ለአካባቢው ማህበረሰብ ችግር ፈቺ አዳዲስ ቴክኖሎጂ በመፍጠርና በማሻሻል ውጤታማ የሆኑ ስራ እየሠራ መሆኑን የአረቅጥ ከተማ ኮንስትራክሽንና ኢንደስትሪያል ኮሌጅ አስታወቀ።

ነሀሴ 21/2014

ለአካባቢው ማህበረሰብ ችግር ፈቺ አዳዲስ ቴክኖሎጂ በመፍጠርና በማሻሻል ውጤታማ የሆኑ ስራ እየሠራ መሆኑን የአረቅጥ ከተማ ኮንስትራክሽንና ኢንደስትሪያል ኮሌጅ አስታወቀ።

በኮሌጁ በሰዓት ከ 70 ኩንታል በላይ ገብስ መውቃት የሚችል ቴክኖሎጂ በመፍጠር ለኢንተርፕራይዞች ማሸጋገር መቻሉም ተጠቁሟል።

ኮሌጁ ማህበራዊ ሀላፊነቱ ለመወጣት ማህበረሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርግ የተለያዩ የበጎ ፈቃድ ስራ እየሰራ ነዉ ።

ሀገሪቱ ከግብርና መር ወደ ኢንደስትሪዉ ለመሸጋገር እያደረገችዉ ባለዉ ጥረት የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጅ የአንበሳዉን ድርሻ እየተወጡ እንደሆነም ይታወቃል።

የአረቅጥ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ዲን አቶ ሚፍታ በደዊ እንዳሉት በቴክኒክና ሙያ ተቋማትና ኮሌጆች የሰለጠነና የበቃ የሰዉ ሀይል በማፍራት ወደ ኢንዱትስሪ ለማሸጋገር የሚደረገው ን ጥረት ዉጤታማ የማድረግ ስራ እየተሰራ መሆኑም አስረድተዋል።

በኮሌጁ ማህበረሰቡን የሚጠቅሙ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን በመፍጠርና መቶ ፐርሰንት በመቅዳትት በማሻሻል ለኢንተርፕራይዞች የማሸጋገር ስራ እየተሰራ እንደሆነም አመላክተዋል።

በአጫጭር በመካከለኛና በዝቅተኛ የሰለጠነ የሰዉ ሀይል ለማፍራት በትኩረት እየተሰራ መሆኑም የተናገሩት የኮሌጁ ዲን በአምና ደረጃ 545 ለሚሆኑ ዜጎች በተለያዩ ዘርፈፎች የአጫጭር ስልጠና መስጠት መቻሉም አብራርተዋል።

ከነዚህም ሰልጣኞች መከካል 248 ሰልጣኞች የብቃት መመዘኛ ፈተና የወሰዱ ሲሆን 240 ሰልጣኞች የብቃት መመዘኛ ፈተናዉም ማለፍ እንደቻሉም አስታዉሰዋል።

የአካባቢው ማህበረሰብ ችግር በጥናት በመለየት ለበጋ መስኖ ስንዴ ውሃ ማጠጫ ማሽንና በሰዓት ከ 70 ኩንታል በላይ ገብስ መውቃት የሚችል ማሸን በመፍጠር ውጤታማነታቸውን በማረጋገጥ ለኢንተርፕራየ ማስተላለፍ መቻሉን ገልጸዋል ።

የተሻሻለ አሰራር በመጠቀም ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ እንዲችሉ በተለያዩ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ከአንድ ሺህ በላይ ኢንተርፕራይዞች ድጋፍ መደረጉም ገልፀዋል ።

በየሴክተሩ በዝቅተኛ ደሞዝ ለሚሰሩ እናቶች ነፃ የትምህርት እድል ከሴቶችና ህፃናት ፅህፈት ቤት ጋር በመተባበር እየተሰጠ ነዉ ያሉት ዲኑ በደረጃ አንድና ሁለት ስልጠናቸውን ያጠናቀቁ ሲሆን በቀጣይ በደረጃ ሶስትና አራት ትምህርታቸውን ይቀጥላሉ ብለዋል።

ማህበራዊ ሀላፊነቱን ለመወጣት በዓምና ደረጃ ለ10 ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስና፣ለአንድ ትምህርት ቤት ለመማር ማስተማር ስራ የሚረዱ ቁሳቁስ ማበርከታቸውን አስታዉሰዉ በቀጣይ የትምህርት ዘመን ለአንድ ትምህረት ቤት የተለያዩ ቁሳቁስ ለማበርከት መዘጋጀቱን ተናግረዋል ።

በአረንጓዴ ኢኮኖሚ አሻራ እውን ለማድረግ በዘንድሮ ደረጃ ከአንድ ሺህ በላይ የፍራፍሬ ፣የጥላ ዛፎችና የተለያዩ ጠቀሜታ ያላቸውን ሀገር በቀል ችግኞችን መተከላቸውን የገለፁት የኮሌጁ ዲን የተተከሉትን ችግኞች ተገቢውን የእንክብካቤ ስራ በመሠራቱ ከ90 ፐርሰንት በላይ ለማፅደቅ እየተሰራ እንደሆነም አብራርተዋል።

ኮሌጁ እየገጠመው ያለው የበጀት ችግር ለመቅረፍ የውስጥ ገቢውን ለማሳደግ ፕሮጀክት ፕሮፖዛል በማዘጋጀት ከወረዳው ባገኘው የእርሻ መሬት ስንዴ በማምረት ለቢሮና ለመማር ማስተማር የሚረዱ ቁሳቁስ የማሟላት ስራ እየተሠራ ነው ብለዋል።
በቀጣይ የተማሪ ቅበላ ለማሳደግ በወረዳው በሚገኙ የ2ኛ ደረጃ ትምህርቶች ርዕሰ መምህራን የሳይንስና ቴክኖሎጂ ክበብ ተጠሪ መምህራን ጋር የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት መደረጉን ገልፀዋል ።
በኮሌጁ የሰርቬ ትምህርት አሰልጣኝ ዳዊት ምትኩ በበኩላቸዉ በአጫጭርና በመደበኛው ክፍለ ጊዜ የአካባቢው ማህበረሰብ ጊዜና ጉልበት የሚቆጥቡ እንዲሁም ምርትና ምርታማነት የሚያሳድጉ ቴክኖሎጂ ለመፍጠርና ለማሻሻል በትኩረት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል ።

= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36CxQ
Twitter:- https://4pvf.short.gy/bTJNNn

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *