ስልጠናው “የህልም ጉልበት ለእመርታዊ እድገት” በሚል መሪ ሀሳብ እንደሚሰጥ ተጠቁሟል።
በንድፈ ሀሳብና በነባራዊ እውነታዎች ተደግፎ በሚሰጠው በዚህ ስልጠና በየደረጃው ያለው አመራር ሀገራዊ፣ ቀጠናዊ፣ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ዲፕሎማሲያዊ ሁኔታዎችን ተገንዝቦ ወቅቱን የዋጀና ውጤታማ አመራር ለመስጠት ያስችላል።
ስልጠናው ሀገሪቱ የጀመረችውን የብልጽግና ጉዞ ከግብ ለማድረስ አመራሩ በአስተሳሰብ፣ በእውቀት፣ በክህሎትና በስነ ምግባር ጎልብቶ የተጣለበትን ኃላፊነት በብቃትና በቁርጠኝነት ለመወጣት የሚያስችለውን አቅም ያዳብራል ተብሎ ይጠበቃል።
ሀገራዊ ህልም ላይ መግባባት፣ አመራሩ ኃላፊነቱ በብቃት እንዲወጣ ማብቃት፣ የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት እንዲይዝ እና ተጨማሪ ግብዓቶች ለማግኘት አላማ ያደረገ ነው ተብሏል።
ስልጠናው ለተከታታይ ለ10 ቀናት የሚቆይ ሲሆን ከ 8 መቶ 10 በላይ አመራሮች ስልጠናው ይወስዳሉ።
በመድረኩ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ፣ የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አለማየሁ ገ/መስቀል፣ የወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፋሪስ ደሊል ጨምሮ የዞኑ አመራሮች ተገኝተዋል።