ህብረተሰቡ ከፀጥታ አካላት በመቀናጀት የአካባቢውን ሰላም ከመጠበቅ ጎን ለጎን ለጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ሁለንተናዊ ድጋፍ ሊያደርግ እንደሚገባም ተገለጸ።

ነሐሴ28/2014 ዓ.ም

ህብረተሰቡ ከፀጥታ አካላት በመቀናጀት የአካባቢውን ሰላም ከመጠበቅ ጎን ለጎን ለጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ሁለንተናዊ ድጋፍ ሊያደርግ እንደሚገባም ተገለጸ።

በጉራጌ ዞን ከአደረጃጀት ጥያቄ ጋር በተያያዘ በዞኑ ሰላምና ፀጥታ ለማረጋገጥ በተሰሩ ስራዎችና በቀጣይ አቅጣጫ ዙሪያ በወልቂጤ ከተማ ውይይት ተካሂዷል።

የጉራጌ ዞን ሚሊሻ ጽህፈት ቤት ኃላፊና የሰላምና ፀጥታ መምሪያ ተወካይ አቶ አድልሃፊዝ ሁሴን የውይይት መድረኩን አስመልክተው በሰጡት መግጫ መንግስት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት በየደረጃው የዞኑ ሰላምና ፀጥታ ለመጠበቅ በተሰራው ስራ የተሻለ ለውጥ መምጣቱን ጠቁሟል።

ለዚህም ውጤት መምጣት የፀጥታ አካላት ገለልተኛ ሆነው ለህብረተሰቡ ግንዛቤ ከመፍጠር ጀምሮ ሰላም ለማስጠበቅ የተሻለ ስራ በመስራታቸው መሆኑን ተናግረዋል።

በዞኑ ኮማድ ፖስት ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ በየዕለቱ የዞኑ ሰላምና ጸጥታ ለማሰጠበቅ የተሰሩ ስራዎች እየገመገመ የተሻለ ስራ እየሰራ ይገኛልም ብለዋል።

ሀገሪቱ ተገዳ የገባችበትን የህልውና ጦርነት ሳቢያ ህብረተሰቡ የአከባቢውን ሰላም ሊያናጉ የሚችሉ ሰርጎ ገቦችን ነቅቶ በመጠበቅ የሚያጠራጥር ነገር ሲኖር መረጃ ለፀጥታ አካላት ሊሰጥ እንደሚገባ የገለጹት አቶ አብድልሃፊዝ ሁሴን እንደ ወትሮ ህብረተሰቡ ለጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት የሚያደርገው ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክሮ ማስቀጠል እንዳለበት ጥሪ አቅርበዋል።

የጉራጌ ዞን ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ጠጄ መሀመድ በበኩላቸው ሀገሪቱ አሸባሪው የህወኋት ቡድን የከፈተባትን ወረራ ለመቀልበስ የህልውና ዘመቻ ላይ በመሆኗ በሰርጎ ገቦች የህብረተሰቡ ሰላም እንዳይናጋ ከጸጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት የአከባቢውን ሰላም ነቅቶ መጠበቅ እንዳለበት በመድረኩ ግንዛቤ መፈጠሩን ገልጸዋል።

ከአደረጃጀት ጥያቄ ጋር በተያያዘ የፀጥታ መዋቅሩ ገለልተኛ በሆነ መልኩ የስጋት ቀጠናዎችን በመለየት ከሌሎች አጋዥ ሀይሎችና ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን በተሰራ ስራ ለውጥ መምጣቱን ገልፀው ይህንንም በቀጣይ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

የዞኑ የሰላምና ፀጥታ ስራ በተሻለ መልኩ ለመስራት የሰው ሀይል ውስንነት እንደነበር አስታውሰው ለዚህም የፖሊስ አባላት መልምሎ በማስመረቅ ወደ ስራ እንዲገቡ ተደርጓል ያሉት ኮማንደር ጠጄ የፖሊስ አባላቱም በአዲስ መንፈስ የህብረተሰቡን ሰላም ለማስጠበቅ በትኩረት መስራት አለባቸው ብለዋል።

የቡታጅራ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ኃላፊ አቶ ነስረዲን ሽፋ እንደገለፁት እንደ ቡታጅራ ከተማ መንግስት ያስቀመጠውን አቅጣጫ ተፈፃሚ እንዲሆን እስከ ታችኛው ቀበሌ ድረስ ኮማንድ ፖስት በማዋቀር የህብረተሰቡ ሰላም ለማረጋገጥ አበረታች ስራዎችን ተሰርተዋል።

የሀገር ሉአላዊነት ለማስከበር በዱር በገደሉ በመዋደቅ ላይ ለሚገኘው ለጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ለማድረግ ሀብት የማሰባሰብና መኪናዎች ለግዳጅ የማሰለፍ ስራ ለመስራት የተጀመሩ ስራዎች መኖራቸውን ገልጸዋል።

በውይይቱ የክልል፣ የዞን፣ የወረዳና ከተማ አስተዳደር የፀጥታ አካላትና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36CxQ
Twitter:- https://4pvf.short.gy/bTJNNn

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *