ሴቶች በሁሉም የልማት መስኮች ተሳታፊ እንዲሆኑ በማድረግና የሚደረስባቸውን የሀይል ጥቃት በጋራ መከላከል እንደሚገባ የጉራጌ ዞን ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ መምሪያ አስታወቀ ።

በሀገራችን ለ46ኛ ጊዜ የሚከበረዉ አለም አቀፍ የሴቶች ቀን (ማርች 8 ) በዞኑ በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት ተከብሯል።

ሴቶች በሰላም ፣በዲሞክራሲ ስርአት ግንባታና በመልካም አስተዳደር ጉዳዮች እኩል ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማሰቻል የበአሉ መከበር ፋይዳዉ የጎላ ነዉ።

ማርች 8 የሴቶች ቀን በአል በዓለም አቀፍ ጀረጃ ለ 111ኛ ጊዜ “Gender Equality to day for asustainable tomorrow “የስርዐተ ፆታ እኩልነት ለዘላቂ ልማት’እንዲሁም በሀገር አቀፍ ደርጃ ደግሞ ለ46 ኛ ጊዜ ” እኔ የእህቴ ጠባቂ ነኝ”በሚል መሪ ቃል የሚከበረው የሴቶች ቀን በጉራጌ ዞን በደማቅ ሁኔታ በወልቂጤ ከተማ ተከብሯል ።

የሴቶች ውሳኔ ሰጭነት ፣ተጠቃሚነትና ተሳታፊነት ለማሳደግ መንግስት በርካታ ስራዎች እየሰራ እንደሆነም ይታወቃል።

በበአሉ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የጉራጌ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አበራ ወንድሙ እንደገለጹት ሴቶች ያልተሳተፉበት ማንኛውም ኢኮኖሚያዊ ፣ፖለቲካዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች ላይ ተጽእኖ እንደሚፈጥር የሚታወቅ በመሆኑ ሴቶችን በሁሉም መስክ ማሳተፍ ይገባል ብለዋል።

ከዛሬ 1 መቶ 11 አመት በፊት በአሜሪካ ግዛት እንኳን ሴቶች ከወንዶች እኩል መብታቸው ሊከበር ቀርቶ የጭቆና ቀንበር ተጭኖባቸው ስለነበር ይህ ምሬት ያንገሸገሻቸው አሜሪካውያን ለእኩል ስራ እኩል ክፍያ የተጀመረው ንቅናቄ ለዛሬ የሴቶች ቀን መከበርና መብቶቻቸው በዘላቂነት እንዲከበር አድርጓል ብለዋል።

በተጨማሪም በሀገር አሜሪካ ንቅናቄው ይጀመር እንጂ በሀገራችን ኢትዮጵያ ያውም በጉራጌ ዞን ከአሜሪካ ከ56 አመት ቀድማ የባህል ተጽዕኖ ሳይበግራት ለሴቶች ነጻነት መጎናፀፍ ምክንያት ለሆነችው የቃቄ ወርዶት ክብር ይገባል ብለዋል ።

የጉራጌ ዞን ሴቶችና ህጻናት ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ መሰረት አመርጋ እንዳሉት የዘንድሮው በዓል ለየት የሚያደርገው ከህጻናት እስከ አዛውንት ያለምንም ልዩነት ዋጋ የተከፈለበት የህዳሴው ግደብ የመጀመሪያ የሀይል የማመንጨት ስራው የተበሰረበት እና 1መቶ 26 ኛው የአድዋ ድል በዓል በልዩ ሁኔታ የተከበረበት ወርና የሴት ጀግኖች የሚታወሱበት እለት በመሆኑ በአሉ ለየት ያደርገዋል ።

የሴቶች ውሳኔ ሰጭነት ፣ተጠቃሚነትና ተሳታፊነት ለማሳደግ መንግስት በርካታ ስራዎች እየሰራ እንደሆነም ገልጸዋል ።

እንደ ሀገርም ሆነ እንደ ዞናችን በሴቶች ላይ እየተፈጸሙ ያሉ የሀይል ጥቃቶች እየተበራከቱ መሆኑ አስታዉሰዉ ይህንንም አጸያፊ ተግባር በጋራ ልናወግዘዉና ልንከላከለዉ እንደሚገባም አሳስበዋል ።

የሴቶች ኢኮኖሚያዊ ችግር ለመቅረፍ እየተደረገ ባለዉ እንቅስቃሴ ጀግኖች እናቶቻችን በግል፣በልማት ቡድን በማህበር ተደራጅተው በግብርና በንግድ የላቀ አስተዋጽኦ እያደረጉ እንደሆነም አስታዉቀዋል።

አንዳንድ የበአሉ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት በዞናችን ውስጥ የሴቶች መብት እንዲከበር ታሪክ የማይሽረው ተግባር ለፈጸመው እናቶች ክብር ይገባቸዋል ብለዋል።

በተጨማሪም ሴቶች በሁሉም የልማት መስኮች እንዲሳተፉና ዉጤታማ ስራ እንዲሰሩ ለማድረግ መንግስትም እያደረገ ያለው በጎ ጅምር ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።

በዞኑ ሴቶች በተለያዩ የልማት ቡድን ውጤት ላስመዘገቡ ፣በ 2013 ወደ ዩኒቨርስቲ መግቢያ ከፍተኛ ውጤት ላመጡ ሴት ተማሪዎች ፣በጤናው ዘርፍ ከፍተኛ እንቅስቃሴ ላደረጉ ተቋማትና ግለሰቦች የዋንጫ፣የገንዘብና የሰርተፍኬት ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

በበአሉም የዞን፣ የወረዳና የከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ፣ እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳትፈዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡

Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *