ህወሃት የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ለማዳከም በኢንዱስትሪዎች ላይ ያደረሰው ጉዳት ለማካካስ ኢንተርፕራይዞችን ማብቃትና ለወጣቶች የስራ እድል የመፍጠር ተግባር ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት መስራት እንዳለበት የጉራጌ ዞን አስተዳደር አስታወቀ።

ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች በሀገሪቱ የኢኮኖሚ የማህበራዊ ልማት ሽግግር ውስጥ ያላቸው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሰራበት እንደሚገባ የጉራጌ ዞን ኢንተርፕራይዝ እና ኢንድስትሪ ልማት መምርያ አስታወቀ።

የጉራጌ ዞን ስራ እድል ፈጠራና ኢንድስትሪ ልማት መምርያ የስራ እድል ፈጠራ ምክር ቤት በዛሬው እለት በወልቂጤ ከተማ የምክክር መድረክ አካሂዷል ።

የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሀመድ ጀማል በዚህ ወቅት እንዳሉት በዘርፉ የተሰማሩ ወጣቶች የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ በበጀት፣ በሰው ሀይል፣ በቁሳቁስና እና የክህሎት ስልጠና መስጠት ያስፈልጋል ብለዋል።

አቶ መሀመድ አክለውም የተደራጁ ኢንተርፕራይዞች ባሉበት አካባቢ የሚያስፈልጋቸው መሰረተ ልማቶች ሊሟላላቸው እና አቅማቸው የበለጠ ለማሳደግ በዞኑ ያሉ የግልና የመንግስት ተቋማት ማስተሳሰር እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።

በዘርፉ የሚሰሩ ተግባራት የበለጠ ለማጠናከር በጥራትና በጥንቃቄ ስራ አጥ ወጣቶችን መለየት እና በዘርፋ የሚሰሩ ስራዎች በመቀመር ለሌሎች ልምድ ልውውጥ እንዲሆን መስራት ያስፈልጋል ሲሉ ተናግዋል።

ህዋሃት በፈጠረው ጦርነት የወደሙ ኢንዱስትሪዎችን ለመተካት ኢንተርፕራይዞች ማብቃትና ለወጣቶችና ሴቶች የስራ እድል የመፍጠር ተግባር ልዩ ትኩረት ተደርጎ መስራት እንደሚያስፈልግ አቶ መሀመድ ተናግሯል።

የጉራጌ ዞን ኢንተርፕራይዝ እና ኢንድስትሪ ልማት መምርያ ኃላፊ አቶ አበበ አመርጋ እንደገለጹት ተቋሙ በገጠር እና በከተማ ተንሰራፍቶ የሚገኘው ድህነትና ስራ አጥነት ለማጥፋት መካከለኛ ገቢ ያለው ህብረተሰብ ለመፍጠር እየሰራ መሆኑን ጠቁመው ለዚህ ተግባር ብቻ ከ5 ሚሊየን ብር በላይ በጀት ተመድቧል ብለዋል።

በመሆኑም የስራ አጦች ቁጥር ለመቀነስ በዞኑ በሚሰሩ ስራዎች ኢንተርፕራይዞችን ያካተተ እና ስራ አጦችን አሳታፊ የሚያደርግ ስራ መሰራት እንደሚያስፈልግ ገልጸው ለአብነትም በዞኑ በሚወጡ ጨረታዎች ኢንተርፕራይዞችን ያካተተ እና የዞኑ ወጣቶችን ማሳተፍ ያለበት ደንብና መመሪያዎችን ማውጣትና ተጠቃሚ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።

አቶ አበበ አክለውም በየወረዳው ያሉ የወል መሬቶች ለወጣቶች እና ሴቶች በመስጠት በማእድን ፣በማኒፋክቸሪንግ ፣በመንገድ፣ በግብርና በሌሎችም የስራ መስኮች ማሰማራትና መከታተል እንዳለበት አሳስበዋል።

የተሰራጨው ብድር መመለስ ለሌሎች ወጣቶች የስራ መፍጠር ወሳኝነት አለው ያሉት አቶ አበበ አመርጋ በዚህ ሂደት ላይ ያለው የብድር አሰረጫጨትም በመረጃ የተደገፈ እና መስፈርቶችን ማቅለል አለበት ነው ያሉት።

ጥቃቅንና አንስተኛ ኢንተርፕራይዞች በሀገሪቱ የኢኮኖሚ የማህበራዊ ልማት ሽግግር ውስጥ ያላቸው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ሁሉም ባለድርሻ አካል በቅንጀት ሊሰራበት እንደሚገባ አሳስበዋል ።

የመምርያው ምክትል ኃላፊና የከተማ የስራ እድል ፈጠራ እና ምግብ ዋስትና ዘርፍ አስተባባሪ አቶ ሙራድ ያሲን ሪፖርቱን በአቀረቡበት ወቅት እንዳሳወቁት እስካሁን ለ6ሺ 291 ወጣቶች የስራ እድል የተፈጠረ ሲሆን 8ሚሊዮን 9መቶ 66ሺ 432 ብድር ተሰራጭቷል።

አቶ ሙራድ አክለውም 12ሚሊዮን 937ሺ ብር በላይ ብድር መመለሱ ገልፀው 2ሚሊየን 9መቶ 99ሺ ብር በላይ ቅድመ ቁጠባ መቆጠብ ችልዋል ነው ያሉት።

በውይይት መድረኩ የተሳተፉ አካላት እንደገለፁት በገጠርና በከተማ ያሉ ስራ አጥ ወጣቶች አልባሌ ቦታ ይውሉ የነበረ ሲሆን በተፈጠረላቸው የስራ እድል ግን ማህበረሰቡ በማገልገል በተጨማራ የራሳቸው ኑሮ እየቀየሩ እንደሚገኙ አስታውሰዋል።

አስተያየት ሰጪዎቹ አክለውም የሼድና የመሬት አቅርቦት ችግር የብድር አመላለስ፣የበጀት፣የሰው ሀይል እጥረት ለስራው ውጤታማነት ማነቆ እየሆነባቸው እንደሆነ አመላክተው በቀጣይ ግን ከዚህ በፊት እያጋጠሙ የነበሩ ችግሮችን በመለየት ትኩረት አድርገው እንደሚሰሩ ተናግረዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው ።

  • አካባቢህን ጠብቅ!
  • ወደ ግንባር ዝመት!
  • መከላከያን ደግፍ!
    በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
    Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
    Website:- https://gurage.gov.et
    Telegram:- https://t.me/comminuca
    Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *