“ሕይወቱን ለሚሰጠኝ ደሜን እለግሳለሁ” በሚል መሪ ቃል በቡታጅራ ከተማ ለጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት የደም ልገሳ ተካሄደ!!

መስከረም 14/2015

“ሕይወቱን ለሚሰጠኝ ደሜን እለግሳለሁ” በሚል መሪ ቃል በቡታጅራ ከተማ ለጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት የደም ልገሳ ተካሄደ!!

“ሕይወቱን ለሚሰጠኝ ደሜን እለግሳለሁ” በሚል መሪ ቃል በቡታጅራ ከተማ የማርሻል አርት ተማሪዎችና ወጣቶች ለጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት የደም ልገሳ አካሄደዋል።

በደም ልገሣ ፕሮግራሙ በክብር እንግዳነት የተገኙት የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ረዳት የመንግስት ተጠሪው አቶ ሽፋ መሃመድ በንግግራቸው ይህን ፕሮግራም ላዘጋጁት የቡታጅራ ከተማ ማርሻል አርት ማህበር እና የከተማው ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት በ/ጽ/ቤታቸው ስም ምስጋና አቅርበዋል።

የከተማው ወጣቶች እና ስፖርት ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ነጋሽ መሃመድ ለወጣቶቹ ባደረጉት ማብራሪያ ሁሉም የከተማዋ ወጣቶች በክረምቱ የበጎ ፍቃድ ተግባር ስራዎች ላይ በንቃት እየተሳተፉ ሲሆን በተላይ በደም ልገሳ ፣ በአረጋውያን ቤት ጥገና ፣ በችግኝ ተከላና ክብካቤ ፣ የአቅም ውስንነት ላለባቸው ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ፣ ለተቸገሩ ሴቶችና ህፃናት ከህዝቡ አልባሳትን በማሰባሰብ የአልባሳት ድጋፍ እንዲሁም በበዓላት ወቅት ከተማው ላይ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይከሰት ከትራፊክ ፖሊስ ጋር በመሆን የመንገድ ትራፊክ ስራ ላይ በንቃት እየተሳተፉ ነው ብለዋል።

በዛሬው እለትም የከተማው የማርሻል አርት ተማሪዎችና መምህራን እንዲሁም ሌሎችም የበጎ ፍቃድ ወጣቶች የማስ ስፖርት(የጋራ ስፖርት) ከሰሩ በኀላ በደም ልገሳ በችግኝ ኩትኳቶና ክብካቤ ስራ እንዲሁም የመስቀል በዓል ምክንያት በማድረግ ከተለያዩ ቦታዎች ወደ ከተማ የሚገቡ መኪኖች የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይኖር ከትራፊክ ፖሊስ ጋር የማስተናበር ስራ እየሰሩ ይገኛል።

በዘንድሮ የክረምት የወጣቶች የበጎ ፍቃድ ስራ ላይ በትኩረትና በስፋት እየሰሩ ለሚገኙ የከተማው ወጣቶች ሀገር ወዳድነታቸው በተግባር እያስመሰከሩ በመሆኑ ሌሎች ወጣቶችም በመሰል ተግባር ላይ እንዲሳተፉ የሚያነሳሳ ተግባር ነው ተብሏል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *