ለብቻዋ አንድ ትምህርት ቤት ከነ ሙሉ ቁሳቁሱ ገንብታ ለመንግስት ያስረከበች ” ጀግኒት ፡ ድንቅ ሴት “

ቀን 27/12/14

ለብቻዋ አንድ ትምህርት ቤት ከነ ሙሉ ቁሳቁሱ ገንብታ ለመንግስት ያስረከበች ” ጀግኒት ፡ ድንቅ ሴት “

የጉራጌ ባህላዊ ምግብ ዝግጅት አምባሳደሯ ዘነበች ታደሰ /ዮኸሚያ ክትፎ ባለቤት /
በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ ጉየና የስዋ ቀበሌ ዮጊያር አካባቢተወልዳ ያደገችው ወ/ሮ ዘነበች ታደሰ ህፅናት ትምህርት ፍለጋ ሩቅ መንገድ እንዳይጓዙ በአካባቢያቸው በቅርብ እርቀት እንዲማሩ የነበራት የልጅነት ህልሟ በእውኑ ያሳካች ድንቅ ሴት ናት ።

ወ/ሮ ዘነበች ይህ አርእያነት ያለው ተግባር ለማከናወን መነሻ ምክንያት የሆናት እንዲህ ስትል ነግራናለች :- በልጅነት እድሜዬ እንዲህ እንዳሁን የትምህርት ተቋማት ባልተስፋፉበት ዘመን ከ12 ኪ.ሜትር እርቀት ድረስ በመጓዝ በብዙ ውጣ ውረዶች ትምህርት የተማርኩበት ሁኔታ መቼም የማረሳው ነው ትላለች ።

ታዲያ በዚያን ጊዜ ለሀገር የሚጠቅሙ ጎበዝ ተማሪዎች በእርቀት ምክንያት ትምህርታቸውን አቋርጠው ወደ ከተማ የሄደበት ሁኔታ በማስታወስ ፈጣሪ በሰጠኝ ሀብት ” ዘነበች የታደሰ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ” በ2003ዓም ለመመስረት ችላለች ።

በ2014 ዓም የተሻሻለው የትምህርት ፖሊሲን በሚጠይቅ መስፈርት መሰረት ትምህርት ቤት ከነበረበት እስከ 4ኛ ወደ እስከ 6ኛ ክፍል ደረጃውን ለማሻሻል በ2.5ሚሊየን ብር ወጪ አሁንም ተጨማሪ 4 ደረጃቸውን የጠበቁ የመማሪያ ክፍሎች ገንብታለች ።
ከዚህ በተጨማሪ የግንባታ ሂደቱ 60% የደረሰው ቅድመ መደበኛ ክፍል ደረጃው በጠበቀ መልኩ እያስገነባችም ትገኛለች ።
ወ/ሮ ዘነበች ከዚህ በተጨማሪ ህልማቸው ገና ብዙ እንደሆነና የፈጣሪ ፍቃድ ከሆነም ብዙ እንደሚሰሩና ይገልፃሉ ።

የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህ የሆኑት አቶ ከበደ ዋርጋ ስለ ዘነበች ታደሰ ሲገልፁ ወ/ሮ ዘነበች ትምህርት ቤቱ ገንብተው ለመንግስት ብቻ አስረክበው የሄዱ ሳይሆን በየወቅቱ ትምህርት ቤቱ በመጎብኘት ለተማሪዎች የዓመት የትምህርት ቁሳቁስ ማለት እስክርብቶና ደብተር ገዝተው ከማበርከት በተጨማሪ ተማሪዎችን በመሰብሰብ የእሷ ተሞክሮ እያካፈለች ጎበዝ እና ነገ ተምረው ለሀገር እንዲጠቅሙ በመምከር እንዲሁም ትምህርት ቤቱ በየጊዜው የሚያስፈልጉ ነገሮች በቅርበት ሆኗ የምትከታተል ትልቆ ጀግና ሴት መሆኗን ይመሰክራሉ ።

የአካባቢው ነዋሪዎችና ተማሪዎች ወ/ሮ ዘነበች ባለሀብት ብቻ ሳትሆን መካሪ ፡ የተቸገረን ለጋሽ በዛ ትምህርት ቤት ሚከታተሉ ተማሪዎች ልክ እንደ ወለደቻቸው ልጆች በመከባከብ የተለየች እናት መሆኗና በአካባቢአቸውም የተለየ ቦታና ክብር እንዳላቸውም ያላቸው ክብርና ምስጋና ይገልፃሉ ።

የእዣ ወረዳ ትምህርት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ተጠምቀ በርጋ ሀገር ተረካቢ ትውልድ ለማፍራት ትምህርት ቤቶች የማይተካ ሚና ይጫወታሉ ብለዋል ።

ለዚህም የትምህርት ተደራሽነትና ጥራት ማሳደግ አስፈላጊ መሆኑንና እንደ ወረዳው በትምህርት ዘርፍም ህብረተሰቡ ከመንግስት ጋር በመተባበር በወረዳው በሁሉም ቀበሌዎች አንድና ከዚያ በላይ ትምህርት ቤቶች ተገንብተው ህብረተሰቡ በቅርብ እርቀት ልጁን እያስተማረ ይገኛልም ብለዋል ።

ይህም ሊሆን የቻለው በወረዳው እንደ ወ/ሮ ዘነበች ታደሰ ያሉት ለትውልድ የሚቆረቆሮ ማህበረሰቦች መኖራቸው ተከትሎ እንደሆነም ይናገራሉ ።

ወ/ሮ ዘነበች ትምህርት ቤቱ ለማሳደግ ያላቸው ጉጉት በቀላሉ የሚገለፅ አይደለም ያሉት አቶ ተጠምቀ በዚህም እንቅስቃሴአቸው የወረዳው መንግስት መምህር ቀጥሮ በመመደብ መፅሀፍ በማሟላትና ሌሎችም አስፈላጊውን ድጋፎች በተቻለው አቅም ለማገዝ ዝግጁም መሆኑን በመግልፅ ለወ/ሮ ዘነበች ያለውን ምስጋናሞ ገልፀዋል ።

ወ/ሮ ዘነበች ታደሰ በንግዱ ዘርፍ የተሰማሩ ሲሆን በአብዛኞች የታወቁበት በጉራጌ ባህላዊ ምግብ ዝጅት አዲስ አበባ 22አካባቢ ዮኸምያ ክትፎ ቤት ባለቤትም ናቸው ሲል የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ዘግቦታል።

ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36CxQ
Twitter:- https://4pvf.short.gy/bTJNNn

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *