ስራ አጥ ዜጎችን በተለያዩ የስራ ዘርፎች ላይ በማሰማራት የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት በትኩረት መሰራት እንዳለበት ተገለጸ።

በጉራጌ ዞን አስተዳደር የስራ ዕድል ለመፍጠር እና የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ የቀጣይ 5 ወራት ክህሎት መር ልዩ የስራ እቅድ ፈጠራ ላይ ዞን አቀፍ የንቅናቄ መድረክ በወልቂጤ ከተማ አካሂደዋል ።

የጉራጌ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የዞኑ ስራ እድል ፈጠራ ኢንተርፕራይዞች ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙስጠፋ ሀሰን በንቅናቄ መድረኩ ወቅት እንደሉት አሁን ያለውን ነባራዊ ሁኔታ በመረዳት ይህን ልዩ የሆነ የ5 ወር ክህሎት መር ልዩ የስራ እቅድ በትኩረት በመሰራት የስራ እድል መፍጠር ይገባል ብለዋል።

አሁን ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ በመጠቀም በመኖ ልማትና አቅርቦት ፣በእንስሳት ማደለብና ማሞከትና ማደለብ ፣ በሰብል ልማትና በሌሎችም ዘርፈ ብዙ ስራዎች ስራ አጥ ዜጎችን ወደ ስራ ለማስገባት በቁርጠኝነት መሰራት እንዳለበት ገልጸዋል ።

ስራ አጥ ዜጎችን በተለያዩ ዘርፎች ላይ በማሰማራት የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት በትኩረት መሰራት እንዳለበት አቶ ሙስጠፋ አመላክቷል

የጉራጌ ዞን ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ መሰለ ጫካ እንደገለጹት የኑሮ ዉድነቱን ችግር ለመቅርፍ አመራሩ በቁርጠኝነት ሊሰራ ይገባል ብለዋል ።

አመራሩ በመቀናጀት በየአካባቢው ያሉትን ጸጋዎችን በመለየት ስራ አጥ የሆኑ ዜጎችን ወደ ስራ በማስገባት ምርትና ምርታማነትን በማሳድግ የኑሮ ውድነቱን መቀርፍ እንደሚገባ አቶ መሰለ ጫካ ገልጸዋል ።

የተሰራጩ ብድሮችን ባለመመለሱ ምክንያት ሌላው ስራአጥ ወጣት እንዳይጠቀም እንቅፋት እየሆነ መቷል ያሉት ዋና የመንግስት ተጠሪው ይህንም ለማስመለስ በልዩ ትኩረት መሰራት እንዳለበት ተናግረዋል ።

የጉራጌ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ መላኩ ብረሀኔ በበኩላቸው የዋጋ ግሽበቱን ለመከላከል ለነገ የሚባል ጉዳይ ባለመሆኑ ሁሉም የሚመለከታቸው አካላት በትኩረት ሊሰሩ ይገባል ብለዋል።

የፋብሪካ ምርቶች በቂ አለመሆን፣ምርቶችን በመጋዘን ማስቀመጥ፣ ህገወጥ ደላሎችና ሌሎችም በርካታ ምክንያቶች ለዋጋ ንረቱ እንደምክንያት የጠቀሱት አቶ መላኩ ብረሀኔ ይህን በዝምታ ባለማለፍ በጋራ ማስተካከል ይገባል ብለዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት እንደገለጹት ከሌላው ጊዜ በተለይ መልኩ ይህን ክህሎት መር የሆነ እቅድ ለማሳካት በትኩረት እንደሚሰሩ ተናግረዋል ።

የኑሮ ውድነቱን ለመቀነስ ስራ አጥ ዜጎች ወደስራ ማስገባትና ህገ ወጥ ደላሎችን ስራአት ማሰያዝና ሌሎችም የሚያባብሱ ጉዳዮችን በጋራ መስራት እንዳለባቸው አመላክተዋል ።

በመድረኩም የክልል፣ የዞን፣የወረዳና የከተማ አስተዳደር አመራሮችና የሚመለከታቸው ባለ ድርሻ አካላት ተሳትፈዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *