አሁን ሀገራችን የገጠማትን ጦርነት በውስጥ የጥፋት ቡድኖች ብቻ እንዳልሆነ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ብስራት ገብሩ ገልፀው ይህንን ጫና ለመቋቋም የወረዳው ማህበረሰብ ሁሉ አቀፍ ድጋፍ እያደረገ ይገኛል ብለዋል ፡፡
ለጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ለ4ተኛ ዙር ድጋፍ ለማድረግ ቅድመ ዝግጀት በማድረግ ላይ መሆኑ ተናግረዋል፡፡
በወረዳው የሀገር ሰላም ለማስከበር ግንባር ላይ ለሚገኙ ለዘማች ቤተሰቦች በምርት አሰባሰብና በሌሎችም ድጋፍ መደረጉ የተናገሩት ዋና አስተዳዳሪው ሀገራችን ሰላሟን እስኪረጋገጥ ድረስ የወረዳው ማህበረሰብ ከሞራል እስከ ግንባር በመሄድ ድጋፍ ለማድረግ እያሳየ ላለው ቁርጠኝነት ምስጋናቸው አቅርበዋል፡፡
ሌላው ደግሞ የወረዳው የመንግስት ረዳት ተጠሪ የሆኑት አቶ መቅሱድ ጀማል እንደገለፁት ለጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት በወረዳ ደረጃ ለ4ተኛ ዙር ድጋፍ ለማድረግ ስንቅ በማዘጋጀት ላይ መሆኑ ተናግረዋል፡፡
ለሀገር ሰላም ሂይወቱ መስዋአት እያደረገ ላለው ለጀግናው የሀገር መከላኪያ ሰራዊት የወረዳው ማህበረሰብ አጋርነቱ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠይቀዋል፡፡
በወረዳዉ ከዚህ በፊት ለሀገር ለመከለከያ ሰራዊት ድጋፍ መደረጉ በመግለጽ ድጋፉ ሲደረግ የሴቶች ተሳታፎ ከፍተኛ እንደነበር ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የሚላከዉን ስንቅ ሲያዘጋጁ የነበሩ ሴቶች ገልጸዋል፡፡
አሁንም ከ4 መቶ ሺህ ብር በላይ የሚሆን በሶ እያዘጋጁ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ አከለዉም ለጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት አጋርነታቸዉ በሞራል፤ በስንቅ ፤በገንዘብ እንዲሁም እስከ ግንባር በመሄድ ድጋፋችን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል ሲል መረጃው ያደረሰን የሙህር አክሊል ወረዳ የመንግስት ኮሚዩኒኬሸን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx