ለአርሶአደሩ የገብያ ትስስር በመፍጠርና ያመረተዉን ምርት በመረከብ ተጠቃሚነታቸዉ ለማረጋገጥ እየሰራ እንደሆነም ዋልታ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን አስታወቀ።

ዋልታ የገበሬዎች ኃ./ስራ ዩኒየን 18ኛው ጠቅላላ ዓመታዊ ጉባኤውን የማህበሩ አባላቶች በተገኙበት በቡታጅራ ከተማ አካሄዷል።

ዩኒየኑ በ521 ሺህ ብር መነሻ ካፒታል ተነስቶ ዛሬ ላይ ከ20 ሚሊዮን ብር በላይ ማድረስ ችሏል።

በጉባኤው ላይ ተገኝተው የ2014 በጀት ዓመት የዩኒየኑ የስራ እንቅስቃሴ ለአባላቱና ለተሳታፊዎች ሪፖርት ያቀረቡት የዋልታ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየኑ ስራ አስኪሄጅ አቶ ወልዴ ቱርፎ እንደገለፁት በዩኒየኑ የአርሶአደሩ ምርትና ምርታማነት ለማሳደግና የገቢ አቅማቸዉን ለማሻሻል በትኩረት እየሰራ ይገኛል።

ዩኒየኑ ስር 31 መሰረታዊ ማህበራትና 10 ሺህ አባላት እንዳሉት ተናግረዉ ዩኒየኑ በ521 ሺህ ብር መነሻ ካፒታል ተነስቶ ዛሬ ላይ ከ20 ሚሊዮን ብር በላይ ካፒታል ማስመዝገብ ባቻሉም አመላክተዋል።

ዩኒየኑ ለአርሶአደሩ የብድር አቅርቦት፣የምርት ማሳደጊያ ግብዓት እና ፀረ ተባይ መድኃኒቶች በወቅቱ እንዲያገኙ እያደረገ እንደሆነም አብራርተዋል።

ዩኒየኑ በዋናነት አርሶአደሩ ያመረቱትን ምርት በመረከብ ገበያ አፈላልጎ ምርትና ምርታማነትን እንዲያሳድጉ የበኩሉን ጥረት ከማድረጉም በላይ አርሶአደሩ የተሻለ ገቢ እንዲያገኙ የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ እንደሆነም ጠቁመዋል።

ዩኒየኑ በሰብል ጥራት ቁጥጥር፣በሰብል ግብይት እንቅስቃሴ፣በገንዘብ ብድር አቅርቦት አርሶ አደሩን ሲያግዝ እንደቆየ የገለፁት ስራ አስኪያሄጁ የሰብል ዋጋ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየናረ በመምጣቱ የታቀደውን ያህል ስኬት ለማስመዝገብ አለመቻሉን ገልፀዋል።

የዋልታ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን በ5 ወረዳዎች ውስጥ ለሚገኙ አርሶ አደሮች አገልግሎት እየሰጠ ሲሆን በሀገሪቱ የተከሰተውን የዋጋ ግሽበትን ከማረጋጋት አንፃር የራሱን ሚና እንዳለውም ጠቁመዋል።

በጉባኤው ላይ የዩኒየኑ ዓመታዊ የኦዲት ሪፖርት ቀርቦ አባላቱ በቀረበው ሪፖርትና የኦዲት ግኝቶች ላይ ውይይት በማድረግ የጋራ መግባባት ላይ ደርሰዋል ሲል የዘገበዉ የቡታጅራ መንግሥት ኮሚኒኬሽን ፅ/ቤት ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *