌ ዞን የላቀ ድርሻ እንዳለዉም አመላክተዋል።
የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ሀላፊ አቶ ፈይሰል ሀሰን እንዳሉት ጤናማ ተክለ ሰውነት እና ንቁ አእምሮ ያለው አምራች ዜጋ ለማፍራት እስፖርታዊ እንቅስቃሴ ወሳኝ ሚና እንዳለዉም ገልጸዉ ።
በግል እና በቡድን የሚደረግ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ በተለይም ማስ ስፖርት ተላላፊ ካልሆኑ በሽታዎች እራሳችን ለመከላከል እና ጤናማ ህይወት ለመምራት ወሳኝ ሚና ስላለው በየከተማው የተጀመሩ መሰል እንቅስቃሴዎች አጠናክረን ልናስቀጥላቸው ይገባል ብለዋል።
ስፖርት ፍቅርን፣ አንድነትን፣ አብሮነትን፣ ትብብርን ያሳድጋል ያሉት ሀላፊዉ ከዚህም በተጨማሪ ስፖርታዊ ዉድድሮች ባህልን፣ ቋንቋን፣ ማንነትን በማስተዋወቅ ረገድ ፋይዳቸዉን የጎላ የጎላ መሆኑም ሀላፊዉ ተናግረዋል ።
የወልቂጤ ከተማ ከንቲባ አቶ እንዳለ ስጦታዉ እንዳሉት የስፖርታዊ ዉድድሮች ህዝብ ለህዝብ በማስተሳሰር ረገድ ትልቅ ፋይዳ ያለዉ እንደሆነም ተናግረዋል።
ስፖርት የወጣቶች ስብዕና ከመገንባት በተጨማሪ የማህበረሰቡ የወንድማማችነት እሴት ለማጎልበት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ የሚገኝ እንደሆነም ተናግረዋል።
ዛሬ ዛሬ የጀመረዉ ዞን አቀፍ የልዩ ልዩ ስፖርታዊ ዉድድሮችና 21ኛዉ የባህል ስፖርት የአካባቢዉን ባህል የምናጎላበት ፣ በስፖርታዊ ዉድድሮች አንድነታችንና ፍቅራችንን የምንገልጽበት ምቹ መድረክ እንደሆነም አብራርተዋል።
ስፖርት የሰላም ፣የፍቅር የአንድነት መገለጫ ሲሆን በከተማችን ለ10 ተከታታይ ቀናት የሚካሄደዉ ስፖርታዊ ዉድድሮች በስኬት እንዲጠናቀቅ ከተማ አስተዳደሩ የበኩሉን እንደሚወጣም አስረድተዋል።
በመክፈቻው ስነ ስርዓት የወልቂጤ ከተማና የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ እግር ካስ ቡድኖች ተገናኝተው 1 አቻ በሆነ ውጤት ተለያይተዋል ሲል የዘገበዉ የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነዉ።
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36CxQ
Tiwter https://4pvf.short.gy/bTJNNn