መንግስት የህዝቡን ሰላምና ደህንነት በማረጋገጥ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴያቸው እንዲመለሱ ለማድረግ የወሰደው እርምጃ እንዳስደሰታቸው የቆሴ ከተማና አካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ።

በአካባቢው የነበረው ችግር ለመፍታት መንግስት ከፍተኛ ጥረት ማድረጉን የጉራጌ ዞን ሰላምና ጸጥታ መምሪያ አስታወቀ።

የአካባቢው ነዋሪዎች ህዝቡን የማይወክሉ ግለሰቦች እያደረሱባቸው የነበረው ግፍና በደል የአብሮነታቸውን እሴት የጣሰ ህገወጥ ተግባር እንደነበር ገልጸዋል።

ባለፉት ሶስት አመታት የስቃይና የመከራ ጊዜ እንዳሳለፉ የተናገሩት ነዋሪዎቹ እነዚህ ህገወጦች የቤት ቃጠሎና የንብረት ውድመት የእለት ተዕለት ተግባራቸው ነበር ብለዋል።

በመሆኑም መንግስት የነዋሪዎቹን ችግር በዘላቂነት እንዲቀረፍ በማድረግ የሰላምና የአንድነት ኮንፈረንስ መካሄዱ ደስታ እንደፈጠረላቸው ገልጸዋል።

የእኖር ኤነር ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሸምሱ ሸሀቡ የሰላም ኮንፈረንሱ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የመጀመሪያ ዙር ኃይል ማመንጨቱን በተበሰረበት እለት መካሄዱ ደስታው ድርብ ያደርገዋል ብለዋል።

የሰው ልጅ የእለት ተዕለት እንቅስቃሴው ለመከወን ፣ በህይወት ለመኖር፣ ሀብት ለማፍራት፣ ወልዶ ለመሳም ሰላም መሰረታዊ እና ለድርድር የማይቀርብ በመሆኑ ህብረተሰቡ የአካባቢውን ሰላም በንቃት መጠበቅ ይጠበቅበታል ብለዋል።

እንደ አቶ ሸምሱ ገለጻ ህዝብ ያለጸጥታ ችግር መኖር እንዲችል እና በልማትና በመልካም አስተዳደር ስራዎች ተጠቃሚ ለማድረግ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

የጉራጌ ዞን ሰላምና ጸጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ መስፍን ተካ በበኩላቸው መንግስት በቆሴና አካባቢዋ የነበረውን ችግር ለመፍታት ቢሰራም ህገወጦች ደግሞ በተደጋጋሚ የቤት ቃጠሎና የንብረት ውድመት በማድረስ ህዝቡን ሲያሰቃዩ እንደነበር ገልጸዋል።

በመሆኑም የነዋሪዎቹን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ ከህብረተሰቡ፣ ከሀገር ሽማግሌዎች እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በተደረገው ውይይት ችግሩ በመቅረፍ የሰላም ኮንፈረንስ ማካሄድ እንደተቻለ አሰረድተዋል።

ህብረተሰቡ የአካባቢው ሰላም በዘላቂነት ለማስቀጠል ከመጠበቅ በተጨማሪ በህገወጥ ድርጊት በሚሳተፉ አካላት መረጃ በመስጠት ከመንግሥት ጋር መስራት እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

በመረጃ ምንጭነት ገጻችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!!
= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:-
https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *