ለዜጎች የክህሎት መር ስልጠናዎችን በመስጠት በሀገር ውጭና በሀገር ውስጥ የስራ እድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየተሰራ መሆኑ የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ቢሮ አስታወቀ።


ለዜጎች የክህሎት መር ስልጠናዎችን በመስጠት በሀገር ውጭና በሀገር ውስጥ የስራ እድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየተሰራ መሆኑ የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ቢሮ አስታወቀ።

የጉራጌ ዞን ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና መምሪያ የእስካሁኑ እቅድ አፈጻጸም፣ለቀጣይ ስራዎች የንቅናቄና ወደ አረብ ሀገራት በስራ ለሚሰማሩ ዜጎች የክህሎት መርህ ስልጠና ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በወልቂጤ ከተማ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሂዷል።

የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ቢሮ ኃላፊ አቶ ቶፊቅ ጅኋር እንዳሉት የቴክኒክና ሙያ ተቋሟቶች ስራ ፈላጊ ዜጎችን በማስቀረት ስራ ፈጣሪ ወጣቶችን ማፍራት ዋና ተግባራቸው ነው።

በክልሉ 27 ሺ የሚሆኑ ዜጎች የውጭ ሀገር የስራ ስምሪት እድል ስልጠና ወስደው ወደ ውጭ ሀገር ሂደው በአግባቡ ስራቸው እየሰሩ ነው ያሉት አቶ ቶፊቅ ይህንን ስራ አጠናክሮ በማስቀጠል ዜጎች የተሻለ ኢኮኖሚ እንዲኖራቸው በትኩረት ይሰራል ነው ያሉት።

ለዜጎች የክህሎት መርህ ስልጠናዎችን በመስጠት በሀገር ውጭና በሀገር ውስጥ የስራ እድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ የተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

የጉራጌ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ እና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አበራ ወንድሙ እንደገለፁት ኮሌጆች ወቅቱን የሚመጥን ስራ ለመስራት ችግሮቻቸው በመለየት በንቅናቄ መፍታት ያስፈልጋል ነው ያሉት።

አክለውም ኮሌጆች የኢኮኖሚ አቅማቸው ለማሳደግ በግብርናና በመሰል ተግባራት በመሰማራት ሀብት ማፍራት እንደሚጠበቅባቸው እና ውጭ ሀገር ለሚሄዱ ዜጎች ደግሞ ሰልጥነው እንዲሄዱ የግንዛቤ ስራ መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

የጉራጌ ዞን ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና መምሪያ ኃላፊ አቶ መስፍን ስርግማ በበከላቸው ዜጎች ከስራ ፈላጊነት ወጥተው ስራ ፈጠሪ በመሆን ኑሮዋቸው ለማሻሻል በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አስገንዝበዋል።

ሰልጠኞች ደግሞ ያገኙት የክህሎት መርህ ስልጠና ወደ ተግባር በመቀየር ተጠቃሚነታቸውን ማረጋገጥ እንደሚገባ የገለጹት አቶ መስፍን አብዛኛው የዞኑ ኮሌጆች ከወረቀት ተኮር ስራ ወጥተው ወደ ቴክኖሎጂው እያደጉ መሆኑን አመላክተዋል።

ኮሌጆች የህብረተቡ ችግር የሚፈቱ የቴክኖሎጂ ስራዎችን በመስራት እና በስራ ፈጠራውም የተሻለ ውጤት እንዲኖር እየተሰራ መሆኑን የገለጹት አቶ መስፍን እነዚህን የሚያግዙ ስልጠናዎችም እየተሰጡ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

የወልቂጤ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ ኸይሩ አህመዲን እንዳሉት በአጭርና በርቀት በርካታ ዜጎች እየሰለጠኑ ሲሆን ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመሆን በማኑፋክቸሪንግ፣በአገልግሎት ዘርፍ፣ በኢንተርፕራይዝና በሌሎችም ዘርፍ ስልጠናዎች ተሰጥተው ወደ ተግባር እያስገቡ እንደሆነ አመላክተዋል።

ለአብነትም በውጭ ሀገር ስራ ስምሪት እድል ደግሞ ከ12 ሺ በላይ ዜጎች ስልጠና እየሰጠን ነው ያሉት አቶ ኸይሩ ስልጠናው በቤት ውስጥ አያያዝ፣በህጻናት እንክብካቤ፣በምግብ ዝግጅትና በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችም እንደሚያካትት አብራርተዋል።

በውይይቱ የተሳተፉ አካላት እንዳሉት ዜጎች በሀገር ውስጣና በሀገር ዉጪ የስራ እድል በመፍጠር በተፈጠረላቸው የስራ እድልም ፍትሀዊ ጥቅም እንዲያገኙና እንግልት እንዳይደርስባቸው እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ገልጸዋል።

ዜጎች የክህሎት መር ስራ እንዲሰሩ እና ብቁ እና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ስልጠናዎች ማዘጋጀትና በስልጠናዎችም በአግባቡ መጠቀም እንዳለባቸው ተናግረዋል።

የቦርድ ስብሰባዎችን በወቅቱ ማካሄድና ከቅበላ አንጻር የበለጠ ሊሰራበት ይገባል ብለዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *