ለሐዋርያት ከተማ ልማት የምሁር አክሊል ወረዳ አመራሮች የአንድ ወር ደመወዛቸውን ለመስጠት ወሰኑ።

ነሀሴ 6/2014 ዓ.ም

ለሐዋርያት ከተማ ልማት የምሁር አክሊል ወረዳ አመራሮች የአንድ ወር ደመወዛቸውን ለመስጠት ወሰኑ።

የምሁር አክሊል ወረዳ ዋና ከተማ የሆነችው የሐዋርያት ከተማ ለማሳደግ ሁሉም ማህበረሰብ የበኩሉን አስተዋፅኦ ሊያደርግ እንደሚገባ የምሁር አክሊል ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ብስራት ገብሩ ገልፀዋል።

ጥያቄያችን በሰለጠነ መንገድ እየጠየቅን ልማታችንን ጎን ለጎን ማስቀጠል ይገባል። በዚህም በብዙ መልማት የሚጠበቅበት የወረዳችን ዋና ከተማ ሐዋርያት ለማልማት ሁሉም ወደ ልማት በመግባት የበኩሉን አሻራ በማስቀመጥ ሁለንተናዊ ብልፅግና ልናረጋግጥ ያስፈልጋል ብለዋል።

ቀጣይ ጊዜያቶች በጋራ በመሆን ለከተማችን ለውጥ መስራት እንደሚገባም የምሁር አክሊል ወረዳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰይፈ ይልማ ተናግረዋል።

በውይይቱም ፅ/ቤቱ በ2014 በጀት ዓመት በዋናነት ያከናወናቸው ተግባራቶች ቀርቦ ውይይት ተደርገዋል።

ፅ/ቤቱ 2015/ለ2016 በጀት ዓመት ሐዋርያት ከተማ የፈርጅ ለውጥ ተደርጎ ከተማ መስተዳድር እንዲሆን የእቅድ አካል አድርገን እየሰራን እንገኛለን ብለው በከተማው የሚሰሩ የመሰረተ ልማት ስራዎች ሁሉም የከተማው ማህበረሰብ የበኩሉን እንዲወጣ አሳስበዋል።

የውይይት ተሳታፊዎች በበኩላቸው ከተማው ለማልማት አመራሩ አርአያ ሊሆን እንደሚገባና በዘላቂነት እንዲለማ የማህበረሰቡና የተወላጆች ተሳትፎ ወሳኝ ነው ብለዋል።

በመጨረሻም በከተማው ለሚሰሩ ስራዎች የልማት፣የሀብት አሰባሰብ እና የሚዲያ ስራ ኮሚቴ በማዋቀር ውይይቱ ተጠናቋል ሲል መረጃው ያደረሰን የወረዳው መ/ኮ/ጉ/ፅ/ቤት ነው።

በረጃ ምጭነት ገፃችንን ስለምትከታተሉ እናመሰግናለን!
እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *