ለ1 ወር ከ12 ቀናት የሚቆይና ከ3 መቶ 50 በላይ ስፓርተኞች የሚሳተፉበት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን የ2014 ዓመተ ምህረት የወንዶች 1ኛ ሊግ 2ኛ ዙር የእግር ኳስ ውድድር በወልቂጤ ከተማ ዛሬ መካሄድ ጀመረ።

ውድድሩ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ከጉራጌ ዞንና ከወልቂጤ ከተማ ባህል ቱሪዝምና ስፓርት ጽ/ቤት የተውጣጡ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና እንግዶች ተገኝተው አስጀምረዋል

የወልቂጤ ከተማ ባህል ቱሪዝምና ስፓርት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ እፀገነት ፈቃዱ ለመላው ስፓርተኞችና ደጋፊዎች ሰላም ወዳድና እንግዳ አክባሪ ወደ ሆነው ወደ ጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ እንኳን በሰላም መጣችሁ ብለዋል።

ዛሬ በተጀመረው የእግር ኳስ ውድድር 11 ክለቦች እንደሚሳተፉና ከ350 በላይ ስፓርተኞች እንዲሁም በርካታ ደጋፊዎች ወደ ወልቂጤ ከተማ እንደጉቡ የገለፁት ወ/ሮ እፀገነት ፈቃዱ ውድድሩ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ 1 ወር ከ12 ቀናት የሚፈጅ መሆኑ ገልፀዋል።

በመሆኑም ሰላም ወዳድ፣ ታታሪ፣ እንግዳ ተቀባዩ የወልቂጤ ከተማ ህዝብ ያለምንም ዋጋ ጭማሪ ስፓርተኞችን ተቀብሎ ማስተናግድ እንዳለባቸው ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

የፀጥታው መዋቅርም የህዝቡን ደህንነትና ሰላም ከማስጠበቁ ጎን ለጎን ውድድሩ በሰላም ተጀምሮ እስቂጠናቀቅ ድረስ እያደረገው ያለው አስተዋጽኦ ከመቼውም ጊዜ በተሻለ አጠናክሮ መሄድ እንዳለበት ተናግረዋል።

ወ/ሮ እፀገነት ፈቃዱ አክለውም መላው የውድድሩ ተሳታፊዎች እና ደጋፊዎች ስፓርታዊ ጨዋነት በተላበሰ መልኩ መንቀሳቀስ እንዳለባቸውም ተናግረዋል።

የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፓርት መምሪያ ኃላፊ አቶ አወል ጅማቶ ውድድሩን ሲያስጀምሩ እንደገለፁት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን የ2014 የወንዶች 1ኛ ሊግ 2ኛ ዙር ውድድር በጉራጌ ዞን በወልቂጤ ከተማ እንዲካሄድ በማድረጉ የተሰማቸውን ደስታ ገልፀው በዞኑ አስተዳደርና ህዝብ ስም ምስጋናቸው አቅርበዋል።

ውድድሩ ወዳጅነት፣ መተባበርን፣ ሠላምና የህዝብ ለህዝብ አንድነትን ይበልጥ የሚያጠናክር በመሆኑ ከፍተኛ ፋይዳ አለው ብለዋለሰ።

አቶ አወል አክለውም ወደ ዞኑ ዋና ከተማ ወልቂጤ የመጡ የስፓርት ሉኡካን ቡድኖች ውድድራቸውን አጠናቀው እስኪሄዱ ድረስ የሚገጥማቸው ማንኛውም ችግሮች ካሉ አቅም በሚፈቅደው ሁሉ ትብብር እንደሚያደርጉ ገልፀዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡

Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *