መላው የጉራጌ ህዝብ ለኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ አህመድ ላደረገው አቀባበል የዞኑ አስተዳደር ምስጋናውን አቅርቧል።


መላው የጉራጌ ህዝብ ለኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ አህመድ ላደረገው አቀባበል የዞኑ አስተዳደር ምስጋናውን አቅርቧል።

የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ የለውጡን መንግስት የሚደግፍ ጉዞ ህዝባዊ ሰልፍና የጠቅላይ ሚኒስትሩ አቀባበል ህዝባችን ዘመናትን የተሻገረ እንግዳ ተቀብሎ የማስተናገድ እሴቱ ከፍ ብሎ ያሳየበት ነበር ብለዋል።

የጉራጌ ማህበረሰብ መገለጫ የሆነው ስራ ወዳድነትና ታታሪነቱን ይበልጥ በማጎልበት የሀገሪቱ የብልጽግና ጉዞ ለማሳካት በቁርጠኝነት ሊሰራ ይገባል።

የጉራጌ ማህበረሰብ በሚኖርበት ቦታ ሁሉ አብሮ እና ተቻችሎ በሰላም መኖር የሚችል ታታሪና ስራ ወዳድ ብቻም ሳይሆን አኩሪ የሆነ የእንግዳ አቀባበል ባህሉ በዛሬው መድረክ ይበልጥ እንዲጎላ አድርጎታል ብለዋል አቶ ላጫ።

የዛሬው የእንግዳ አቀባበል ፕሮግራም እንዲሳካና በሰላም እንዲጠናቀቅ የክልላችን ርዕሰ መስተዳድር ክቡር እንዳሻው ጣሰው ፣ በየደረጃው ያለው አመራራችን፣ ወጣቶች፣ ሴቶች፣ የጸጥታ አካላት፣ መላው የጉራጌ ህዝብ እና ሌሎች ተሳታፊዎች ላበረከቱት አስተዋጽኦ ከፍ ያለ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *