ለበርካታ ዓመታት የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ሆኖ ሲነሳ የነበረው የመቆርቆር የንፁህ መጥጥ ውሃ ተደራሽነት ለማረጋገጥ እና ስራው ለማስጀመር ከጨረታ አሸናፊው ተቋራጭ ጋር ርክብክብ መካሄዱ የምሁር አክሊል ወረዳ አስተዳደር ገለፀ።

በምሁር አክሊል ወረዳ ስር ከሚገኙት ቀበሌዎች ውስጥ የመቆርቆር ቀበሌ የውሃ ችግር አንዱ መሆኑን እና የአካባቢው ማህብረሰብ የመልካም አስተዳደር ጥያቄ እንደ ነበረ የምሁር አክሊል ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ብስራት ገብሩ ገልፀዋል።

የወረዳው አስተዳደር ከዞን እና ከክልል ባለድርሻ አካለት ጋር በመወያየት የቀበሌውን የውሃ ችግር ከግንዛቤ በማስገባት ጥናት ሲያካሄድና በርካታ ስራዎች ሲያከናውን እንደነበር ገልፀዋል።

አቶ ብስራት አክለውም የችግሩ አሳሳቢነት በመረዳት በጥናቱ መሠረት ከዚህ በፊት ጥልቅ የከርሰ ምድር ውሃ ቁፋሮ መከናወኑ ጠቅሰው በበጀት እጥረት ለታለመለት አላማ ሳይውል ቀርቶ አሁን ላይ በአለም ባንክ የገንዘብ ምንጭነት በኢትዮጵያ የአፍሪካ ቀንድ የከርሰ ምድር ውሃ ዘላቂ ልማት ፕሮጀክት ባለቤትነት ለመገንባት የዞን የውሃና ማዕድን ኢነርጂ መመሪያ ኃላፊ፤ የጉራጌ ዞን የዋና አስተዳዳሪ አማካሪ እና የክልል የውሃ ፕሮጀክት ተዋካይ በተገኙበት የውሃ ፕሮጀክቱ አሸናፊ ለሆኑት ለአቶ ሺመልስ አለሙ ለጠቅላላ የስራ ተቋራጭ የስራ ርክብክብ መደረጉን ገልፅዋል።

የማህበረሰቡን የንፁህ መጠጥ ውሃ ችግር ለመቅረፍ እና ተቋራጩ በገባው ውል መሠረት እንዲያጠናቅቅ የአካባቢው ማህበረሰብ፣ ወረዳው፣ ዞኑ እንዲሁም ሌላውም በመቀናጀት ሊሰራ ይገባል ሲሉ የምሁር አክሊል ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የምሁር አክሊል ወረዳ የውሃና ማዕድን ኢነርጂ ፅ/ቤት ዋና ኃላፊ የሆኑት አቶ ወርቁ ርዳ የወረዳው የንፁህ የመጠጥ ውሃ ሽፋን 28.54% መሆኑን ገልፀው የንፁህ መጠጥ ውሃ ሽፋን ለማሻሻል የወረዳው መንግስት ትኩርት በመሰጠት እየስራ መሆኑን ገልፀዋል።

ከፍተኛ የውሃ ሽፋን ችግር ካለባቸው ቀበሌዎች የመቆርቆር ቀበሌ አንዱ መሆኑን አንስተው በአለም ባንክ የገንዘብ ምንጭ የሚሰራው የመቆርቆር ቀበሌ የውሃ ፕሮጀክት በመጀመሪያ ዙር ከ13 ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍል በ15 የውሃ ቦኖ ተጠቃሚ እንደሚያደርግ እና ወደ ፊት ጥናት በማድረግ ሌሎች ቀበሌዎች ተጠቃሚ ለማድረግ አሰከ 27 ቦኖዎች የማሰጠቀም አቅም እንዳለው ገልፀዋል።

የጉራጌ ዞን ውሃና ማዕድን ኢነርጂ መምሪያ ኃላፊ አቶ አየለ ፈቀደ እንደ ዞን የንጹህ መጠጥ ውሃ ችግር አለባቸው ተብሎ ከተለዩ ቦታዎች በምሁር አክሊል ወረዳ የመቆርቆር ቀበሌ አንዱ መሆኑንና ህዝቡ ለረጅም ጊዜ ሲያነሳው የነበረ ጥያቄ እንደነበር ተናግረው ወረዳው ከዞኑ ጋር በመናበብ ችግሩ ለመቅረፍ ጥናት ተደርጎ ጥልቅ የከርሰ ምድር ውሃ ቁፋሮ መደረጉን ተናግረዋል።

እንደሀላፊው ገለፃ የቀበሌው የመጠጥ ውሃ ችግር ለመቅረፍ ስራው የሚሰራው በኢፊድሪ መንግስት ሆርን ኦፍ አፍሪካ የከርሰ ምድር ውሃ ዘላቂ ልማት ፕሮጀክት አማካኝነት እንደሆነና የገንዘቡ ምንጭ የአለም ባንክ መሆኑን ጠቁመዋል።

በመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ ከ57ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ 15 ቦኖዎች ተገንብተው በአንድ አመት ውስጥ ተጠናቆ ለማህበረሰቡ ለማስጠቀም በትኩረት እንደሚሰራ አመላክተዋል።

ፕሮጀክቱ በምእራፍ ሁለት የውሃው ተደራሽነት ለማስፋፋት እንደሚሰራ በዚህም አራት ቀበሌዎች (ጭሬት እና መቆርቆር)ሙሉ በሙሉ እና (ዘናበነር እና አጣጥ)ቀበሌዎች በከፊሉ በማስጠቀም በሂደቱም ባጠቃላይ 42 ቦኖዎች በመገንባት የአካባቢው ማህበረሰብ የውሃ ችግር ይቀርፋል ተብሎ ይታመናል ብለዋል።

አቶ አየለ አክለው ፕሮጀክቱ ተገንብቶ ሲያበቃ ከማስፋፊያው ውጪ 13ሺህ የህብረተሰብ ክፍል ተጠቃሚ እንደሚያደርግ አመላክተው በተያዘለት የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቅ የአካባቢው ማህበረሰብ ሁለንተናዊ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

ዘገባው፦ የምሁር አክሊል ወረዳ የመንግስት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *