ህብረተሰቡ የመስቀል በዓል ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲያከብር አስፈላጊውን የቅድመ ዝግጅት ስራ መከናወኑን የጉራጌ ዞን ሰላም ጸጥታ መምሪያ አስታወቀ።

የጉራጌ ዞን የጸጥታ ተቋማት ህብረተሰቡ የመስቀል በዓል በሰላም እንዲያከብር በርካታ የቅድመ ዝግጅት ስራ መሰራታቸን መግለጫ ሰጥተዋል።

የጉራጌ ዞን ሰላምና ጸጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ የሕያ ሱልጣን በሰጡት መግለጫ እንዳሉት የመስቀል በዓል በጉራጌ ብሔር ዘንድ በየዓመቱ በድምቀት ይከበራል።

በመሆኑም በርካታ የጉራጌ ተወላጆችና ቱሪስቶች ከሀገር ውስጥና ከውጭ ሀገር በመምጣት ወደ ጉራጌ ዞን እንደሚጓዙ የገለጹት አቶ የሕያ ዜጎች ያለምንም የጸጥታ ስጋት ከጠዋት 12:00 ሰዓት እስከ ምሽት 12:00 ብቻ መጓዝ ይጠበቅባቸዋል።

የትራፊክ ፍሰቱ ከአደጋ ነጻ በሆነ ሁኔታና ያለምን የጸጥታ ስጋት ህብረተሰቡ እንዲጓዝ ከቀቤና ልዩ ወረዳ፣ ከኦሮሚያ ምዕራብ ሸዋ ዞንና ከሸገር ሲቲ ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ኃላፊው ገልጸዋል።

የጉራጌ ዞን ፖሊስ አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር ገና ደገሙ በበኩላቸው በልዩ ድምቀት የሚከበረው የጉራጌ መስቀል በዓል ህብረተሰቡ ያለምን የጸጥታ ስጋት እንዲያከብር የተጠናከረ የቅድመ ዝግጅት ስራ ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል።

በዓሉ ለማክበር ከተለያዩ ቦታዎች ወደ ወልቂጤ ከተማ ገብተው ወደ ሚፈልጉት የዞኑ አካባቢ መንቀሳቀስ የሚቻለው እስከ ምሹቱ 4:00 ብቻ መሆኑን ታውቆ ህብረተሰቡ እንቅስቃሴ እንዲያደርግ ገልጸዋል።

ህብረተሰቡ በዓሉ በሰላም እንዳያከብር የሚያውኩ የማስታወቂያ ድምጾች፣ ከኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አውቅና ውጪ ገንዘብ ለመሰብሰብ የሚደረግ ጥረት፣ የርችትና የመሳሪያ ቶክስ፣ አብሮነትን የሚያሻክሩ ጹሑፎችና የህትመት ውጤቶች፣ የማይፈቀዱ ባንዲራዎች መጠቀም የተከለከሉ መሆናቸው ዋና ኢንስፔክተር አሳስበዋል።

ዜጎች የጸጥታ ስጋት የሚሆኑ የሚያጠራጥሩ ሁኔታዎች ሲያጋጥማቸው በአቅራቢያው ለሚገኝ የጸጥታ ሀይል መረጃ በመስጠት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ሊያበረክቱ እንደሚገባ ተጠቁሟል።

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃ መስቀሉ በሰላ አደረሳቹ መልዕክት የጉራጌ ዞን ሰላምና ጸጥታ መምሪያ፣ የጉራጌ ዞን ፓሊስ መምሪያ፣ የወልቂጤ ከተማ ሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤትና የወልቂጤ ከተማ ፓሊስ ጽ/ቤት በጋራ አስተላልፈዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *