መንትዬዎች በ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተመሳሳይ ዉጤት አመጡ።

ተማሪ ሚጣ ሞሳ እና ሀና ሞሳ መንትዬዎች ናቸዉ። ሁለቱም መንትዬዎች የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ ባዘጋጀው ዞን አቀፍ የጥያቄና መልስ ውድድር መድረክ ተሞክሮዋቸው ለተማሪዎች እንዲያካፍሉ ጥሪ ከተደረገላቸው ተማሪዎች መሀከል ተገኝተው ነበር።

በወልቂጤ ከተማ በጉብሬ ክፍለ ከተማ በአባ ፍራንሷ ሁለተኛና መሰናዶ ትምህርት ቤት የ2013 ዓመተ ምህረት ሀገር አቀፍ የ12ኛ ብሔራዊ ፈተና ተፈትነዋል።

የሁለቱ መንትዬዎቹ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ዉጤት 477 አምጥተዉ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለመግባት ይጠባበቃሉ።

ሚጣ ሞሳ 477 ዉጤት ፣ ሀና ሞሳ 477 መንትዮዎቹ ተመሳሳይና መንታ ዉጤት ነዉ ያመጡት።

ሁለቱም መንትዬዎች የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ ባዘጋጀው ዞን አቀፍ የጥያቄና መልስ ውድድር ተሞክሮዋቸው ለተማሪዎች ለማካፈል ተገኝተው እንደገለፁት ትምህርታቸው በክፍል ውስጥ በተገቢ ይከታተላሉ ከትምህርት መልስ ላይብረሪ ገብተዉ ማጥናት ያዘወትራሉ።

ይህ ደግሞ የቤተሰብና መምህራን ክትትልና ድጋፍ ታክሎበት የበለጠ ዉጤታማ እንዳደረጋቸዉ ይናገራሉ።

ተማሪ ሚጣ ሞሳና ሀና ሞሳ የአጠናን ተሞክሮዎቻቸዉን ሲናገሩ ለተማሪዎች ዉጤታማነት ትምህርት በክፍል ውስጥ በተገቢ ከመከታተል ባሻገር ላይብሪ (ቤተ መጽሀፍት ) ወሳኝ በመሆኑ በሁሉም አካባቢዎችና ትምህርት ቤቶች ውስጥ ደረጃው የጠበቀ ቤተመፅሀፍ መሰራትና ማደራጀት ያስፈለረጋል ብለዋል።

የሁለቱም መንትዬዎች ቀጣይ አላማቸዉ ሲገልጹ አንድ ዩኒቨርሲቲ ዉስጥ ገብተዉ የህክምና ትምህርት በማጥናትና በከፍተኛ ዉጤት ተመርቀዉ ለመስራት እና ሀገራቸው ለማገልገል ትልቅ ራዕይ አላቸዉ።

       ( መንትዬዎች መንታ ዉጤት አመጡ !!!)

በመረጃ ምንጭነት ገፃችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!

= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *