ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ለመቀነስ የስራ አጥ ዜጎች የስራ እድል ተፈጥሮላቸው የኢኮኖሚ ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉ የጉራጌ ዞን ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያው አስታውቋል።

ወጣቶች ከሀገር እንዳይሰደዱና ከስደት ለተመለሱት ከ2 ሚሊየን ብር በላይ መድቦ የስራ እድል መፍጠሩም ተጠቁሟል።

መምሪያው በእኖር ወረዳ ከስደት የተመለሱና ለስደት ተጋላጭ ሆነው የስራ እድል የተፈጠረላቸው ወጣቶች ያሉበት ሁኔታ ተዛዙሮ አይቷል።

የጉራጌ ዞን ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ሀላፊ ወይዘሮ አመተእሩፍ ሁሴን እንደገለጹት በዞኑ ከፍተኛ የሆነ የሰዎች ስደት ካለባቸው 10 ወረዳዎች አንዱ እኖር ወረዳ ሲሆን ጋሳዊዲ ቀበሌ ደግሞ የበለጠ ተጋላጭ አካባቢ ሆኖኗል።

ስደት የሚበዛው በኢኮኖሚ ችግር፣በግንዛቤ እጥረትና ያልተጨበጠ ተስፋ በመስጠት ሲሆን ችግሩ ለመቅረፍ የሚዲያ የአየር ሰአት በመግዛት ግንዛቤ የመፍጠር፣የስራ እድል የመፍጠር፣ ከሀይማኖት አባቶችና ከባለድርሻ አካላት ጋር ኮሚቴ ተዋቅሮ እየተሰራበት እንደሆነም ተናግረዋል።

ወይዘሮ አመተሩፍ አክለውም ፕሮጀክት ተቀርጾ በመሰራቱ ከአለም አቀፍ የፍልሰት ድርጅት በተገኘ 2 ሚሊየን ብር ደጋፍ ከስደት ተመላሽ የሆኑ 50 ወጣቶች በከብት ድለባና እርባታ፣በፍየል ድለባና እርባታ፣ እንዲሁሞ በዶሮ አርባታ ተሰማርተው ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚ እየሆኑ ይገኛሉ ብለዋል።

ወጣቶቹ የክህሎት ስልጠና በመስጠት ወደ ስራ ገብተዋል ያሉት ኃላፊዋ ቀጣይም የወጣቶቹ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚመለከታቸው ተቋም ሊደግፋቸው ይገባል ብለዋል።

ስራው ከጀመሩ አጭር ጊዜ ቢሆኑየንም ባሳዩት ለውጥ በየማህበራቸው ከ10 ሺ እሰከ 75 ሺ ብር መቆጠብ መቻላቸው የተናገሩት ወይዘሮ አመተሩፍ ስራው ውጤታማ እንዲሆን የሚመለከታቸው ተቋማት ድጋፍና ክትትል እንዲያደርጉ አሳስበዋል።

የእኖር ወረዳ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ጨዋነሽ ኢማም እንደገለጹት ያሉ ወጣቶች ለስደት እንዳይጋለጡና ከስደት የተመለሱት ደግሞ ከማህበረሰባቸው ተቀላቅለው ቤተሰባቸው እያገዙና እራሳቸው ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከሚመለከታቸው ተቋማት በመቀናጀት እየተሰራ ነው።

ይህም ወጣቶች በሀገራቸው ሰርተው መለወጥ እንደሚችሉ ማስተማሪያ መሆኑን ኃላፊዋ አመላክተዋል።

ወይዘሮ ዘይነባ ፈድሉና ወዘሪት ኒኢማ ሀጁ በጋሳዉዴ ቀበሌ ከአረብ ሀገር ተመላሾች ናቸው።በሰው ሀገር የሚደርስባቸው ግፍና መከራ በርትቶባቸው ወደ አካባቢያቸው ተመልሰው በተመቻቸላቸው የስራ እድል ተጠቃሚ መሆናቸው አስታውቋል።

ወጣት አብድል ሀሚድ ዲንሰፋና ወጣት አብድላ ፈድሉ በጋሳውዳ ቀበሌ የእድሉ ተጠቃሚ በመሆናቸው ከራሳቸው አልፈው ቤተሰባቸው መደገፍ መቻላቸውና በቀጣይም ስራቸው አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

።በመረጃ ምንጭነት ገፃችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!
= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *