== ለጉራጌ ዞን አትሌቶች የወጣ የጥሪ ማስታወቂያ ==

የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፓርት መምሪያ ተተኪ አትሌቶችን ለማፍራት በዘቢዳር አትሌቲክስ ክለብ ማሰልጠኛ ማዕከል በማስገባት ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።

በመሆኑም ዘቢዳር አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል ገብቶ መሰልጠን የምትፈልጉ በጉራጌ ዞን የምትገኙ አትሌቶች ቅዳሜ ማለትም የካቲት 12/2014 ዓ/ም ከጠዋቱ 2:00 ወልቂጤ ከተማ ስታዲየም በመገኘት የመግቢያ ውድድር(cuper test) እንድታደርጉ የጉራጌ ዞን ወጣቶች ስፓርት መምሪያ ጥሪውን ያስተላልፋል።

ማሳሰቢያ:- ለመወዳደር የምትመጡ አትሌቶች በተባለው ሰዓትና ቦታ መገኘት እንድትችሉ ከእሩቅ የምትመጡ አርብ ማለትም በ11/ 06/2014 ዓ/ም ወልቂጤ ገብታችሁ እንድታድሩ መምሪያው ያሳስባል።

                የጉራጌ  ዞን ወጣቶች ስፓርት መምሪያ
                                   ወልቂጤ 
                          የካቲት 10/062014 

   === አካባቢህን ጠብቅ!   ====
  ==== ወደ ግንባር ዝመት!  ====
  ==== መከላከያን ደግፍ!   ====

በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *