ህብረተሰቡን በማሳተፍ በጸረ ሙስና ትግሉ ላይ ተጨባጭ ለዉጥ እንዲመጣ ከመቼዉ ጊዜ በላይ በትኩረት እንደሚሰራ የጉራጌ ዞን አስተዳደር የስነ ምግባር ኦፊሰር አስታወቀ።

መስከረም 13/2015 ዓ .ም

ህብረተሰቡን በማሳተፍ በጸረ ሙስና ትግሉ ላይ ተጨባጭ ለዉጥ እንዲመጣ ከመቼዉ ጊዜ በላይ በትኩረት እንደሚሰራ የጉራጌ ዞን አስተዳደር የስነ ምግባር ኦፊሰር አስታወቀ።

ባለፈዉ በጀት አመት ከ29 ሚሊየን ብር በላይ የተመዘበረ የመንግስት ሀብት ማስመለስ መቻላቸዉም ተጠቁሟል።

ዞኑ ባለፈዉ በጀት አመት በአፈጻጸም ግንባር ቀደም በመሆን የዋንጫ ፣ የሜዳሊያና የሰርተፍኬት ተሸላሚ መሆኑም ሆኗል።

የጉራጌ ዞን አስተዳደር የስነ ምግባር ኦፊሰር አቶ ጀማል አህመድ እንዳሉት ሙስና ለመከላከል ማህበረሰቡን በስፋት የማስተማር ስራዉ እየተሰራ ነዉ።

የስነ ምግባር ኦፊሰር ስራ መሰረት የሚያደርገዉ 80 ፐርሰንት የማስተማር እንዲሁም 20 ፐርሰን የተመዘበረ የህዝብ ሀብትና ንብረት የማስመለስና መረጃዎችን በተለያዩ መንገድ ፈትሾ የማዉጣት ስራ እየሰሩ እንደሆነም አስረድተዋል።

በየደረጃዉ በሚገኙ ተቋማት የተደራጁ የስነ ምግባር ኦፊሰሮች እና በየተቋማት ሰራተኞችና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ በስፋት መሰራቱም አስታዉሰዋል።

ባለፈዉ በጀት አመት 52 ሺህ ለሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች የፊት ለፊት ስልጠና ለመስጠት አቅደዉ ከ54 ሺህ በላይ ሰዎች የግንዛቤ ስልጠና መስጠት እንደቻሉም አስታዉሰዉ ሙስና የአስቸኳይ መከላከል ላይ ለ4 መቶ 57 ሺህ ሰዎች የማሰልጠን ስራ እንሰራለን ብለዉ ከ4መቶ 72 ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን የማሰልጠን ስራ መስራታቸዉም አስረድተዋል።

በየትምህርት ቤቱ የተቋቋሙ የተለያዩ የተማሪዎች ክበባት በማንቀሳቀስ በሙስና የሀገር ሀብትና ንብረት እንዳይመዘበር የመከላከል ስራ ላይ በሰፊዉ የግንዛቤ ስራ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

በአስቸኳይ መከላከል ስራ ላይ ከ24 ሚሊየን ብር በላይ የተመዘበረ ሀብት ማስመለስ መቻላቸዉም አስረድተዉ በአፈር ማዳበሪያ ፣በኮንስትራክሽን ፣ በግብር ሰነዶች በማጭበርበር የወጡና ከህዝብ ተሰብስበዉ ለህዝብ መዋል ሲገባዉ ለህዝብ ሳይዉል የቀሩትን ሀብት ለማስመለስ በተሰራዉ ቅንጅታዊ ስራ 29 ሚሊየን ብር ማስመለስ መቻላቸዉም አስታዉሰዋል።

የጸረ ሙስና ትግሉ የበለጠ ለመከላከል ከሚዲያዎች ጋር ትስስር የመፍጠርና በዘርፉ በተሰሩ ስራዎች የመጡ ለዉጦችን ለህዝብ የመግለጽ ስራ ይሰራል ብለዋል።

ተመዝብረዉ የወጡ ሀብቶች እንዲመለሱ ለማድረግ ከህዝብ የሚመጡ ጥቆማዎች በመቀበልና አስቀድመን ለመከላከል በተሰራዉ ስራ ከ450 በላይ ጥቆማ ከህብረተሰቡ እንደተሰጣቸዉም አመላክተዋል።

ከተሰጡ ጥቆማዎች መካከል 252 በአስተዳደራዊ የተፈቱና 37ቱ በፖለቲካዊ የተፈቱ ሲሆን የተቀሩት ጥቆማዎች ወደ ዓቃቤ ህግ በመዉሰድ ምርመራ እየተደረገባቸዉ እንደሆነም አብራርተዋል።

ዞኑ በክልል ደረጃ ሲመዘን በአስተዳድር ሴክተር ፋይናንስ ሴክተር ሶስተኛ ፣ በትምህርት ቤቶች ክበባት በክልሉ አንደኛ በመዉጣት እንዲሁም በአስተዳደራዊ ስራ ላይ አንደኛ በመሆን የሜዳሊያ ፣ የዋንጫና የሰርተፍኬት ተሸላሚ መሆኑን ገልጸዋል ሲል የዘገበዉ የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ነዉ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *