ህብረተሰቡ ለተገለገለበት ክፍያ ደረሰኝ በመቀበል በዞኑ ዉስጥ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች ቀጣይነታቸዉ ሊረጋገጥ እንደሚገባም የጉራጌ ዞን ገቢዮች መምሪያ አሳሰበ።

ግንባለፉት አስር ወራት ከ1 ቢሊየን 933 ሚሊየን 999ሺህ ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡም ተጠቁሟል።

የጉራጌ ዞን ገቢዮች መምሪያ ሀላፊ አቶ ሙራድ ረሻድ እንዳሉት
በበጀት አመቱ ከመዘጋጃና ከመደበኛ ለመሰብሰብ የታቀደዉ 2 ቢሊዮን 361 ሚሊዮን 952ሺ 762 ብር ገቢ ለመሰብሰብ ግብ ተጥሎ እየተሰራ ነዉ።

በዚህም ባለፉት አስር ወራት 1 ቢሊየን 933 ሚሊየን 999ሺህ 118 ብር መሰብሰብ እንደቻሉም አስረድተዉ ይህም የእቅዱ 82 ፐርሰንቱ ማሳካት እንደተቻለም አመላክተዋል።

ከተሰበሰበዉ ገቢ ዉስጥ የመዘጋጃ ቤት ገቢ ወደ 68 ፐርሰንት እንዲሁም የመደበኛ ገቢ 84 ፐርሰንት ማሳካት እንደተቻለም አስታዉሰዉ የመዘጋጃ ቤት ገቢ በተወሰነ መልኩ ዝቅ ያለበት እንደሆነም ተናግረዉ በጉድለት የሚታዩ ችግሮችን በመገምገም በቀሪ ጊዜያት የተሻለ ስራ መሰራት እንዳለበትም አብራርተዋል።

በጉድለት የገመገሙት የመዘጋጃ ቤት ገቢ አፈጻጸም ዝቅ እንዲል ያስቻለዉ በርካታ ዉዝፍ እዳዎች እንዳልተሰበሰቡና በዘርፉ ያለዉን ሀብት አሟጦ አለመሰብሰብ ሲሆን ለአብነት የሊዝ መሬቶች ለረጅም ጊዜ ዉዝፍ እዳዎቻቸዉ እየተሰበሰብ እንዳልሆነም አመላክተዉ የህንጻና የቤት ኪራይ እየተሰበሰበ እንዳልሆነም አብራርተዋል።

የታክስ ገቢ አፈጻጸም ተመጣጣኝ እንዳልሆነና በከተሞች አካባቢ የደረጃ ‘ሀ’ እና የደረጃ ‘ለ ‘ ግብር ከፋዮች ደረሰኝ ለተገልጋዩ ማህበረሰብ ከመስጠት አንጻር ሰፊ ዉስንነት እንዳለባቸዉ ያስረዱት ሀላፊዉ ተገልጋዩ ማህበረሰብ ደረሰኝ ለከፈለበት ክፍያ ደረሰኝ ከመጠየቅ አንጻር ሰፊ ጉድለት ያለበት እንደሆነም አመላክተዉ ተገልጋዩ ደረሰኝ ጠይቆ መቀበል እንዳለበትም አሳስበዋል።

በከተሞች አካባቢ ባለፉት ሁለትና ሶስት አመታት ጀምሮ ለተገልጋይ ደረሰኝ ከመስጠት አንጻር ሰፊ ችግር እንዳለም አመላክተዉ በዚህም ዘርፍ ተጨባጭ ዉጤት እንዲመጣ የግንዛቤ ስራ በሰፊዉ ለመስራትና የታክስ ህግ ተገዢነት የማሻሻል ስራ በቀሪ ሁለት ወራት ዉስጥ አጠናክረዉ እንደሚሰሩም አስረድተዋል።

በኢንተለጀንቶች የተለዩ በርካታ ግብር ከፋዮች መኖራቸዉም አመላክተዉ ቡታጅራ ከተማ 119 ግብር ከፋዮች ዉስጥ 6 ቱ ብቻ ናቸዉ ለተገልጋዩ ደረሰኝ የሚሰጡት ብለዉ በተመሳሳይ ወልቂጤ ላይም ከ119 ግብር ከፋዮች 4ቱ ብቻ ደረሰኝ የሚሰጡ ሲሆን ሌሎችም ከተሞች ጨምሮ አብዛኞች ለተገልጋዮ ማህበረሰብ ደረሰኝ እንደማይሰጡም ገልጸዋል።

በእነዚህ አካላቶች ላይ ህግ የማስከበርና አስተዳደራዊ ቅጣት እየተወሰደባቸዉ እንደሆነም አመላክተዉ በዚህ አንድ ወር ዉስጥ ከ34 በላይ ግብር ከፋዮች እያንዳዳቸዉ 50 ሺህ ብር እንዲቀጡ አድርገናል ብለዉ ደረሰኝ የማይሰጡና የተለዩ ወልቂጤ ፣ አገና ቡታጅራ ፣ኢንሴኖ ከተሞች ላይ ወደ 34 ግብር ከፋዮች እንዲቀጡ ተደርጓል ብለዉ ይህም ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አብራርተዋል።

ከዚህም ጎን ለጎን በዘንድሮ አመት የደረጃ ‘ሐ’ ግብር ከፋዮች የእለት ሽያጭ ግመታ ላይ ባለፉት ስድስት አመታት በክልሉ በነበሩ የጸጥታ ችግሮች ምክንያት እንዳልተሰራና በየ ሶስት አመቱ መታደስ እንዳለበት ተናግረዉ የእለት ሽያጭ ግመታዉ ስራ ከመጋቢት 18/2015 እስከ ሚያዚያ 18 /2015 የግመታዉ መጠቃለል አለበት ብለዉ ግብ ጥለዉ በመስራት በዚህም በዞኑ 20 ሺህ 2መቶ 44 የደረጃ ሐ ግብር ከፋዮች የእለት ሽያጭ ግመታ ተደርጎላቸዋል ብለዋል።

ግብር ከፋዩ የሚከፍለዉ ግብር ፍትሃዊ መሆን አለበት ብለዉ በደረጃ” ሐ”ግብር ከፋዮች መረጃ አደረጃጀት ማዘመን እንደሚገባም አመላክተዉ በከተሞች አካባቢ የአሁኑ የገብያ ዋጋ ሊመጥን የማይችልና በቀን የሚሸጠዉ ሽያጭ በጣም አሳንሶ የማሳወቅና ያደበቅ አዝማሚያዎች እንደተስተዋለም አስረድተዉ እነዚህ ችግሮች ደረጃ በደረጃ ለመቅረፍ አበክረዉ እንደሚሰሩም አስታዉቀዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *