ለአፍታም ለህይወቱ ሳይሳሳ ለሀገር መከታ የሆነው መከላከያ ሰራዊታችን በሁሉም የሀገራችን ክፍሎች ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዉያን የተፈጥሮና ሰዉ ሰራሽ አደጋ ባጋጠማት ጊዜ ሁሉ ለህዝቡ ቀድሞ የሚደርስና የሀገር ባለዉለታም እንደሆነም የጉራጌ ዘን ዋና አስተዳዳሪ አስታወቁ።

መከላከያ ሰራዊታችን ኢትዮጵያዊነታችን በሚል የቡታጅራ ከተማ ነዋሪዎች ታላቅ የድጋፍ ሰልፍ አካሄዱ።

የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ በድጋፍ ሰልፉ ተገኝተዉ ባስተላለፉት መልዕክት የሀገር መከላከያ ሰራዊታችን በኢትዮጵያ መንግስት ግንባታ ዉስጥ የማይተካ ታሪካዊ ሚና የተጫወተና ጠንካራ ባለዉለታ ነዉ።

ሀገራችን ኢትዮጵያ በዉጭ ወራሪ ሀይሎች እንዳትደፈር በዱር በገደሉ ተዋድቆ ክብራችንና ሉአላዊነታችን ያስከበረና እኛ ኢትዮጵያዉያ በአለም አደባባይ አንገታችን ቀና አድርገን እንድንኖር ዉድ መሰዋዕትነት ከፍሎልናል ብለዋል።

መከላከያ ሰራዊታችን በሁሉም የሀገራችን ክፍሎች ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዉያን የተፈጥሮና ሰዉ ሰራሽ አደጋ ባጋጠማት ጊዜ ሁሉ ለህዝቡ ቀድሞ የሚደርስና የሀገር ባለዉለታም ነዉ ብለዋል።

የዉጭና የዉስጥ ጠላቶች ተቀናጅተዉ ኢትዮጵያ ለማፈራረስና ለማዋረድ በዘመቱበት ጊዜ ሁሉ በኢትዮጵያ አንድነትና በፍጹም ጀግንነት ተዋድቆ የህይወትና የአካል መሰዋዕትነት ከፍሎ ሀገራችን ከብተናና ከመዋረድ ያተረፈ እንደሆነም ጠቅሰዋል።

የትኛዉም አይነት ጽንፈኝነት የሁሉም ኢትዮጵያዉያን የጋራ ጠላት ስለሆነ ሁላችንም ተባብረን ልናመክነዉ ይገባል ብለዉ ጽንፈኝነት ህብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትና የኢትዮጵያዊ አንድነትን ጸር እንደሆነም አመላክተዋል።

የቡታጅራ ከተማ ከንቲባ አቶ ነስሩ ጀማል እንዳሉት እኛ ኢትዮጵያን በሀዘንም ይሁን በደስታ ፣በመከራ ጊዜያትን እየተጋገዝን ፣ እየተደጋገፍን ፣ ይቅር እየተባባልን እየተቻቻልን ያጠፋዉን እየገጸስን የጎደለዉን እየሞላን ተቻችለንና ተከባብረን በፍቅርና በወንድማማችነት የዘለቅን ኩሩ ህዝቦች ነን።

ከሚያለያዩን ነገሮች ይልቅ አንድ የሚያደርጉን ነገሮች ስለሚበልጥ በደምና በስጋ የተገመደ ከብረት የጠነከረና ለዘመናት የዘለቀ የአብሮነት ዕሴት ያለን ድንቅ ህዝቦች ን ብለዋል።

ለሀገር ህልዉና በየ በረሃዉ ዘብ ለቆመዉ የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊታችን ያለንን ሁለንተናዊ አጋርነት አሁንም አጠናክሮ በመቀጠል ደጀንነታችንን በተግባር ከማረጋገጥ ባሻገር የአካባቢዉና የከተማዉ ሰላም ማህበረሰቡ ከጸጥታ አካላቶች ጋር ተቀናጅተዉ መስራት እንዳለበትም አብራርተዋል።

የጉራጌ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ሀላፊና የኢዜማ ፓርቲ ሀላፊ አቶ ደምስስ ገብሬ በድጋፍ ሰልፉ ተገኝተዉ እንዳሉት የሀገር መከላከያ ሰራዊት የአንድን ብሔር ፣የአንድን ሐይማኖት እንዲሁም አንድ አካባቢ ወግኖ ሳይሆን ፍጹም የሆነ ኢትዮጵያዊ ዜግነት ተላብሶ መላዉ የሀገራችን ህዝቦች በእኩል የሚያይና ዱር እያደረ ነብሱን የሚሰጥ እንደሆነም አመላክተዋል።

የዉስጥ ሰላማችን ለማደፍረስ የሚጥሩ ዜጎች በገዛ ሀገራቸዉ እየገደሉና እያፈናቀሉ ያሉትን ጽንፈኞችን ልካቸዉን እንዲያስገባልን ከጎኑ መቆም እንደሚገባም አብራርተዋል።

በድጋፍ ሰልፉ የተገኙ አንዳንድ የቡታጅራ ከተማ ነዋሪዎች በሰጡት አስተያየት ለሀገር ክብርና ህልዉና እየተዋደቀ ለሚገኘዉ የመከላከያ ሰራዊት መደገፍ እንደሚገባና ጽንፈኞች የሁሉም ኢትዮጵያዉያ ጠላቶች እንደሆኑም ተናግረዋል ሲል የዘገበዉ የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ነዉ።።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *