መልካም የመታመን ዘመን” በሚል መሪ ቃል የቡታጅራ ከተማ የደረጃ “ሐ”ግብር ከፋዮች ግብራቸውን እየከፈሉ መሆኑን የቡታጅራ ከተማ ገቢዎች ባለስልጣን ቅ/ጽ/ቤት ተገለፀ

የ2015 ዓመተ ምህረት የግብር ወቅት ከሀምሌ 1 2014 ዓ.ም የተጀመረ ሲሆን ግብር ከፋዮች እንዳይጉላሉ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎቶችን ለመስጠት የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቅርንጫፋ ጽ/ቤትና የከተማው ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት በቅንጅት እየሰሩ መሆኑ ገለፁ።

አንድ ነጋዴ ለሰራበት ስራ ለሀገሩ ልማት ይውል ዘንድ በሚያገኘው ገቢ ልክ ግብሩን በወቅቱ መክፈል እንደሚገባውና ከአላስፈላጊ ወጪ እንዲድን ግብሩን በወቅቱ መክፈል እንዳለበት ተገልጿል።

በዚህም የደረጃ “ሐ” ግብር ከፋዮች ቡታጅራ ከተማ ላይ በሚገኙ እሬሻና እሪንዛፍ ክፍለ ከተሞች ላይ መክፈል የተጀመረ ሲሆን የነጋዴው ጊዜና እንግልት ለማስቀረት የግብር መክፈያና የንግድ ፍቃድ እድሳት በአንድ አዳራሽ ውስጥ በትይዩ እየሰሩ መሆኑን ቅኝት ባደረግንበት ወቅት መታዘብ ችለናል።

አቶ ሙሰማ ሁሴን የተባሉ ግብር ከፋይ በስፍራው ተገኝተን ባደረግንላቸው ቃለመጠየቅ እንደገለፁት የግብር መክፈያ ቦታና የንግድ ፍቃድ ማደሻ ቦታ በተመሳሳይ ቦታ በመሆኑ ከአላስፈላጊ እንግልት መዳን ችለናል ብለውናል።

አቶ አወል ወራቄ የቡታጅራ ከተማ ገቢዎች ባለስልጣን ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ እንደገለፁት በ2014 ዓ.ም በመደበኛ እና በመዛገጃ ቤታዊ ገቢ 171 ሚሊየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ ከመቶ ፕርሰንት በላይ መሰብሰቡን ገልፀዋል።

ይህንን መነሻ በማድረግ በ2015 በጀት ዓመት ከአምናው እቅድ ከ30 ፕርሰንት በላይ በማሳደግ መሰብሰብ እንደሚቻል ተናግረዋል።

የ2014 በጀት ዓመት ከተማው ከእቅዱ በላይ ግብር መሰብሰብ የተቻለው ባለሙያው ከአመራሩና ከህብረተሰቡ ጋር በቅንጅትና በቁርጠኝነት በመስራቱ እንደሆነ ገልፀው በቀጣይም ግቡን ለማሳካት ቅንጅታዊ ስራው በቀጣይነትም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል።

አቶ ሀቢብ አብደላ የነጋዴው ጊዜና እንግልት ለመቀነስ ከገቢዎች ጋር በመቀናጀት በአንድ ጣራ ስር ከመስራትም ባለፈ አሰራራችን በማዘመን መረጃዎቻቸውን በኦንላይን ኢንተርኔት አገልግሎት እየሰጠን ነው ብለዋል፤ይህም የነጋዴውን መረጃ ከማዘመንም በተጨማሪ ህገወጥ ነጋዴዎችንም ለመከላከል ያግዛል ብለዋል።

ነጋዴው የሚከፍለውን ገቢ የከተማውን እድገትና ልማት የሚውል መሆኑን በመረዳት ግብሩን በታማኝነት በጊዜው እንዲከፍሉ አሳስበዋል።

ከተማው በደረጃ “ሐ” ግብር ከፋዮች እስከ 14 ሚሊየን ብር እንደሚሰበስብ የገለፀ ሲሆን እስከ ሀምሌ 13/2014 ድረስ ከ7 ሚሊየን ብር በላይ መሰብሰቡን ተገልጿል።

የደረጃ “ሐ” ግብር ከፋዮች በአጭር ቀናት በማጠናቀቅ የደረጃ”ለ” ግብር ከፋዮች ግብር እንደሚጀመር ከከተማው ገቢዎች ባለስልጣን ቅ/ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በመረጃ ምንጭነት ገፃችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!
= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36CxQ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *