ሁለተኛው ዙር የፖሊዮ በሽታ መከላከያ ክትባት ዕድሜያቸው ከ 5 ዓመት በታች ለሆኑ ከ3 መቶ ሺህ በላይ ህፃናት እንደሚሰጥ የጉራጌ ዞን ጤና መምሪያ አስታወቀ።

መምሪያው በሁለተኛው ዙር የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ለወረዳና ከተማ አስተዳደር ጤና ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች እና ለሌሎች ባለድርሻ አካላት ስልጠና መስጠቱንም ተመልክቷል።

የዞኑ ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ሸምሱ አማን ስልጠናውን ባስጀመሩበት ወቅት እንደተናገሩት የፖሊዮ በሽታ መከላከያ ክትባት በአግባቡ በመስጠት ተደራሽ ለማድረግ ባለድርሻ አካላት ተቀናጅተው ሊሰሩ ይገባል።

ህፃናትን እድሜ ዘመናቸውን ለአካል ጉዳትና ለሞት የሚዳርገውን የፖሊዮ በሽታ ለመከላከል የቤት ለቤት የፖሊዮ በሽታ መከላከያ ክትባት በዘመቻ የሚሰጥ ሲሆን ክትባቱ ሳይባክን በጥንቃቄ መስጠት ይገባል ብለዋል ኃላፊው።

የፖሊዮ በሽታ የህፃናትን የእጅና የእግር ጡንቻ የሚያዳክምና የሚያልፈሰፍስ ገዳይ በሽታ ቢሆንም በሽታውን በክትባት መከላከል ስለሚቻል ክትባቱ በዘመቻ ለመስጠት አስፈልጓል ብለዋል።

አያይዘውም ኃላፊው የፖሊዮ በሽታ መከላከያ ክትባት ቤት ለቤት ከመስጠት ጎንለጎን ለእናቶች በማህጸን ወደ ውጭ መውጣት ላይ ያላቸው ግንዛቤ እንዲዳብርና በጤና ተቋማት ክትትል እንዲያደርጉ መስራት እንደሚገባ አብራርተዋል።

በየ ወረዳው የሚመረቁ ሞዴል ቀበሌዎች በወባ፣ በስነ ምግብና በሌሎች ተጓዳኝ ምክንያቶች የሚፈጠሩ የጤና ችግሮች ለመከላከል ጉልህ ሚና የሚጫወቱ በመሆናቸው በጤናው ዘርፍ የሚፈለገውን ውጤት ለማስመዝገብ በቁርጠኝነት መስራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

በመምሪያው የጤናና ጤና ነክ ጉዳዮች ድንገተኛ ምላሽ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሳህሌ ክብሩ በበኩላቸው በዞኑ ህፃናትን እድሜ ልካቸው ለአካል ጉዳትና ለሞት የሚዳርገውን የፖሊዮ በሽታ ለመከላከል የቤት ለቤት የፖሊዮ በሽታ መከላከያ ክትባት ዘመቻ ከሚያዝያ 7 እስከ 10/2014 ድረስ እንደሚሰጥ ገልጸዋል።

የፖሊዮ በሽታን በክትባት መከላከል ስለሚቻል ወላጆችና አሳዳጊዎች ዕድሜያቸው ከ 5 ዓመት በታች የሆኑ ህፃናትን ከዚህ ቀደም የፖሊዮ በሽታ መከላከያ ክትባትን ቢከተቡም ባይከተቡም ቤት ለቤት በሚካሄደው የክትባት ዘመቻ ህፃናቱን እንዲያስከትቧቸው መልዕክት አስተላልፈዋል።

የስልጠናው ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት ከዚህ ቀደም በክትባት አሰጣጥ ላይ ይስተዋል የነበረው ችግር ለመቅረፍ አቅም ፈጥሮላቸዋል።

የፖሊዮ በሽታ ክትባት በሚፈለገው ጊዜው ማግኘት ስለማይመቻል ወላጆና አሳዳጊዎች ፖሊዮን ለማጥፋት በሚደረገው ዘመቻ ልጆቻቸው ለማስከተብ በንቃት እንዲሳተፉ እንሰራለን ብለዋል።

በመረጃ ምንጭነት ገፃችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!

=ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *