በጀርመን ሀገር የደቡብ ልማት ማህበር ሉካን ቡድን ከዚህ ቀደም ለሆስፒታሉ ያደረጋገው የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ በስራ ላይ መዋላቸውንና የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክሮ ለማስቀጠል የሚያስችል የስራ ጉብኝት ተካሂዷል።
የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልና የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ቺፍ ኤክስኩቲቭ ዳይሬክተር ዶ/ር አብድራሂም በድሩ እንደገለጹት ሆስፒታሉ ለአንድ መቶ ሺህ የህብረተሰብ ክፍሎች የህክምና አገልግሎት መስጠት እንደሚችል ጠቁመዋል።
በሆስፒታሉ ያለተጀመሩ የህክምና አገልግሎቶችን በተለይም አከባቢው ከንግድ እንቅስቃሴ ጋር በተገናኘ ከፍተኛ የመኪና አደጋ የሚከሰት በመሆኑ የአጥንት ህክምና ሌሎች ህክምናዎች በስፔሻሊስት ሀኪሞች ለማስጀመር ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።
አክለውም ዩንቨርስቲው ከመማር ማስተማር ጉን ለጎን በምርምር ስራ ትኩረት በማድረግ የማህበረሰቡን የጤና ችግር ለመቅረፍ በቁርጠኝነት እየሰራ መሆንም አስታውቀዋል።
እንደ ዶክተር አብድራሂም ገለፃ ሆስፒታሉ አሁን ከሚሰጠው የስፔሻሊቲ ህክምና ባሻገር በቀጣይ የሰብ ስፔሻሊቲ ህክምና ለመጀመር የ5 አመት ፕሮግራም ቀርፆ እየሰራ እንደሚገኝም አስረድተዋል።
የህብረተሰቡን የጤና ፍላጎት እየሰፍ በመምጣቱ በቀጣይ በ ሆስፒታሉ ያሉ በርካታ የህክምና ቁሳቁሶች እጥረት ለመቅረፍ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላትና ሁሉም የአከባቢው ተወላጆች እገዛ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።
ዶክተር አብድራሂም አያይዘውም በጀርመን ሀገር የደቡብ ልማት ማህበር ሆስፒታሉ ከዚህ በፊት ስራ እንዲጀምር በርካታ የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉን አስታውሰው ቁሳቁሶቹም ለህብረተሰቡ ተገቢ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን ለማረጋገጥና በቀጣይም ከተቋሙ ጋር በጋራ ለመስራት የዳሰሳ ጥናትና የስራ ጉብኝት መደረጉንም አስረድተዋል።
ልማት ማህበሩ ለተቋሙ እያደረገ ላለው ከፍተኛ አስተዋፅኦ አመስግነዋል።
በጀርመን ሀገር የደቡብ ልማት ማህበር ሰብሳቢ ወይዘሮ ዘመናይ አዳነ ሆስፒታሉን በጎበኙበት ወቅት እንደገለጹት በ2009 ዓ.ም በርካታ የህክምና ቁሳቁሶችን በማሰባሰብ ከማህበሩ ጋር በመሆን ለሆስፒታሉ ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልፀዋል።
በጉብኝቱም ከዚህ በፊት ለተቋሙ ድጋፍ ያደረጉዋቸው የህክምና ቁሳቁሶች በተገቢው ለህብረተሰቡ አገልግሎት እየሰጡ በመሆኑ እጅግ መደሰታቸው የተናገሩት ኃላፊዋ በጀርመን ሀገር ሆነው ድጋፉን ለሰባሰቡና ለላኩ አካላት ሁም አመስግነዋል ።
በደቡብ ክልል ውስጥ በጤና፣ በትምህርትና በሌሎች ማህበረሰባዊ አገልግሎቶችና የህክምና ቁሳቁስ ድጋፎችን አጠናክረው እንደሚቀጥሉና ለጤና ባለሙያዎች የእውቀት ሽግግር ለማድረግ ስልጠና ለመስጠት መታቀዱንም አስረድተዋል።
ህክምና ሲያደርጉ ያገኘናቸው ታካሚዎች እንዳሉት ሆስፒታሉ ለአከባቢው ማህበረሰብ እየሰጠ ባለው አገልግሎት መደሰታቸውና ባላሙያዎችም ለታካሚዎች እያደረጉት ያለው እንክብካቤ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም ጠቁመዋል።
ተቋሙ ለህብረተሰቡን በጤናው ዘርፍ የሚስተዋለውን ችግር ለመቅረፍ እያደረገ ያለው ተግባር በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx