ህብረተሰቡ ተገቢውን አገልግሎት እንዲያገኝ ታማኝ ፣ቅን፣ ታታሪ ሰራተኛ ማፍራት እና እውቅና መስጠት ወሳኝነት እንዳለው የጉራጌ ዞን አስተዳደር አስታወቀ።


አመራሩና ፈጻሚው አካል የአገልጋይነት አመለካከት በመላበስ ለህብረተሰቡ የበለጠ ማገልገል እንደሚገባ የጉራጌ ዞን ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት መምሪያ ገልጿል።

መምሪያው የ2016 በጀት አመት የእውቅናና ሽልማት ማጠቃለያ መድረክ በወልቂጤ ከተማ አካሂዷል።

የጉራጌ ዞን ምክትል አስተዳደሪ አቶ አበራ ወንድሙ በዚህ ወቅት እንደገለጹት የዞኑ መንግስት ባለፉት አመታት ብዙ ፈተናዎች ቢገጥሙትም ሰራተኛው ይህንን ተቋቁሞ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን ሲሰራ ቆይቷል።

ሰራተኛው የልማቱ ቀጥተኛ ተሳተፊ በመሆኑ የሚወርዱ ፖሊሲዎች ፣መመሪያዎች እና ደንቦች በመተግበርና በማስተግበር እረገድ የማይተካ ሚና መጫወቱ አቶ አበራ ተናግረዋል።

በመሆኑም ህብረተሰቡ ተገቢውን አገልግሎት እንዲያገኝ ብቁ ሰራተኛ ማፍራትና ባስገኘው ውጤት ልክ እውቅና መስጠት ሚናው ከፍተኛ መሆኑ አስታውቀዋል።

የጉራጌ ዞን ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ትብለጥ እስጢፋኖስ ለህብረተሰቡ የበለጠ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት ታማኝ ፣ቅን እና ታታሪ ሰራተኛ ማፍራት እና እውቅና መስጠት ወሳኝነት እንዳለው ገልጸዋል።

በአለፈው አመት በአመራሩና በፈጻሚው የፍትሀዊነት ፣የቅልጥፍና ፣የውጤታማነት ችግሮች ከመቅረፍ አንጻር መሻሻሎች ቢኖሩም የህዝብ እርካታና አመኔታ ከማረጋገጥ አንጻር ቀጣይ ሰፊ ስራ መስራት ይጠበቃል ነው ያሉት።
ወ/ሮ ትበለጥ አክለውም በአንድ አንድ አገልግሎት ሰጪ ተቋሟት ላይ ለተገልጋዩ ክብር አለመስጠት ፣በአገልጋይነት መንፈስ አለመስራት ፣ለህብረተሰቡ አጥጋቢ አገልግሎት ያለመስጠት ችግር እንደነበር ለአብነት ጠቅሰዋል።

በመሆኑም አመራሩና ፈጻሚው የአገልጋይነት አመለካከት በመላበስ፣ ፈተናዎች ሳይበግሩን ፣ ለህብረተሰቡ በታማኝነትና በቅንነት የበለጠ ማገልገል እንደማገባ ወ/ሮ ትብለጥ መልእክታቸው አስተላልፏል።

ተሸላሚዎች በበኩላቸው ማንም አካል እውቅናና ማበረታቻ ሲሰጠው ለቀጣይ የበለጠ ተገቶ እንዲሰራ የሚያደርገው በመሆኑ ቀጣይ ይህንን ልምዳችን ተጠቅምን የተጣለብን ኃላፊነት ለመወጣት በትኩረት እንሰራለን ብለዋል።

በእለቱም በአመቱ ጥሩ አፈጻጸም ላሳዩ ለቀበሌ ስራ አስከያጆች ፣በመምሪያ እና በወረዳ ተቋማት ከፍተኛ ውጤት ላመጡ ባለሙያዎች ፣የየተቋሙ የህዝብ ክንፎች ፣የወረዳና የዞን ተቋማት እውቅናና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

ከእነዚህም ከዞን ተቋሟት
1ኛ ግብርና መምሪያ
2ኛ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ
3ኛ ፍትህ መምሪያ ናቸው
ከወረዳ ደግሞ
1ኛ እዣ ወረዳ
2ኛ እኖር ወረዳ
3ኛ ጌታ ወረዳ ሲሆኑ ከከተማ አስተዳደሮች ወልቂጤ ከተማ አስተዳደር 1ኛ በመሆን አጠናቋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *