መምሪያው የጉራጊኛ ትምህርት መጽሀፍቶች ለማዳበር ለጉራጊኛ ትምህርት መምህራና ለሌሎችም ባለድርሻ አካላት የአቅም ማጎልበቻ የስልጠናና የምክክር መድረክ ለሁለት ተከታታይ ቀናት በወልቂጤ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

መምሪያው የጉራጊኛ ትምህርት መጽሀፍቶች ለማዳበር ለጉራጊኛ ትምህርት መምህራና ለሌሎችም ባለድርሻ አካላት የአቅም ማጎልበቻ የስልጠናና የምክክር መድረክ ለሁለት ተከታታይ ቀናት በወልቂጤ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

በስልጠናና በምክክር መድረኩ የተገኙት የጉራጌ ዞን አስተዳደር ጽህፈት ቤት ኃላፊና የቋንቋ ትምህርት ቴክኒክ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ደሳለኝ ፈቀደ እንዳሉት የዞኑ መንግስት የጉራጊኛ ቋንቋ የመማሪያና የስራ ቋንቋ እንዲሆን በትኩረት እየተሰራ ይገኛል።

ቋንቋ መግባቢያ ብቻ ሳይሆን የማንነት መገለጫ ጭምር መሆኑን ያነሱት አቶ ደሳለኝ ከዚህ ቀደም ለጉራጊኛ ቋንቋ ትምህርት ትኩረት ባለመሰጠቱ ትውልዱ በቋንቋው ሳይማርና የስራ ቋንቋ ሳይሆን ቆይቷል ብለዋል።

ይህንንም ችግር ለመቅረፍ በባለፉት አመታት በዞኑ በቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች በጉራጊኛ ቋንቋ ማስተማር መጀመሩንና በ1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሙከራ ትምህርት እየተሰጠ መሆኑን አንስተዋል።

የዞኑ ቴክኒክ ኮሚቴ በቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶችና በ1ኛ ክፍል የሙከራ ትምህርት አሰጣጡና ያለበት ደረጃ ላይ የመስክ ምልከታ ማድረጉን ገልጸው በዚህም የታዩ የተሻሉ ተግባራት ለማስቀጠልና የነበሩ ጉድለቶች ለማረም ያለመ መድረክ ነው ብለዋል።

በዞኑ የጉራጊኛ ቋንቋ በስርአተ ትምህርት በማካተት የመማሪያና የስራ ቋንቋ ለማድረግ ብሎም ለማሳደግ የተጀመረው ስራ ሁሉም የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ አቶ ደሳለኝ አስገንዝበዋል።

የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ መብራቴ ወልደማርያም በበኩላቸው በዞኑ ባለፉት ሁለት አመታት የጉራጊኛ ቋንቋ በስርአተ ትምህርት በማካተት የተጀመረው ስራ የተሻለ ደረጃ ላይ ይገኛል ብለዋል።

በመድረኩም በመማር ማስተማሩ ሂደት ብሎም መጽሀፉ ሙሉ ለሙሉ ወደ ህትመት ከመግባቱ በፊት ያጋጠሙ ችግሮች በስልጠና እንደሚዳበርም ገልጸዋል።

ቴክኒክ ኮሚቴው በመስክ ምልከታው ወቅት ባደረገው ምልከታ እየተሰጠ ያለው የጉራጊኛ ትምህርት ላይ ያሉ ጠንካራ ጎኖች ማጠናከርና ያሉ ጉድለቶችን በማረም ዘርፉ ውጤታማ እንዲሆን መስራት እንደሚገባ አመላክተዋል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *