ለ5ኛ ዙር ለመከላከያ ሠራዊት ከ43 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የደረቅ ስንቅ ድጋፍ ማድረጉን የጉራጌ ዞን አስተዳደር አስታወቀ።

የዞኑ ህዝብ ለመከላከያ ሠራዊት እያደረገ ያለው ድጋፍ ከፍተኛ መሆኑን ተጠቁሟል።

የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሀመድ ጀማል ድጋፋን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ ህብረተሰቡ ከመንግስትና ከመከላከያ ሰራዊት ጎን በመቆም ደጀንነቱን በተግባር እያረጋገጠ ይገኛል ብለዋል።

በዚህም ለ5ኛ ዙር የዞኑ ህዝብ 43 ሚሊዮን 170 ሺህ ብር የሚገመት በሶ 2ሺህ 7መቶ 38 ኩታል እና ስኳር 300 ኩታል ስንቅ ለመከላከያ ሰራዊት እንዲሁም በጦርነቱ ምክንያት ከአማራና አፋር ክልሎች ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ መደረጉን አቶ መሀመድ ገልጸዋል። ከዚህ ቀደም ከ105 ሚሊዮን ብር የአይነት ድጋፍ የተደረገ ሲሆን በአጠላይ ከ148 ሚሊዮን ብር በላይ የአይነት ድጋፍ መደረጉንም ተናግረዋል።

በሀገሪቱ እየተካሄደ ያለው ጦርነት ዘርፈ ብዙ እንደመሆኑ መጠን ህብረተሰቡ ለመከላከያ ሰራዊት እያደረገ ካለው ድጋፍ ጎን ለጎን የአካባቢውን ሰላም እየጠበቀ በልማት ስራ ከፍተኛ ተሳትፎ በማድረግ የበጋ መስኖ ስንዴ ከ2 ሺህ 1 መቶ ሄክታር መሬት በላይ ለማልማት ታቅዶ እየተሰራ እንደሚገኝ ዋና አስተዳዳሪው ተናግረዋል።

በዞኑ ከቁሳዊ ድጋፍ በተጨማሪ ከ1ሺህ በላይ ወጣቶች ወደ ግንባር በመዝመት ከመከላከያ ሰራዊት ጋር እየተዋደቁ ይገኛሉ ያሉት አቶ መሀመድ ጀማል በቀጣይ 40 አመራሮችና 20 ሃኪሞች ወደ ግንባር ለመዝመት በዝግጅት ላይ የሚገኙ ሲሆን ህብረተሰቡ ለመከላከያ ሰራዊት እና በጦርነቱ ሳቢያ በአማራና በአፋር ክልሎች የተፈናቀሉ ወገኖች ለመደገፍ የሚያደርገውን ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

በስንቅ ዝግጅቱ ሲሳተፋ ያገኘናቸው አንዳንድ የዞኑ ነዋሪዎች በሰጡት አስተያየት ለ5ኛ ዙር እየተደረገ ባለው ድጋፍ ከጉሊት ነጋዴዎች ጀምሮ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች የተሳተፋበት መሆኑን ጠቁመው አስፈላጊ ከሆነ እስከ ግንባር ድረስ እንደሚዘምቱ ተናግረዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

  • አካባቢህን ጠብቅ!
  • ወደ ግንባር ዝመት!
  • መከላከያን ደግፍ!

በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *