ሐምሌ 14/2016 ዓመተ ምህረት ታላቁ የጎዳና ላይ የ15 ኪሎ ሜትር ሩጫ በወልቂጤ ከተማ እንደሚካሄድም ታዉቋል ።

የኬሮድ ኢትዮጵያ ታላቁ ሩጫ በበላይነት የሚመራዉ አትሌትና አሰልጣኝ ተሰማ አብሽሮ እንዳሉት በኢትዮጵያ ዉስጥ ከታላቁ ሩጫ ቀጥሎ ኬሮድ ኢንተርናሽናል ዉድድር ተጠቃሽ ነዉ።

በዘንድሮ አመት ለ4ኛ ዙር በወልቂጤ ከተማ የሚደረገዉ የ15 ኪሎ ሜትር ታላቁ ሩጫ የሚካሄድ እንደሆነም አብራርተዉ ዘንድሮ የፓራኦሎምፒክስ ዉድድርም እንደሚያካትት አስረድተዋል።

የዞኑ ብሎም የከተማዉ ማህበረሰብ በእንግዳ አቀባበሉ ፣ በስራ ባህሉ የሚታወቅ ሲሆን ለዉድድሩ የሚመጡ እንግዶች የተለመደ አቀባበል ማድረግ እንዳለባቸውና አገልግሎት ሰጪ ተቋማትም መስተንግዶቸው ይበልጥ ያማረ ማድረግ እንዳለባቸዉም ተናግረዋል።

ቀደም ሲል በተካሄዱ የኬሮድ ታላቁ ሩጫ ዉድድር ቱሪዝም በማጎልበት፣ ታዳጊ አትሌቶችን በማዉጣት ፣ማህበረሰቡ በዉድድሮች እንዲሳተፉ በማድረግ ረገድ ከፍተኛ ዉጤት ማምጣትና አካባቢዉን የበለጠ በማስተዋወቅ ረገድ ትልቅ ዉጤት አምጥቷል።

ሐምሌ 14/2016 ዓ.ም ለ4ኛዉ ዙር በወልቂጤ ከተማ የሚካሄደው ውድድር በርካቶች የሚሳተፉበትም እንደሆነም ተናግረዉ ማህበረሰቡና ወጣቶች በዉድድሩ መሳተፍ እንዳለባቸዉም ተናግረዉ ለዉድድሩ ስኬት አመራሮችም እርስ በእርስ በመነጋገር የድርሻቸዉን የሚወጡ እንደሆነም አመላክተዉ ሩጫዉ ስኬታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በተገቢዉ ማከናወን እንደሚገባም ተናግረዋል።

የዘንድሮዉ የኬሮድ ታላቁ ሩጫ በወልቂጤ ከተማ እንደሚካሄድ ሰሞኑን በተለያዩ ሚዲያዎች መግለጫ መስጠታቸዉም አስታዉሰዉ በቀጣይ ቀናቶች የሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካላቶች በተገኙበት በወልቂጤ ከተማ ሩጫዉን አስመልክተዉ መግላጫ እንደሚሰጡም ታዉቋል።

የዘንድሮዉ የኬሮድ ታላቁ የ15 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ከፍተኛ ሽልማት የተዘጋጀበት እንደሆነም አመላክተዋል።

በዉይይቱ የተገኙ የዞኑና የወልቂጤ ከተማ አመራሮች በሰጡት አስተያየት ዉድድሩ በስኬት እንዲጠናቀቅ በየትኛዉም ዘርፍ በትኩረት እንደሚሰራም አመላክተዉ ማህበረሰቡ የአካባቢዉን ሰላም በማስጠበቅ ረገድ ቀደም ሲል የነበረዉ ባህል ማስቀጠል በዉድድሩ መሳተፍም እንዳለበትም ተናግረዋል።

ወጣቶች ስፖርታዊዉ ዉድድሩ የበለጠ በማነቃነቅ በኩል የበኩላቸዉን መወጣት እንዳለባቸዉና ለዉድድር ስኬት መስራት ይኖርባቸዋል በሚል ተናግረዋል።

በዉይይቱ የጉራጌ ዞን አስተዳደር ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ደሳለኝ ፈቀደ ፣የዞኑ ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ሀላፊ አቶ ፈይሰል ሀሰን ፣የዞኑ ባህል ቱሪዝም ሀላፊ ወይዘሮ መሰረት አመርጋ ፣የዞኑ ሰላምና ጸጥታ ሀላፊ አቶ የህያ ሱልጣን ፣የዞኑ መንግስት ኮሚኒኬሽን ሀላፊ አቶ ሀዲሞ ሀሰን የወልቂጤ ከተማ ከንቲባ አቶ እንዳለ ስጦታዉ እንዲሁም የወጣቶችና ስፖርት ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሞሳ አብራር፣ የኬሮድ ታላቁ ሩጫ መስራችና አስተባባሪዎች ተገኝተዋል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *