ለመስቀል በዓል ወደ ሀገር ቤት የገቡ እንግዶች ሲመለሱም ምቹ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲያገኙ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ የጉራጌ ዞን ትራንስፖርት እና መንገድ ልማት መምሪያ አስታወቀ።


ለመስቀል በዓል ወደ ሀገር ቤት የገቡ እንግዶች ሲመለሱም ምቹ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲያገኙ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ የጉራጌ ዞን ትራንስፖርት እና መንገድ ልማት መምሪያ አስታወቀ።
በአገኙት የትራንስፖርት አገልግሎት ደስተኛ መሆናቸው ያነጋገርናቸው ተሳፋሪዎች ገለጹ።

የጉራጌ ዞን ትራንስፖርት እና መንገድ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙራድ ከድር እንደገለፁት ጉራጌ የመስቀል በዓል በድምቀት የሚያከብረው እንደመሆኑ መጠን አረፋንም መነሻ በመድረግ ወቅቱን የሚመጥን ዝግጅት ተደርጓል።

በዓሉ ምክንያት በማድረግ ወደ ዞናችን የሚገቡ በርካታ ቱሪስቶች፣ተወላጆችና እንግዶች ወደ ዞናችን የሚገቡበት ነው ያሉት አቶ ሙራድ እነዚህ እንግዶች በሰላም ገብተው በሰላም እንዲወጡ ከኦሮሚያ ክልል እና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጋር የተሰራው ቅንጅታዊ ስራ ውጤት አስገኝቷል ብለዋል።

አክለውም ከዚህ በፊት የነበሩ የጸጥታ ችግሮችና ብዥታዎች፣የአደጋ ስጋቶች ፣የተሳፋሪ መጉላላት ፣ትርፍ መጫን እና ሌሎችም ማስቀረት መቻሉ አስገንዝበዋል።

በተለይ በኦሮሚያ ክክል በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን የተደረገው አቀባበልና እንክብካቤ የጉራጌ እና የኦሮሞ ህዝብ አንድነት፣ ወንድማማችነትንና አብሮነትን ያረጋገጠ እንደሆነ ኃላፊው አስገንዝበዋል ።

ለዚህም በተለይ በኦሮሚያ ክልል የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ትራንስፖርት እና መንገድ ልማት መምሪያ፣የገላን ክፍለ ከተማ፣ የሰበታ ክፍለ ከተማ፣ከመምሪያ እስከ ቀበሌ በዘርፋ ያሉ ባለሙያዎች እና የጸጥታ አካላት ጨምሮ ለተባባሪ አካላት ሁሉ ምስጋናቸው አስተላልፏል።

በመስቀል ወቅት ተሳፋሪው በሰላማዊና ያለ እንግልት የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲያገኝ እየተሰራ ያለው ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉ የተናገሩ ሲሆን ለዚህም ተመላሾች እንዳይጉላሉ ተጨማሪ መኪኖች ተመድበው ህብረተሰቡ ትርፍ ክፍያ ሳይከፍልና ሳይጉላላ ወደ ስራው በሰላም እየተመለሰ መሆኑን አብራርተዋል።

የመምሪያው ምክትልና የትራንስፖርት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ግሩም ወ/ሰንበት የተቀመጡ ህግና ደንቦች እንዳይጣሱና የማህበረሰቡ ጥሩ ስም እንዳይበላሽ በቅንጅት እየተሰራ መሆኑና ይህም ተጠናክሮ ይቀጥላል።

ከማህበራት ፣የስምሪት ሰራተኞች ፣ከዘርፉ ባለሙያዎች እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት የተሰራው ስራ ለማህበረሰቡ ቅሬታ መፍታት እየተቻለ መሆኑን ተናግረዋል።

ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርግ አሰራር በመዘርጋት ለአብነትም የኢ ቲኬቲንግ እና መናኸርያዎች የማዘመን ስራ ላይ የበለጠ ውጤታማ እያደረጉ ይገኛል ብለዋል አቶ ግሩም።

የጉራጌ ዞን ፖሊስ መምሪያ ዋና ኢንስፔክተር ገና ደገሙ እንዳሉት የመስቀል በአል በሰላም ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ድረስ ከአጎራባች ዞኖች የጸጥታ አካላት ጋር በቅንጅት ሲሰራ እንደነበር አስታውሰዋል

በዚህም ከአንድ አደጋ በስተቀር ምንም አይነት አደጋ አለመከሰቱ እና በዓሉ በሰላም መከበሩ ያስታወቁት ዋና ኢንስፔክተር ገና ደገሙ እንደ ዞንም የጸጥታ ስጋት ያለባቸው አካባቢዎች የጸጥታ አካላት እንዲመደቡ መደረጉ ጠቁመዋል።

ትርፍ በሚጭኑ፣ህዝብ የሚያጉላሉ ፣ከታሪፍ በላይ የሚያስከፍሉ የማይገባ ድርጊት በሚፈጽሙ አካላት ህጋዊ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑ በመገለጽ።

አቶ ጌታቸው ተዳሺና አቶ ታምሩ ወልዴ ሲሳፈሩ ያገኘናቸው ሲሆን የመስቀል በአል በሰላምና ያለ እንግልት እንድንጓዝ በተለይ ከአጎራባች ዞኖችና ከተማዎች የተሰራው ስራ አድንቀዋል።

በመሆኑም በአገኙት የትራንስፖርት አገልግሎት ደስተኛ መሆናቸው ተሳፋሪዎቹ የገለጹ ሲሆን አሁንም እንድ አንድ አሽከርካሪዎች ትርፍ የሚያስከፍሉ በመኖራቸው ጥብቅ ክትትል እንዲደረግባቸው ጠቁመዋል።

ህዝቡም ሲሳፈር የጋራ አስተሳሰብ በመያዝ ትርፍ ከመክፈልና ትርፍ ከመጫን እራሱን ሊቆጥብ ይገባል ብለዋል ሀሳብ ሰጪዎቹ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *