ሰኔ 21/2015 ዓ.ምበጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ 1444ኛው የኢድ አል አደሃ አረፋ በዓል በድምቀት ተከበረ፡፡

ሰኔ 21/2015 ዓ.ም
በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ 1444ኛው የኢድ አል አደሃ አረፋ በዓል በድምቀት ተከበረ፡፡

ህዝበ ሙስሊሙ በዓሉ ሲያከብር የሰላም፣ የመቻቻልና የመረዳዳት እሴቶች ማጠናከር እንደሚገባ ተገለፀ፡፡

የአረፋ በዓል በኢትዮጵያ በተለይም በጉራጌ ዞን በህዝበ ሙስሊሙ ዘንድ በድምቀት ከሚከበሩ አበይት ክብረ በዓላት አንዱ ሲሆን የተራራቁ ወገኖች የሚቀራረቡበት፣ የተቸገሩት የሚረዱበት ህዝበ የአብሮነት እሴቶች የሚጎለብቱበት በዓል ነው።

የጉራጌ ዞን እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ኡስታዝ ሼህ ሀቢብ ሀጅ ህያር በበዓሉ ተገኝተው እንዳሉት የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል ማህበራዊ ትስስራችንን ይበልጥ እንድናጠናክር ከሚታረደው እርድ አንድ ሶስተኛው ለሚስኪኖችና ለአቅመ ደካሞች እንድለግስ፣ ለጎረቤት፣ ለዘመድ እዝማድና ለሌሎችም በማካፈል እንድንናከብር የታዘዝንበት የአንድነትና የመተሳሰብ በዓል ነው።

በመሆኑም ህዝበ ሙስሊሙ ከአላህ የታዘዝነውን ተግባር በመፈጸም የተቸገሩ ወገኖችን ከማሰብ ባለፈ በማካፈል ሊሆን ይገባልም ብለዋል።

ህዝበ ሙስሊሙ ለሀገር ሰላም፣ ልማትና እድገት ላይ እያደረገው ያለው ንቁ ተሳትፎ በቀጣይም ከመንግስት ጎን በመቆም ማጠናከር እንዳለበት ተናግረዋል።

የወልቂጤ ከተማ ከንቲባ አቶ እንዳለ ስጦታው የአረፋ በዓል የሰው ልጅ ለፈጣሪው የታማኝነቱን ልክ የገለጠበት ፈጣሪም ለሰው ልጅ የፍቅሩን መጠን ያሳየበት ትልቅ በዓል ነው ብለዋል።

የአረፋ በዓል በዞኑ ማህበረሰብና በከተማችን ነዋሪዎች ዘንድ ሲከበር ልጆች ለቤተሰቦቻቸው ያላቸውን ለሌላቸው ፍቅራቸውን፣ መተባበራቸውን ብሎም መተማመናቸውን የሚገልጹበት በዓል እንደሆነ አስረድተዋል።

በዓሉን ስናከብር የተለመደውን እርስ በእርስ በመተሳሰብ፣ ጥላቻን የምናስወግድበት፣ የመተዛዘን ተግባር የምናጸናበት በዓል ሊሆን ይገባል ብለዋል።

ከበዓሉ ጎን ለጎን የክረምት ወር እንደመሆኑ መጠን የአረንጓዴ አሻራ ስራዎችን በማጠናከር በየአከባቢያችን የሰላምና የልማት እንቅስቃሴዎች ላይ በንቃት መሳተፍ እንደሚገባም ጠቁመዋል።

የበዓሉ ተሳታፊዎች እንዳሉት የአረፋ በዓል በሰላም መከበሩ ገልጸው ህዝበ ሙስሊሙ በበዓሉ ወቅት የመረዳዳት የመተሳሰብ እሴቶችን በማጠናከር የተቸገሩ ወገኖችን በማካፈል መከበር እንዳለበትም ገልጸዋል።

በዓሉ ከማክበር ጎን ለጎን ህዝበ ሙስሊሙ በሀገር ሰላም፣ ልማትና እድገት ላይ እያደረገ ያለው ንቁ ተሳትፎ በቀጣይም አጠናክሮ ማስቀጠል ይኖርበታል ብለዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *