ሕዝቡ በየደረጃው ያነሳቸው ጥያቄ ለመመለስና ብልፅግና ፓርቲ በጉባኤው ያስቀመጣቸው አቅጣጫዎች ለማሳካት የቀጣይ የዘጠና ቀናት እቅድ መዘጋጀቱን የጉራጌ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት አስታወቀ።

በብልፅግና ጉባኤ ማግስት ፓርቲው ያስቀመጣቸው አቅጣጫዎችና በየደረጃው በተደረጉ ውይይቶች ከህዝቡ የተነሱ ጥያቄዎች በቀጣይ ሶስት ወራት ሊከናወኑ የሚገባቸው እቅዶች ላይ የዞን አመራሮች የወረዳ አስተዳዳሪዎች፣ የከተማ አስተዳደር ከንቲባዎችና የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊዎች በተገኙበት በወልቂጤ ከተማ ውይይት ተካሂዷል።

የጉራጌ ዞን ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ክፍሌ ለማ እንደገለፁት በብልጽግና ፓርቲ ጉባኤ የተላለፉ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎችን መሰረት በማድረግ በዞኑ በ14 የውይይት ማዕከላት የልማት፣መልካም አስተዳደር እንዲሁም በሰላምና ደህንነት ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ውይይት መደረጉ አስታውሷል ፡፡

በማህበረሰቡ ሳይመለሱ የቆዩ ጥያቄዎች የሚፈቱበትን አቅጣጫና ስልት ለመቀየስ እንዲሁም ግብዓቶችን ለማሰባሰብ ታልሞ በተከናወነው ሕዝባዊ የውይይት መድረክ በርከት ያሉ ግብዓቶችን የተገኙበት እንደነበር ገልፀው እነዚህ ጥያቄዎች በሚቀጥሉት ሶስት ወራት ህዝቡን በማሳተፍ ተደራሽ ለማድረግና ለመፍታት እቅድ መዘጋጀቱን ተናግረዋል፡፡

ሕዝቡ በየደረጃው ያነሳቸው ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ ለመመለስ ያስችል ዘንድ ቀጣይ አመራሩ በልዩ ትኩረት የሚመራው የዘጠና ቀናት እቅድ መሆኑ ገልፀዋል።

እቅዱ በዋናነት ማህበረሰቡ በልማት፣ መልካም አስተዳደር፣ የጸጥታና ደህንነት፣ እንዲሁም ከኑሮ ውድነት ጋር የተያያዙ ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ መሰረት በማድረግ የተዘጋጀ የዘጠና ቀናት እቅድ ሲሆን ይህም ከሚያዝያ 1/2014 እስከ ሰኔ 30/2014 ዓመተ ምህረት ድረስ የሚቆይ መሆኑን አቶ ክፍሌ አስታውቀዋል።

አቶ ክፍሌ አክለውም እቅዶቹም አሁን ያለንበት ሀገራዊና ዞናዊ ጉዳዮች ላይ ታሳቢ ያደረገ ሲሆን ከህዝብ የተነሱና የታቀዱ እቅዶች ደረጃ በደረጃ ለመተግበር ጥረት ይደረጋል ብለዋል።

እቅዱን ተግባራዊ ለማድረግ ስምንት ግቦች የተቀመጡ ሲሆን ግቦቹ ለማሳካት ደግሞ ዝርዝር ተግባራትና ስልቶችን ያቀፈ የእቅድ ሰነድ በማዘጋጀት ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት በየደረጃው በተካሄዱ ውይይቶች ህዝቡ ያነሳቸው ጥያቄዎች ፓርቲው በጉባኤው ካስቀመጣቸው አቅጣጫዎች በማስተሳሰር ተገምግሞ መደራጀታቸው ተገቢ መሆኑ ገልፀው እንደዞን በዚህ መልኩ መሰረታዊ የሆኑ ችግሮች ለይቶ በማቀድ የጋራ አቋም መያዙ ችግሮቹ ተጋገዞ ለመፍታት ያግዛል ብለዋል።

ህዝቡ በየደረጃው ያነሳቸው ጥያቄዎች ለመፍታት ህብረተሰቡ በተገቢ በማሳተፍ ለተሻለ ተጠቃሚነት በትኩረት እንደሚሰሩም ገልፀዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

በመረጃ ምንጭነት ገፃችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!

=ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *