ህዝበ ሙ ስሊሙ በረመዳን ወቅት ሲያከናውናቸው የነበሩ መልካም ተግባራት ከበዓሉ በኋላም አጠናክሮ ማስቀጠል እንዳለበት የጉራጌ ዞን እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት አስታወቀ።

ሚያዚያ 2/2016ዓ.ም
=============== ህዝበ ሙስሊሙ በረመዳን ወቅት ሲያከናውናቸው የነበሩ መልካም ተግባራት ከበዓሉ በኋላም አጠናክሮ ማስቀጠል እንዳለበት የጉራጌ ዞን እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት አስታወቀ።

በጉራጌ ዞን በወልቂጤ ከተማ 1445ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል በተለያዩ ሀይማኖታዊ ስርዓቶች በድምቀት ተከብሯል።

የጉራጌ ዞን እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ሰብሳቢ ኡስታዝ አባስ ያሲን በበዓሉ ወቅት እንዳሉት የኢድ ሰላት ከዚህ በፊት ከነበረው ይበልጥ በድምቀት በሰላም ተከብሯል።

ህዝበ ሙስሊሙ በረመዳን ወቅት በአብሮነት፣ በመተባበር፣ የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳት ያሳለፈውን መልካም ተግባር ከበዓሉ በኋላም አጠናክሮ ማስቀጠል እንዳለበት ገልጸዋል።

በሀገሪቱም ሆነ በዞኑ ያለውን አንጻራዊ ሰላም ቀጣይነት እንዲኖረው ህዝበ ሙስሊሙ ከመንግስት ጎን በመሆን የአካባቢው ሰላም ነቅቶ ሊጠብቅ እንደሚገባ ተናግረዋል።

አቶ መሀመድ አወል፣ አቶ ሸምሱ ሰማን እና አቶ አብድልሰመድ አብደላ የበዓሉ ተሳታፊዎች ሲሆኑ የኢድ ሰላት በድምቀት መከበሩን ገልጸዋል።

በከተማው የመጣው አንጻራዊ ሰላም ማህበረሰቡ ያለውን እሴቱን ተጠቅሞ ከመንግስት ጋር በመሆን ዘላቂ ሰላምና ልማት ለማረጋገጥ መስራት ይገባል ብለዋል።

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1445ኛው የኢድ አል ፈጥር በዓል አደረሳችሁ።

        ኢድ ሙባረክ!!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *