ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ይበልጥ ለማዘመንና የማህበረሰቡ ተጠቃሚነት ለማሳደግ የባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሰራር ወሳኝ መሆኑን የጉራጌ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ አስታወቀ።

መምሪያው የ2014 በጀት አመት የአንደኛ ግማሽ አመት እቅድ አፈፃፀም ግምገማና የቀጣይ እቅድ ላይ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የምክክር መድረክ በአገና ከተማ አካሂዷል።

የጉራጌ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ኃላፊ አቶ ደምስ ገብሬ በመድረኩ ተገኝተው እንደገለፁት የህብረተሰቡን ኑሮ ቀላል እንዲሆን ለማስቻልና የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፉ ለማሳደግ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ርብርብ እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል።

በኢኮቴ ሃርድዌርና ሶፍትዌር መሳሪያዎችን ጥገናና እድሳት በማድረግ ከመንግስት መደበኛ በጀት ሊወጣ የነበረውን ከ1 ሚሊየን 56 ሺህ 7 መቶ ብር በላይ ሀብት ማዳን መቻሉንም ተናግረዋል።

ሁሉም ባለበት አከባቢ በመሆን ከክልልና ከፌደራል ጋር ውይይት በማድረግ የሚፈልጉትን መረጃ ለመቀበልና ለማስተላለፍ የቪዲዮ ኮንፈረንስ ውይይቶች መደረጉን የገለፁት አቶ ደምስ በዚህም ከመንግስት ሊወጣ የነበረውን 1 ሚሊየን 16 ሺህ 698 ብር ማዳን እንደተቻለም አመላክተዋል።

ተቋሙ ከወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር ዞናዊ ዌብሳይት በማልማት ላይ መሆኑን ገልፀው ይህም በቀጣይ የዞኑን የኢንቨስትመንት፣ የቱሪዝም መዳረሻዎችንና ሌሎችንም ሀብቶችና ቅርሶች ለአለም ህዝብ ለማስተዋወቅ ትልቅ ሚና እንደሚኖረው ጠቁመው በቀጣይ የተለያዩ የፈጠራ ስራዎች የባለቤትነት መብት እንዲያገኙ ጥረቶች እየተደረጉ መሆኑም ገልፀዋል።

ከፖለቴክኒክ ጋር በመቀናጀት ክበባት ለማጠናከርና የፈጠራ ስራውን እንዲጎለብት ለ19 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ስልጠና መሰጠቱንም አመላክተዋል።

ተቋማትን በቴክኖሎጂ በማስተሳሰር ከወረቀት ነፃ የሆነ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ የተጀማመሩ ስራዎች እንዳሉም ገልፀዋል።

በዞኑ ቡኢ፣ ቆሼና ቡታጅራ የማህበረሰብ የመረጃ ማዕከላት ላይ በዘርፉ የሰለጠኑ ወጣቶች የስራ ዕድል በመፍጠር ለማህበረሰቡ የቴክኖሎጂ ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን አቶ ደምስ ተናግረዋል።

አቶ ዲንሰፍ ጀማል ከእነሞርና ኤነር አቶ ደመላሽ ውዴ ከደቡብ ሶዶ ወረዳ የመድረኩ ተሳታፊ ሲሆኑ በጋራ በሰጡት አስተያየት በኢኮቴ ሃርድዌርና ሶፍትዌር ለበርካታ ጊዜያት ተበላሽተው የተቀመጡ መሳሪያዎችን ጥገናና እድሳት በማድረግ ወደ ስራ የማስገባት ስራ መስራታቸውን ጠቁመው በዚህም ከመንግስት ካዝና ሊወጣ የነበረውን ሀብት ማዳን መቻላቸለም ገልፀዋል።

የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ በማልማትና በማስፋት ለህብረተሰቡ ተደራሽ በማድረግ ተጠቃሚነታቸውን ማረጋገጥ ይገባል ያሉት ተሳታፊዎቹ ለዚህም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

ተቋሙ አዲስ ከመሆኑ አንፃር የበጀት እጥረት፣ የሰው ሀይልና የቢሮ እጥረት በመኖሩ ተግባራቶችን በተሻለ ደረጃ ለማከናወን ተግዳሮት መሆኑን ገልፀው የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት እገዛ እንዲያደርጉም ጠይቀዋል።

የ2014 በጀት አመት የሁለተኛ ግማሽ አመት እቅድ አፈፃፀምና የተከለሰ እቅድ ቀርቦ ሰፋ ያለ ውይይት ተደርጎባቸዋል።

በመድረኩም የጉራጌ ዞን ምክርቤት የዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች ጨምሮ የሁሉም ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደር ሳይንስና ቴክኖሌጂ ጽህፈት ቤት ኃላፊዎችና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

በመረጃ ምንጭነት ገጻችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!!

= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:-
https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *