ህብረተሰቡ በአረንጓዴ አሻራ ልማት ስራ ያሳየውን አንድነትና መተጋገዝ በሌሎችም የልማት ስራዎች ላይ የበለጠ ማጠናከር እንዳለበት የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳደር አስታወቀ።

ዞን አቀፍ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ በስራይ ቀበሌ ተካሄዷል።

የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሀመድ ጀማል በችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው እንዳሉት የአረንጓዴ አሻራ ልማት ስራ በዞኑ በእምነት ተቋማቶች ቀድሞ የተጀመረ ተግባር መሆኑ ጠቅሰው ለዚህም ማህበረሰቡ ለደን ልማትና ለአከባቢ ጥበቃ ስራ የቆየ ባህል እንዳለው ማሳያ ነው ብለዋል።

ህብረተሰቡ በአረንጓዴ አሻራ ልማት ስራ ያሳየውን አንድነትና መተጋገዝ በሌሎችም የልማት ስራዎች ላይ የበለጠ ማጠናከር እንዳለበት የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳደር አስታወቀ።

መንግስት ከሚሰራው የአረንጓዴ ልማት ባለፉት አስርት አመታት የጉራጌ ልማት ማህበር ማህበረሰቡን ባሳተፈ መልኩ የአረንጓዴ ልማት በሚል ሰፋፊ ስራዎች መሰራታቸው ገልፀው የህብረተሰቡም ግንዛቤ ከጊዜ ወደ ጊዜ የበለጠ እያደገ መምጣቱንም ተናግረዋል።

በዞኑ በዘንድሮ አመት ከ1 መቶ ሚሊዮን በላይ ችግኞችን ለመትከል ታቅዶ እስካሁን 85 በመቶ ማሳካት መቻሉን ገልፀው ተግባሩንም በቀጣይ አጠናክሮ ማስቀጠል ያስፈልጋል ብለዋል።

የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ የአንድ ጀንበር ስራ ብቻ ሳይሆን የሁልጊዜ ተግባር በማድረግ በንቅናቄ በሁሉም የመንግስትና የእምነት ተቋማቶች ላይ የችግኝ ተከላው ስራ የበለጠ በማጠናከር የተያዘው ግብ በአጭር ጊዜ ለማሳካት ጥረት ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።

ችግኝ መትከል ብቻ ሳይሆን የተተከሉ ችግኞችን ከመንከባከብ አንፃር በዞኑ ልምዱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን ተናግረው በቀጣይም በትምህርት ቤቶች፣ በእምነት ተቋማትና በተጎዱ አከባቢዎች ላይ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞችን መትከሉ ላይ ልዩ ትኩረት መስጠት ያስፈልጋል ብለዋል።

የደቡብ ክልል ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ዘይቱና ኢብራሂም እንዳሉት አሻራችን ለትውልዳችን በሚል መሪ ቃል በሀገር አቀፍ የተጀመረውን የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ምክንያት በማድረግ በክልሉ በአንድ ጀንበር 1መቶ ሚሊዮን በጉራጌ ዞን 19 ነጥብ 9 ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞችን መተከሉንም ገልፀዋል።

በዞኑ በአንዳድ አከባቢዎች የሚገኙ ባህርዛፎችን የመሬት ለምነትና ምርትና ምርታማነትን የሚጎዱ በመሆናቸው እነዚህን በፍራፋሬ ለመተካት እየተሰራ ያለው ተግባር የሚበረታታ ነው ብለዋል።

የተተከሉ ችግኞች ለምግብነት፣ ለጥላና ለመድሀኒትነት የሚውሉ ከመሆናቸውም ባለፈ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው መሆኑን ገልፀው ህብረተሰቡ ካለው ልምድ አንፃር የተተከሉ ችግኞች በመንከባከብና እንዲፀድቁ በማድረግ ለታለመላቸው አላማ እንዲውሉ መስራት ይኖርባቸዋል ብለዋ።

የእዣ ወረዳ አስተዳደሪ አቶ ክብሩ ፈቀደ በበኩላቸው በዘንድሮ አመት 8ነጥብ 5 ሚሊዮን ችግኞችን በማዘጋጀት እስካሁን 6ነጥብ 79 ሚሊዮን ችግኞችን መተከላቸውን ገልፀው የቀሩት በቀሪ ጊዜያት ለመትከል ርብርብ እንደሚደረግም ገልፀዋል።

የአረንጓዴ አሻራ ስራ ማጠናከር የአለም የሙቀት መጠንን እንዲቀንስ ከማድረጉም ባለፈ በግብርናው ዘርፍ ምርትና ምርታማነትን ለማረጋገጥ ሚናው የላቀ ነው ብለዋል።

የአከባቢው ማህበረሰብ የተተከሉ ችግኞችን ከሰውና ከእንሰሳት ንክኪ ነፃ ለማድረግ መከለሉን ገልፀው በቀጣይም የተተከሉ ችግኞችም ፀድቀው ውጤታማ እንዲሆኑ መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

በችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ ላይ የተሳተፉ አርሶ አደር ኑረዲን አህመድና አቶ ሸሪፍ አወል በጋራ በሰጡት አስተያየት ከዚህ በፊት ከጉድጓድ ዝግጅት ጀምሮ አካባቢውን የመከለል ስራ ሲሰሩ መቆየታቸውም ተናግረዋል።

ችግኝ መትከል የአየር ንብረቱ እንዲስተካከል ከማድረጉም ባለፈ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ሚናው ትልቅ ነው ብለዋል።

በቀጣይም አከባቢው ከእንሰሳትና ከሰው ንክኪ ነፃ እንዲሆን ከማድረጋቸውም ጎን ለጎን በመንከባከም እንዲፀቁ ለማድረግ እንደሚሰሩም ተናግረዋል።

በመረጃ ምንጭነት ገፃችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!
= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36CxQ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *